የሉሲፈርን ኮከብ ሰጥተውን የሚያባሉን አሜሪካኖች በዚሁ ኮከብ እራሳቸው መባላት ጀምረዋል!


✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

የሚገርም ነው! በፍሎሪዳዋ 'ቦካ ራቶን' (በስፓኒኛ 'የዓይጥ አፍ') በተሰኘችው ከተማ የጌታችንን የልደት በዓል መቃረብ ተከትሎ ሰይጣን አምላኪዎች እንደ ዋቄዮ-አላህ እሬቻ አምላኪዎች ክርስቲያኖችን ለመፈታተን የባፎሜት ምስል ያረፈበት ባለ አምስት-ማዕዘኑን ኮከብ (ፔንታግራም) በከተማዋ አደባባይ ላይ አቆሙ። ይህን ለመቃወም ብዛት ያላቸው ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን፣ መስቀሉን እና ጸበል በመያዝ ወደዚህ ሰንደቃችንን ወዳቆሸሸው ኮከብ አመሩ።

በይበልጥ የሚገርመው ደግሞ፤ ክርስቲያን አሜሪካውያን ቅዱስ መጽሐፉን፣ ክቡር መስቀሉን እና ጸበሉን ይዘው "ሰይጣን ሂድ ከከተማችን ጥፋ!" እያሉ ሰይጣን አምላኪዎችን ፊት ለፊት ይጋፈጣሉ፤ እኛ ኢትዮጵያውያን ግን በተቃራኒው ይህን የሉሲፈር ኮከብ ሰንደቃችን ላይ ለጥፈን ሰይጣናዊውን ኢሬቻን በከተሞቻችን ሲያከብሩ የመጡን ሰይጣን አምላኪዎችን ጸጥ እንላቸዋለን። አሜሪካውያን የእኛን ወርቅ ወስደው ድንጋያቸውን ለእኛ ይሰጡናል!

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፥፴፪፡፴፫]

"ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።"

#ኢትዮጵያ_አውታር
#ሰላቢ_እጆች
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment