VIDEO
ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
የ COVID-19 ክትባት እስከ ዓመቱ መጨረሻ ዝግጁ ሊሆን እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት ሃላፊ ዛሬ ገልፀዋል ፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሓኖም ገብረየሱስ በተፈጠረው ወረርሽኝ ላይ ለሁለት ቀናት የስራ አስፈፃሚ ቦርድ ስብሰባ ማጠናቀቂያ ላይ እንደተናገሩት “ክትባቶች ያስፈልጉናል እናም እስከዚህ አመት መጨረሻ ክትባት ሊኖረን ይችላል የሚል ተስፋ አለ” ብለዋል፡፡
ዘጠኝ የሙከራ ክትባቶች እ.ኤ.አ. በ 2021 መጨረሻ 2 ቢሊዮን ክትባቶችን ለማሰራጨት ያለመ በአለም አቀፉ የዓለም የጤና ክትባት ተቋም በአለም አቀፍ ክትባት ተቋም ውስጥ ይገኛሉ ፡፡
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሓኖምን የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር እንዲሆኑ ሲመኙ ከነበሩት ግለሰቦች መካከል ቢል ጌትስ አንዱ ነው። ሰሞኑን እየተካሄደ ካለው የፀረ-ቴዎድሮስ ዘመቻ ጀርባ የተለመደው ድራማ ነው የሚታየው። ኢ-አማንያኑ አሜሪካና ቻይና አብረው ነው የሚሠሩት፤ የኮሮና ቫይረስን ያመረቱት ሁለቱም በህብረት ነው፤ አሁን ወረርሽኙ ያስከተለውን ከፍተኛ ዕልቂትና የማህበረሰባዊ-ምጣኔ ኃብታዊ ቀውስ ከራሳቸው ዘወር ለማድረግ በ ዶ/ር ቴዎድሮስ ላይ የሌባ ጣታቸውን ይጠቁማሉ። ጉዳዩ ከግለሰብ ቴዎድሮስ ጋር ሳይሆን ከኢትዮጵያ ጋር ነው። ጅራፍ እራሱ ገርፉ እራሱ ይጮኽና ውሻውን መጥፎ ስም ሰጥቶ ይደፋዋል። “በጣም ጥሩው መከላከያ ጥሩ አጥቂነት ነው” የሚለውን ስልት ይጠቀሙ የለ።
“ዓለም ዛሬ 6.8 ቢሊዮን ሰዎች አሏት፡፡ ያ ወደ ዘጠኝ ቢሊዮን ያህል እየመራ ነው ፡፡ አሁን በአዳዲስ ክትባቶች ፣ የጤና እንክብካቤ እና የመራቢያ ጤና አገልግሎቶች ላይ ትልቅ ስራ የምንሰራ ከሆነ ምናልባት ምናልባት ቁጥሩን በ10 ወይም በ 15 በመቶ ዝቅ ማድረግ እንችላለን፡፡”-ቢል ጌትስ
"The world today has 6.8 billion people. That's heading up to about nine billion. Now if we do a really great job on new vaccines, health care & reproductive health services, we could LOWER that by perhaps 10 or 15 percent." -Bill Gates
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሓኖምን ገና ሲመረጧቸው፤ “ያለ ምክኒያት አለመረጧቸውም!” ብየ ነበር። ኢትዮጵያን ለዚህ ዘመን በደንብ አዘጋጅተዋታል። አውሬው ሕዝቦቿን በነገድ ከከፋፈለ በኋላ በአውሬው መታወቂያና ፓስፖርት ላይ የነገድ ስም ብሎም የየትኛው እምነት ተከታይ እንደሆነ ቁልጭ ብሎ እንዲቀመጥ አድርጓል። ይህ ደግሞ በቀበሌ ሥርዓት የተዋቀሩትን የኢትዮጵያ ከተሞችና መንደሮች ዲያብሎሳዊ ሥራቸውን ለመስራት ትልቅ እድል ሰጥቷቸዋል። ለእነ ግራኝ ዐቢይ አሕመድና ታከለ ኡማ የየትኛውን ነገድ/ብሔር ነዋሪዎች መከተብ፣ መመረዝና መግደል እንደሚችሉ በጣም አመቺ የሆነ ሁኔታ ፈጥሮላቸዋል።
የተማረው ያልተማረው ወገን ገዳዮቹን “መሪዎቹን” በማወደስ እድሜውን ሲገፋና በማይረቡ ነገሮች እርስበርስ እየተነታረክ ጊዜውን በከንቱ ሲያጠፋ፤ ገዳዮቹ “ልሂቃን” ግን እርሱንና ዘሩን ለማጥፋት ሌት ተቀን ተግተው በመስራት ላይ ናቸው። የአውሬ ምሣ የሆነው ሰጎን በድንጋጤ አንገቱን አሸዋ ውስጥ ይቀብራል፤ የዘመኑ ትውልድ ግን በግድየለሽነት አንገቱን አሸዋ ውስጥ ለመቅበር የሚፈልግ ይመስላል።
“ወደ አገራችን በረቀቀ መልክና በድብቅ የገባው ይህ የፀረ–ህይወት እንቅስቃሴ ከ1970ዎቹ ዓመታት ጀምሮ በትጋት እየሠራ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ከኢትዮጵያ ሌላ፡ ይህ የቤተሰብ አጥፊ ፕላን በጥቁር አፍሪቃውያን ላይ ብቻ ነው እየተካሄደ ያለው። ከሦስት ወራት በፊት ለንደን ከተማ ውስጥ ይህን አስመልክቶ እነ ቢል ጌትስ አዘጋጅተውት በነበረው ስብሰባ ላይ ተገኝተው የነበሩት ከሳሃራ በረሃ በታች የሚገኙት አፍሪቃ አገሮች ሲሆኑ፤ የሰሜን አፍሪቃና ዓረብ አገሮች ጭራሹን አልተሳተፉም።85 ሚሊየን ሕዝብ የሚኖሩባት በረሃማዋ ግብጽ የሕዝብ ቁጥርሽን ቀንሽ የሚል ሃሳብ ቀርቦላት አይታወቅም፡ እንዲያውም ምዕራባውያኑ የእርዳታ ገንዘቡን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በደስታ ይሰጧታል፤ የኢትዮጵያንም ውሃና አፈር በነፃ ታገኛለች፡ ጦረኛ የሆኑ ልጆችን መፈልፈሏንም ያለምንም ተቃውሞ ትቀጥልበታለች። ከ 1ቢሊየን በላይ የሕዝብ ቁጥር ያላት ህንድ እንደ ዶፖ ፕሮቬራ የመሳሰሉትን የወሊድ መከላከያ መርፌዎች ከልክላለች (እ.አ.አ በ 2002 ዓ.ም)
አዎ! የዲያብሎስ ሠራዊት ኢትዮጵያውያንን በረሃብ፣ በበሽታና በእርስ በርስ ጦርነቶች እንዳሰበው/እንዳቀደው ለማጥፋት አልተቻለውም፤ ታዲያ አውሬው አሁን ውስጥ ሠርጎ በመግባት መርፌንና፤ (“መድኃኒት” አልለውም)መርዛማ‘ቅመሞችን‘በነፃ በማደል መጠራጠር የተሳነውን ወገናችንን ወደ ወጥመዱ ለማስገባት እየሞከረ ነው።
ወገን፤ እህቶቻችን፣ እናቶቻችን፣ ጓደኞቻችንና ሚስቶቻችን እንደ ዓይጥ ተቆጥረው የህክምና ሙከራ ሲደረግባቸው እያየን እንዴት ዝም እንላለን? ይህን ይህን መሰሉን አስከፊ ሥራ ለማጋለጥ ካልተነሳሳን ከእንስሳ በምን ነው የምንሻለው?
የሚከተሉትን መረጃዎች ለሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ በሚያስቆጣ መልክ የማስተላለፉ ተግባር የያንዳንዳችን ብሔራዊና ሰብዓዊ ግዴታ መሆን ይኖርበታል።
Blogger Comment
Facebook Comment