የመሬት መንቀጥቀጡ በዮሐንስ ራዕይ ላይ በተጠቀሱት ሰባቱ የእስያ አብያተ ክርስቲያናት | ድንቅ ነው!



✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

በቱርክ እና ግሪክ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀ ልክ በዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ ውስጥ በተጠቀሱት የ፯/ 7ቱ አብያተ ክርስቲያናት አካባቢ መሆኑ እጅግ በጣም የሚያስገርና ብዙ ነገር የሚናገር ነው። በግርኳ ፍጥሞ (Patmos) ደሴት ነበር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የራዕይን መጽሐፍ የፃፈው። በቱርክ ደግሞ በመንቀጥቀጡ ክፉኛ የተመታቸው ክፉኛ የተመታችው ስሚረነስ (Smyrna) ፯ቱ አብያተክርስቲያናት ከሚገኙባት ቦታዎች አንዷ ናት። ዛሬ ኢዝሚር ትባላለች። የክርስቶስ ተቃዋሚውና የሀሰተኛው ነብይ መሐመድ የልደት ቀን በሚከበርበት (መውሊድ) ዕለት መከሰቱ ደግሞ ያለምክኒያት አይደለም። ዋ! ዋ! ዋ!

[የዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ ፩፥፱]

"እኔ ወንድማችሁ የሆንሁ ከእናንተም ጋር አብሬ መከራውንና መንግሥቱን የኢየሱስ ክርስቶስንም ትዕግሥት የምካፈል ዮሐንስ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ምስክር ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ።"

ከሦስት ሳምንታት በፊት አውሎ ንፋስ "ኢዝሚር" ብለው የሰየሟትን የመጽሐፍ ቅዱሷን ሰምርኔስ ከተማ ነው አጠቃት።

ስምርኔስን ኢዝሚር፣ ናዝሬትን አዳማ...የቦታ መጠሪያ ስሞችን እየቀያየሩ እግዚአብሔር ያልሰጣቸውን ቦታዎች ለሚወሩ ለክርስቶስ ተቃዋሚዎች፤ ዋ! ዋ! ዋ!

በዮሐንስ ራዕይ ላይ የተጠቀሱት ሰባቱ የእስያ አብያተ ክርስቲያናት ያለምክኒያት አይደለም ዛሬ "ቱርክ" በተባለቸው የክርስቶስ ተቃዋሚ ሃገር እንዲገኙ የተደረገው። ድንቅ ነው!

የቦታዎቹን ስም ልክ ናዝሬትን – አዳማ ፣ ደብረዘይትን – ቢሾፍቱ ብለው እንደሰየሙት እንደ እኛዎቹ የቱርክ ወኪሎች ወራሪዎቹ ቱርኮችም እግዚአብሔር የሰየማቸውን ቦታዎች እንደተለመድው እንዲህ በማለት ቀይረዋቸዋል፦

፩. ኤፌሶን – ሰልጁክ

፪. ሰምርኔስ – ኢዝሚር

፫. ጴርጋሞን – ቤርጋማ

፬. ትያጥሮን – አኪሳር

፭. ሰርዴስ – ሳርት

፮. ፊልድልፍያ – አላሸሂር

፯. ሎዶቅያ – ዴንዝሊ

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment