የዓለምን ጦርነት የምትመራው አክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ናት

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

የአውሎ ነፋሳቱንና የመሬት መንቀጥቀጡን አቅጣጫ መከተሉ ብቻ በቂ ማስረጃ ነው። አዎ! በሂደት፤ ላለፉት መቶ ሰላሳ ዓመታት፤ ላለፉት ላለፉት ሃምሳ ዓመታት፣ ላለፉት አምስት ዓመታት እየተሠራ ያለው በሕይወት የተረፈው 'ኢትዮጵያዊ' ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን እንዲጠላ ማድረግ ነው። ለዚህም ነው በቋንቁ ከፋፍለውና የሉሲፈራውያኑን ሰንደቅ ዓላማ አስይዘው እርስበርስ በማባላት ላይ ያሉት።

ዛሬ፡ መላዋ ዓለም በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ስላለው ግፍና መከራ ዝም ጭጭ ብላለች፤ የስጋ ነገር ነውና ለወሬው ዩክሬን ትበልጥባታላች። እያየነው እኮ ነው። ምክኒያቱም፤ የመንፈሳዊውን ሕይወት በሚመለከት “በቀል የኔ ነው!” ያለን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላካችን ኃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ ተረክቦና ከቅዱሳኑ ጋር ሆኖ ሥራውን እየሠራ ስለሆነ ነው።

✞✞✞ የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ✞✞✞

❖❖❖[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፭፥ ፴፩፡፴፬]❖❖❖

የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል። ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።”

ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ(ማቴ ፳፭ስለ ጌታችን ዳግም አመጣጥ እና በፍርድ ወንበር መቀመጥ ሲገልጽ «የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፤ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል።» በማለት ጻድቃንን በበጎች፣ ኃጥአንን በፍየሎች መስሎ ጻድቃንን ለክብር በቀኝ፣ ኃጥአንን ለሃሳር በግራ ለይቶ ያቆማቸዋል። ቀጥሎም ጌታችን ክርስቶስ በፍርድ ቃል በቀኙ ያሉትን «እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።» ይላቸዋል። ነገር ግን ጻድቃን ብዙ መልካም ሥራ ሰርተው ሳለ ምንም እንዳልሰሩና እንዳላደረጉ ሆነው ከእግዚአብሔር ቸርነት የተነሳ ክብር እንደተሰጣቸው አውቀው በትህትና ቃል «ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህእንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን?» ይሉታል። እርሱም መልሶ በሕይወት ዘመናቸው ከእነርሱ ለሚያንሱት ያደረጉትን መልካም የቸርነትና ትህትና ሥራ እንደዋጋ ቆጥሮላቸው «እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት» ብሎ ጻድቃንን ወደ ዘለዓለም ሕይወት ይሰዳቸዋል።

ነገር ግን በኃጥአን ላይ ከዚህ በተቃራኒ ፍርዱም ሆነ የእነሱም ምላሽ የተለየ ይሆናል። ጌታም እርሱን ባላመለኩት መጠንና ከሰይጣናት በተስማማ ሁኔታ መንገዳቸውን ባደረጉ ልክ እንዲህ በማለት ይፈርድባቸዋል፤ «እናንተ ርጕማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘለዓለም እሳት ከእኔ ሂዱ። ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።» እነርሱ ግን ፍርዱን በመቃወም እንዲህ እያሉ ይከራከራሉ። «ጌታ ሆይ፥ ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም?» ጌታችንም በምላሹ የርህራሄን ሥራ ለታናናሾቻችሁ አልሰራችሁም ፤ ያን አለመስራታችሁ ለኔ አለመስራታችሁ ነው ብሎ ወደ ዘለዓለም ቅጣት ይሰዳቸዋል።

ያቺ የፍርድ ቀን የዓለም ፍጻሜ ናት። በዛች ቀን መስማት እንጂ መመለስ መከራከር የለም። የዚያች ቀን የፍርድ ውሳኔ ዛሬ በምድር ላይ የምንፈጽመው የአምልኮና የመልካም ወይም የክፉ ምግባር ውጤት ነው። ዛሬ አካሄዳችንን ከእግዚአብሔር ጋር ካደረግን ከእግዚአብሔር ጋር በተስፋዪቱ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት እንሆናለን፤ዛሬ አካሄዳችንን ከዲያብሎስ ጋር ካደረግን ግን በግራ ከዲያብሎስ ጋር እንቆማለን፤ትሉ በማያንቀላፋ እሳቱ በማይጠፋ በገሃነም እሳት መኖር ግድ ይለናል። የዛሬ የአምልኮ አያያዛችን የፍጻሜውን ቀን ይወስነዋልና ዛሬ ሳናመነታ አኗኗራችንን እንወስን።

አባታችን አባ ዘ-ወንጌል በአንድ ወቅት እንዲህ ብለውን ነበር፦"ኢትዮጵያን በዚህ ወቅት እያስተዳደሯት ያሉት ጠላቶቿ ናቸው” አሥር በመቶ የሚሆነው ኢትዮጵያዊ ብቻ ነው የኢትዮጵያን ትንሣኤ ማየት የሚችለው” ያሉንም ትክክል መሆኑን እያየነው ነው። እንግዲህ የተበከለውና የቆሸሸው የመጽጂያ ሰፊ ጊዜና ብዙ አጋጣሚዎች ለመቶ ዓመታት ያህል ተሰጥቶት ነበር፤ ግን ዛሬም፤ አውቆቱም ሆነ ሳያውቀው፤ አብዛኛው “ኢትዮጵያዊ” 666 አውሬውን በማገልገል ላይ ነው። መላው ዓለምም ይህን አውቆታልአሁን ጊዜው እያለቀ ነውይህ ማስጠንቀቂያ ከትግራይ አብራክ ለወጡትና እግዚአብሔርንና ጽዮን ማርያም እናቱን ለከዱት ለሻዕቢያዎችና ህወሓቶችም ጭምር ነው።

❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፯፥፳፰]❖❖❖

እግዚአብሔር ፍርዱን ይወድዳልና፥ ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና፤ ለዘላለምም ይጠብቃቸዋል ለንጹሓንም ይበቀልላቸዋል፤ የኅጥኣን ዘር ግን ይጠፋል።”

በተቀረው ዓለም በጣም ብዙ ሕዝብ ይረግፋል፤ በተለይ ኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ በሚቆጣጠሩት የዓለማችን ክፍል። እነ አሜሪካ ይጠፋሉ፣ እነ ቱርክ ኢራንና ሳውዲ አረቢያ ድራሽ አባታቸው ይጠፋል።

❖❖❖[የዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ ፳፪]❖❖❖

  •  በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውኃ ወንዝ አሳየኝ።
  •  በወንዙም ወዲያና ወዲህ በየወሩ እያፈራ አሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፥ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ መፈወሻ ነበሩ።
  •  ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል፥ ፊቱንም ያያሉ፥
  •  ስሙም በግምባሮቻቸው ይሆናል።
  •  ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፥ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።
  •  እርሱም። እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸው፥ የነቢያትም መናፍስት ጌታ አምላክ በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን ሰደደ።
  •  እነሆም፥ በቶሎ እመጣለሁ። የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብፁዕ ነው አለኝ።
  •  ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ።
  •  እርሱም። እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።
  •  ለእኔም። ዘመኑ ቀርቦአልና የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው።
  • ፲፩ ዓመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፥ ርኵሱም ወደ ፊት ይርከስ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፥ ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ አለ።
  • ፲፪ እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።
  • ፲፫ አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።
  • ፲፬ ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።
  • ፲፭ ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።
  • ፲፮ እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።
  • ፲፯ መንፈሱና ሙሽራይቱም። ና ይላሉ። የሚሰማም። ና ይበል። የተጠማም ይምጣ፥ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።
  • ፲፰ በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የትንቢት ቃል ለሚሰማ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ፤ ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል፤
  • ፲፱ ማንምም በዚህ በትንቢት መጽሐፍ ከተጻፉት ቃሎች አንዳች ቢያጎድል፥ በዚህ መጽሐፍ ከተጻፉት ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ዕድሉን ያጎድልበታል።
  •  ይህን የሚመሰክር። አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።
  • ፳፩ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment