አሁን ደግሞ በረሃብ አማካኝነት ሕዝቤን ለመቅጣት ወስነዋል


✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

አሜሪካ (USAID) እና የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ለትግራይ፣ ኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ አቆሙ፡ ስውር የዘር ማጥፋት ዘመቻው ቀጥሏል፡ አሁን ደግሞ በረሃብ አማካኝነት ሕዝቤን ለመቅጣት ወስነዋል። ከሉሲፈራውያኑ ስንጠብቅ የነበረው ይህ ነው!

ታዲያ ከሁለት ዓመት በፊት ያወሳነው ነገር እየተከሰተ አይደለምን?! የኖቤል የሰላም ሽልማት ለዘር ማጥፋት ወንጀል ቀብድ/ፈቃድ ነው አላልምን?! እነዚህ አረመኔዎች በቂ ክርስቲያን ሕዝብ አላለቀላቸውም፤ አሁን ደግሞ ከድሮንና ጥይት የተረፈውን እንደለመዱት እርስበርስ እየተወነጃጀሉ በረሃብና በሽታ ለመጨረስ ተዘጋጅተዋል። አስቀድመን ጠቁመናል፤ ሻዕብያም፣ ህወሓትም፣ ኦነግ/ብልጽግናም፣ አዴፓ/በአዴንም፣ አብንም፣ ኢዜማም ወዘተ ሁሉም አረመኔ የሉሲፈራውያኑ አገልጋዮች ናቸው። እነ ኢሳያስ አፈወርቂ/አብደላ ሃሰን፣ ደብረ ሲዖል፣ ጌታቸው ረዳ፣ ግራኝ አብዮት አሕመድ ዓሊ፣ ብርሃኑ ነጋ፣ ጃዋር መሐመድ ሁሉም የሲ.አይ.ኤ እና ኤን.ኤስ.ኤ ቅጥረኞች ናቸው። አይናችን እያየው ነው!

የተባበሩት መንግስታትን ጨምሮ ሁሉም ዓለም አቀፋዊ አካላት የጀርመኑን ፈላስፋ ጆርጅ ሄገለን ኋላ ቀር ዲያብሎሳዊ ሂደት ፤  “ችግር – ምላሽ – መፍትሔ / ብሎም “Thesis-Antithesis-Synthesis (ተሲስ ፣ ፀረ-ፀረስታ እና ውህደት/መደመር) ተከትለው ነው የሚንቀሳቀሱት።

ሉሲፈራውያኑ ሻዕብያን + ህወሓትን + ኦነግ/ብልጽግናን እንደ አሻንጉሊት በመጠቀም፤ “እርስ በርሳችሁ የተጋጫችሁ መስላችሁ ሕዝበ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኑን ጨፍጭፉልን፤ የሕዝብ ቁጥራችሁን ቀንሱ። ከዚያም 'ሰላም! ስላም!' እያላችሁ ተደራደሩ፤ እኛ ገንዘቡንም ምግቡንም እንለቅላችኋለን። በመኻል የኩኩሉሉ ድብብቆሽ ጨዋታውን 'በሰላም' ትቀጥሉና ገንዘቡንም ምግቡንም ደብቁት፣ ስረቁት በዚህ መልክ ሌሎች ሚሊየን ክርስቲያኖች እንዲያልቁ እናደርጋለን፤ ለዓለምም የሕዝበ ክርስቲያኑ ሕፃናት እንደበፊቱ በረሃብ ደቅቀውና ኮስምነው የሚያሳዩትን ምስሎች በመልቀቅ ኢትዮጵያን በድጋሚ እናዋርዳታለን።

❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፹፫፤]❖❖❖

፩ አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል።

፪ እነሆ፥ ጠላቶችህ ጮኽዋልና፥ የሚጠሉህም ራሳቸውን አንሥተዋልና።

፫ ሕዝብህን በምክር ሸነገሉአቸው፥ በቅዱሳንህም ላይ ተማከሩ።

፬ ኑ ከሕዝብ እናጥፋቸው፥ ደግሞም የእስራኤል ስም አይታሰብ አሉ።

፭ አንድ ሆነው በአንተ ላይ ተማከሩ፤ በአንተ ላይ ቃል ኪዳን አደረጉ፤

፮ የኤዶማውያን ድንኳኖች እስማኤላውያንም፥ ሞዓብም አጋራውያንም፥

፯ ጌባል አሞንም አማሌቅም፥ ፍልስጥኤማውያንም ከጢሮስ ሰዎች ጋር፤

፰ አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፥ ለሎጥ ልጆችም ረዳት ሆኑአቸው።

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment