✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ የላሊበላ ዓብያተክርስቲያናት እናት የሆነው ጥንታዊው ገዳም ሚካኤል እምባ ደብረሲና ድንቅ ነው፤ ሀገራችንን አናውቃትም እኮ! በአራተኛው መቶ ክፍለዘመን በ፫፻፴፰/ 338 ዓ.ም ላይ ቅዳሴ የተጀመረበት ታሪካዊ ገዳም ነው። ገዳም ሚካኤል እምባ በምስራቅ ትግራይ ወረዳ አፅቢ ወምበርታ ሚካኤል እምባ ቀበሌ የሚገኝ ታሪካዊ ግዙፍ ውቅር ቤተክርስቲያን ገዳም ነው። ከኣፅቢ ከተማ በ ፲፮/16 ኪሎሜትር አቅራቢያ የሚገኘው ይህ ታሪካዊ ገዳም የተሠራበት ዕለት በትክክል ባይታወቅም፤ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በ፫፻፴፰/338 ዓ.ም ላይ ቅዳሴ የተጀመረበት ገዳም ነው።
❖❖❖ የቅዱስ ሚካኤል በረከት በያልንበት ይድረሰን! እንደ እነ አብርሃ ወአፅብሃ ለእግዚአብሔር አምላክ የሚገዙና የሚታዘዙ ፍትሃዊ መሪዎችን ይስጠን! አሜን! አሜን! አሜን! ❖❖❖ ✞✞✞[መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮፥፲፪]✞✞✞ “ግፍን መሥራት በንጉሥ ዘንድ ጸያፍ ነገር ነው፥ ዙፋን በጽድቅ ይጸናልና።” ✞✞✞[መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፥፰]✞✞✞ “በፍርድ ወንበር የተቀመጠ ንጉሥ ክፉውን ሁሉ በዓይኖቹ ይበትናል።” ✞✞✞[መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ ምዕራፍ ፰፥፲፭]✞✞✞ “ዳዊትም በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤ ዳዊትም ለሕዝቡ ሁሉ ፍርድንና ጽድቅን አደረገላቸው።” |
Blogger Comment
Facebook Comment