✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ያልተባበሩት መንግስታት፤ ለዩክሬን የደቂቃ ጸሎት አደረጉላት የኢትዮጵያው የዘር ማጥፋት ጦርነት ሰለባ ለሆኑት ከ፩/1 ሚሊዮን በላይ ክርስቲያኖች ግን እንኳን ጸሎት ሊያደርጉ፤ የተፈጸመው ጥፋት እንዳይመረመር ተግተው በመሥራት ላይ ናቸው።
ምክኒያቱም፤ ሁሉም የዚህ የዘር ማጥፋት ወንጀል አካላት በመሆናቸው ነው። ከአንቶኒዮ ጉቴሬስ እስከ ቴዎድሮስ አድሓኖም፣ ከአሜሪካ እስከ ዩክሬይን፣ ከኢራን እስከ እስራኤል፣ ከቱርክ እስከ ኤሚራቶች፣ ከተባበሩት መንግስታት እስከ አፍሪካ ህበረት ሁሉም በጥንታውያኑ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ላይ ተናብበው ጭፍጨፋውን አካሂደዋል።
ዛሬ በግልጽ የምናየው ሤራ የተጠነሰሰው ከመቶ ሰላሳ ዓመታት ጀምሮ፤ ከዓድዋው ድል በኋላ ነው።
የዓድዋው ድል የእግዚአብሔር አምላክ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስና የአክሱም ጽዮናውያን ድል ብቻ ነው!
የዓድዋው ድል ኢትዮጵያ ኃይሏ ፡ በቅድሱ ኪዳን ሃይማኖቷ መኾኑ የተረጋገጠበት፡ ድል ነው!
Blogger Comment
Facebook Comment