እስኪ ሁለቱን ሃገራት እናነጻጽራቸው፤
አሜሪካ፤ ዓርብ ሐምሌ ፴፩ /24 – ፪ሺ፲፪ / 2012 ዓ.ም
አመጸኞች በፖርትላንድ፡ ኦሬገን መጽሐፍ ቅዱስን + የአሜሪካን ባንዲራ አቃጠሉ
በአሜሪካ የተከሰተው ድርጊት ከጥቂት ዓመታት በፊት በኢራን ወይም በፍልስጤም ነበር ሊከሰት የሚችለው፤ ለዛውም በበነገታው የአሜሪካ የበቀል ሮኬቶች ኢራኖችን ወይም አረቦችን ዱቄት ለማድረግ ተምዘግዘገው ይላኩ ነበር።
ኢትዮጵያ፤ እሑድ ሐምሌ ፳፮ /26 – ፪ሺ፲፪ ዓ.ም
ፖሊሶች ስንደቃችንን ቀድደው ጣሉ፤ ኢትዮጵያ ብሔርተኞችን ደበደቧቸው፣ አሠሯቸው
በኢትዮጵያ ሃገራችን ደግሞ ታሪካዊውን ሰንደቃችንን እያዋረዱ፣ የያዟቸውውን ኢትዮጵያውያንን የሚደበድቡትና የሚያሥሩት ኢትዮጵያን "እንጠብቃለን" የሚሉት የሠራዊቱ ክፍሎች ናቸው። ረሳነው እንዴ ባለፈው ጊዜ እኮ ፖሊሶች እና ወታደሮች ነበር ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ዘው ብለው በመግባት ሰንደቃችንን ከሕንፃው ላይ ሲያወርዱ የነበሩት።
አዎ! ተሳላቂው ዐቢይማ በግልጽ ደጋግሞ ነግሮናል፦
"'በሬ ሆይ! ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ' በማለት የተረትኩበት ይሄ ሞኝ ሕዝብ እኮ አገሩንና ሰንደቁን በደንብ ይወዳል፤ ስለዚህ እኛ ኦሮሞዎች 'ኢትዮጵያ አትፈርስም' እያለን በማስፈራራት አርፎ ቁጭ እንዲልና የሚወደውንም ነገር ሁሉ አንድ ባንድ በድፍረት እየነጠቅነው ሃገሪቱን ቀስበቀስ እናፈራርሳታለን፤ ኦሮሞ እስኪነቃ ነው እንጂ፣ እስኪነሳ ነው እንጂ ሲነሳ ሚዳቋ አትበላንም፤ እኛ ዝሆን ነን፤ እንሰብራለን፤ እንበላለን፤ እንገዛለን።" ሃሳብ አለን፤ ድርጅት አለን፤ ከአለም ጋር ግንኙነት አለን፤ ህዝባችን በስራ ያውቀናል፤ እኛም ህዝባችንን እናውቃለን፤ ሽማግሌዎቻችንን እናውቃለን፤ ተያይዘን መላውን አፍሪካን ለመለወጥ፣ ይሄ ዘመን የእኛ ስለሆነ፣ ይህን ዘመን የሰጠን እግዝያብሄር በመሆኑ አሳልፈን ሰጥተን ዳግም ወደ ባርነት ለመመለስ አንፈልግም፤ ያ ደግሞ ተመልሶ አይመጣም። እጃችሁ የገባውን ነገር ጠብቁ፤ ቆጥቡ፤ አጠንክሩ፤ ጉድለት(ስህተት) ካለ ምከሩ። ያለበለዚያ ይህን ከጅ ካወጣን አጥር ውስጥ ተቀምጠው እንደሚያለቅሱት ዓይነት ለቅሶ ስለሚሆን፣ ከዚህ በኋላ ለኦሮሞ ለቅሶ የማይሆንለት ስለሆነ፣ ያገኘነውን ይዘን፣ የቀረውን ሞልተን፣ ወደ ፊት መሄድ እንድንችል”
ወገኖቼ፤ ይህ ጽንፈኛ ተግባር እኮ ከአመጸኞቹ ኮሙኒስቶች፣ ፋሺስቶችና ናዚዎች ሌላ በየተኛውም ሃገር ታይቶና ተደርጎ የማይታወቅ ተግባር ነው። የሃገርን ሰንደቅ ይህን ያህል ማዋረድ?!
ታዲያ ግራኝ ዐቢይ አሕመድ ዓሊ፣ ታከለ ዑማና መንጋዎቻቸው ወዲያው መረሸን የሚገባቸው ቀንደኛ የኢትዮጵያ ጠላቶችና ከሃዲ ወንጀለኞች አይደሉምን?!
አዎ! አባታችን አባ ዘ-ወንጌል በአንድ ወቅት እንዲህ ብለውን ነበር፦ "ኢትዮጵያን በዚህ ወቅት እያስተዳደሯት ያሉት ጠላቶቿ ናቸው!"
Blogger Comment
Facebook Comment