✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
✞ ከአንጾኪያ፣ እስክንድርያ፣ እየሩሳሌም፣ ሮም እና ባይዛንቲየም፣ ጋር መካተት ያለበት ሌላ ከተማ ወይም አገር ቢኖሩ ኖሮ ከጎናቸው መሆን ያለባት ኢትዮጵያ ናት። ዛሬ የኒቆሚዲያው ዩሴቢየስ የቤተክርስቲያን ታሪክ ፪ ኛን መጽሐፍ ከዘኍልቍ ምዕራፍ ፲፪፣ የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፰ እና ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር ሲወሰዱ፣ ኢትዮጵያ በክርስትና እምነት ውስጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነች ሀገር እንደነበረች የሚገልጹትን አንዳንድ ጠቃሚ እውነታዎችን ይዞ ይጀምራል።
ግን ይህችኛው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ዘ-መንፈስ ናት በሰይጣን የምትመራዋ ዓለም ተገቢውን ትኩረት ልትሰጠው ያልፈለገችው። ላለፉት ሁለት ዓመታት እንኳን ከሚሊየን በላይ የተጨፈጨፈው ኢትዮጵያዊ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኑ ሆኖ ሳለ፤ ይህ ጭፍጨፋ ሃይማኖታዊ ግብ እንዳለውና በሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ለመናገር የደፈረ አንድም 'ኢትዮጵያዊ' የለም።
ለዚህም እኮ ነው፡ እንኳን የተቀረው ዓለም፡ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኑ ዓለም ሳይቀር ድጋፉን እንዲነፍገን የተደረገው። ከዚህ ጨፍጫፊ የጋላ-ኦሮሞ አገዛዝ ጋር ጎን እንደ ግብጽና ሩሲያ ያሉ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ሃገራት ሳይቀሩ የተሰለፉት። በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው ግፍና ጥቃት በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ላይ መሆኑን እያንዳንዳችን እስካላሳወቅን ድረስና፣ “የዘር ማጥፋት ወንጀል በትግራዋይ ላይ፣ በዐምሓራ ላይ፣ በጉራጌ ወዘተ ላይ ነው የተፈጸመው” ማለቱን፣ ብሎም ክቡር መስቀሉን እና ታቦተ ጽዮንን በመሸከም ፈንታ የሉሲፈርን/ቻይናን ሰንደቅ ማውለብለቡን ከቀጠልን እግዚአብሔር አምላክም ፈጽሞ አይሰማንም፣ ከገባንበት መቀመቅም አያወጣንም። ምክኒያቱም ይህ ሃቁ አይደለምና ነው፤ ምክኒያቱም ፈጣሪያችን 'ትግራዋይ'፣ 'ዐምሓራ'፣ ጉራጌ ወዘተ የተሰኙትን የስጋ ማንነትና ምንነት ያላቸውን ብሔሮችን ወይንም ነገዶችን አያውቃቸውምና ነው።
Blogger Comment
Facebook Comment