✍ ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
☝️ መንበረ ሰላማ የሚባል የፕትርክና መንበር ኢትዮጵያ ውስጥ ኖሮ አያውቅምና አጭበርባሪዎቹ የትግራይ ጳጳሳት እረፉ‼️
👉 አምና አቡነ መርቆሬዎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ያረፉ ዕለት ሚዲያው ላይ ያሉ "ሰባኪ ነን!" የሚሉ ጥራዝ ነጠቆች አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃንን የመጀመሪያ አድርገው ቅዱስ ፓትርያርኩን አቡነ መርቆሬዎስን 114ኛው ፓትርያርክ አድርገው ሲገልጹ አቡነ ሰላማ ጳጳስ እንጅ ፓትርያርክ ያልነበሩ መሆናቸውን በማንሣትና ከእሳቸው በኋላ የእኛን ማለትም ኢትዮጵያውያንን ጳጳሳት እስካገኘንበት ጊዜ ድረስ ከግብጽ ይመጡ የነበሩት መቶ ዐሥሩ ጳጳሳት በሙሉ ጳጳሳት የነበሩ እንጅ ፓትርያርክ ያልነበሩ መሆናቸውን በመግለጥ ይሄ አገላለጻቸው ስሕተት መሆኑን ገልጨ ጽፌ ነበር። ከዚያ በኋላ ከፊሎቹ ሲታረሙ ከፊሎቹ የማያነቡና የማይሰሙ ግን አሁንም በስሕተታቸው ቀጥለዋል‼️
⚠️ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከግብጽ ቤተክርስቲያን ጋር በተደረገ እጅግ አታካች ተጋድሎ የራሷን ጳጳሳት ያገኘችው በ1922ዓ.ም. ሲሆን የራሷን ፓትርያርክ ያገኘችው ደግሞ በ1951ዓ.ም. ነው። ከዚያ በፊት ሀገራችን ኢትዮጵያ የግብጽ ቤተክርስቲያን አንድ ሀገረስብከት ተደርጋ ተቆጥራ ለ1600 ዓመታት ያህል አንድ አንድ ጳጳሳት እየተላላት ያገለግሉ ነበር እንጅ የራሷ ሲኖዶስና የራሷ ፓትርያርክ አልነበራትም ነበር‼️
📌 እንግዲህ የትግራይ ጳጳሳት ያልገባቸውና ያልተረዱት ይሄንን ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መንበረ ፓትርያርክ የተተከለው በ1951ዓ.ም. ሲሆን መንበረ ፕትርክናው የተተከለውም አዲስ አበባ ነው። እኒህ የመጀመሪያው ፓትርያርክም አቡነ ባስልዮስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ናቸው። ከዚያ በፊት አክሱምም ሆነ ሌላ ቦታ በኢትዮጵያ ውስጥ ፓትርያርክ ተሹሞ አያውቅም። ፓትርያርክ ተሹሞ ስለማያውቅም መንበረ ፓትርያርክም ኖሮን አያውቅም‼️
🔴 የቅዱሱ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ ፕትርክናም በእግዚአብሔር ፈቃድ ቀጥታ ከእግዚአብሔር የተገኘ እንጅ እንደሌሎቹ በሐዋርያት ትውፊት መሠረት በአንብሮተ ዕድ የተገኘ ስላልሆነ እሱን እዚህ ላይ አንጠቅስም። እሱም ቢሆን መንበሩ የነበረው ሸዋ ነው እንጅ አክሱም አልነበረም‼️
ስለሆነም የትግራይ ጳጳሳት መንበረ ሰላማ እያሉ የሚሉት ነገር ዝም ብለው ጨርሶ ባልገባቸው ነገር ላይ እየቀባጠሩ ወይም ደግሞ አውቀው ለማደናቆርና ለመበጥበጥ ፈልገው ሊያደናቁሩበት ካልሆነ በስተቀር መሠረት ያለው ነገር አይደለም። አዎ አክሱም የአቡነ ሰላማ ጳጳስ ዘኢትዮጵያ መንበር ነበረች አሁንም ይሄ መንበረ ጵጵስና አለ ወደፊትም ይኖራል። ይህ መንበር ግን የጵጵስና መንበር ነው እንጅ የፕትርክና መንበር አልነበረም ወይም አይደለም‼️
🔔 ስለሆነም "ለሃይማኖታችን ቆመናል!" የምትሉ ተጋሩ ካላቹህ እነኝህን አማሳኝና ካድሬ የትግራይ ጳጳሳትን "እረፉ አታጭበርብሩ!" በሏቸው። ነገሩ ፖለቲካዊ እንጅ ፈጽሞ ቀኖናዊም ሆነ ሌላ መሠረት የለውም። የሚገርመው ነገር "የኦርቶዶክስንና የአማራን አከርካሪ እንዳያንሠራራ አድርገን ሰብረነዋል!" ያለውን የዲያብሎስ አገልጋይ ፀረ ቤተክርስቲያንን ወያኔን በፍጹም ትጋትና ታማኝነት ሲያገለግሉ ኖረውና አሁንም እያገለገሉ ባሉበት ሁኔታ በዚህም አገልግሎታቸው የቤተክርስቲያንን አከርካሪ ያሰበሩ አጋንንት ሆነው እያለ ነው እንግዲህ ለቤተክርስቲያንና ለሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ መስለው ምንንት ቅብርጥስ እያሉ ሰው ለመምሰል ጥረት እያደረጉ የሚገኙት‼️
😭 መጀመሪያ እነሱ እራሳቸው ወያኔ ጦርነት ከፍቶ ያንን ሁሉ ሕዝብ በግፍ ሲጨፈጭፍ ወያኔን አውግዘዋል ወይ??? ከዚያስ በኋላ "ተዋጉ፣ ጀግኑ፣ ጨክኑ!" እያሉ ባርከው ላኩብን እንጅ ወረው በያዟቸው የአማራ መሬቶች ያንን ሁሉ አረመኔያዊ ግፍ ሲፈጽሙ "የማይገባ ተግባር ነው!" ብለው አውግዘዋል ወይ⁉️
❓በየትኛው የሞራል ልዕልናቸው ነው ታዲያ እነኝህ ሰው መሳይ አጋንንት ሊመጻደቁብን እየሞከሩ ያሉት ለመሆኑ⁉️
Blogger Comment
Facebook Comment