አሁንስ እነ አሳምነውን፣ ሽመኘውን ምናልባትም ተማሪዎቹን የገደሏቸው ዐቢይና ሽመልስ መሆናቸው ተረጋገጠላችሁ?

Opinion - The Lemma Megerssa Moment and the Oromo Dilemma: Between ...

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

ዘፋኝ ሃጫሉንም ያስገደሉት ዐቢይ አመድ፣ ሽመልስ አብዲሳ፣ ጀዋር መመድ እና ለማ መገርሳ ናቸው። 100%

ሽመልስ አብዲሳ፣ ለማ መገርሳ፣ ጀዋር መ ሐመድ፣ በቀለ ገርባ የተናገሯቸው ነገሮች ዐቢይ አህመድ ከተናገራቸው በምን ይለያሉበምንምሁሉም አንድ ናቸውናእስኪ መልስ ብለን ግራኝ ዐቢይ አመድ በወሎ፣ በስልጤ፣ በሐረር፣ በባሌና በካይሮ የተናገራቸውን ጽንፈኛ ንግግሮች በድጋሚ እናዳምጣቸው፤ በጽንፈኝነታቸው ከእነ ሽመልስ ቢከፉ እንጅ አያንሱም።

የልዑል እግዚአብሔር መልአክ ቁራውን አብዲሳን(ሺቁራው አብዲሳ)ያስለፈለፈው እኮ መንፈሳዊ ዓይኑ የታወረበት፣ ጆሮው የተደፈነበት ወገን ዓይቶና ሰምቶ ይነቃ ዘንድ ነው። በጣም የሚያሳዝን ነው፤ ምንም ዘመናዊ ትምህርት ወይም የዶክትሬት ማዕረግ የሌላቸው ቆሎ እየቆረጠሙ የሚኖሩ እናቶችና አባቶች እኮ ገና ከመጅመሪያው ለዐቢይ አመድ ሊ የሥልጣኑ ዙፋን ሲያስረክቡት "ግራኝ ተመልሶ መጣብን!” በማለት ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ነበር። ይህ መመጻደቅ አይደለም፤ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁንና እኅተ ማርያም እና እኔም ከሌሎች ጥቂት ወገኖች ጋር ያው ከመጀመሪያው ሰዓት አንስተን ለአንዲትም ደቂቃ ያህል ለዚህ አውሬ ሰው እጃችንን ሳንሰጥና፤ እንደ አብዛኛው ግብዝ ወገን ከነፍሳችን ቆርሰን በመሸጥ ወለም-ዘለም እያልን ሳንጓዝ እስከ ዛሬው ዕለት ድረስ ለመዝለቅ በቅተናል። በሌላ በኩል ግን አውቀናል፣ መረጃ እናገኛለን፣ መገናኛ ብዙሃንንም ይዘናል፣ "ከኛ ሌላ ዋ!" የሚሉት ወገኖች፤ የተመረጡት ሳይቀሩ ስጋዊ የዲቃላ ማንነትና ምንነት እንዳላቸው ግለሰቦች ሆነው መርህ እና አቋም በሌለው እርካሽና ኋላ-ቀር አካሄድ፣ ዛሬ ደጋፊ፣ ነገ ተጠራጣሪ፣ ከነገ ወዲያ ተቃዋሚ ናቸው፤ በዚህም እውንተን ይዘው ቀጥተኛውን መንገድ በመምረጥ ፈንታ እንደ እባብ ጠመዝማዛውን መስመር ተከትለው በመሄድ ሲሰነካከሉ ለማየት በቅተናል። ዛሬም እንኳን "ምናልባት ዐቢይ ባይሳካለት በሚል መደናገጥ ሌላውን መመዳዊ አታላይ አጋሩን የሶማሌውን ሙስጠፌን ከፍ ከፍ በማድረግ ላይ ናቸው። "ዋናው ቁምነገር ስልጣን ከእጃችን መውጣት የለበትም፤ ተዋሕዶ የሆነ የሰሜን ሰው አይምጣብን እንጅ ካስፈለገም ኢትዮጵያ ትፍረስ..." በሚል ዲያብሎሳዊ ምኞት ተጠምደው። ለማ እና ተዋሕዶ እና ዐቢይ ትግሬ ባለመሆናቸው ነበር "ዋውቲም ለማ፣ ሙሴያችን ቅብርጥሴእያሉ ሲሰግዱላቸው የነበሩት። እነዚህ ሰነፎች በዚህም ጭፍን እና ደካም አካሄዳቸው ብዙዎችን አሳስተዋል፤ ዛሬም በማደናገርና በማሳሳት ላይ ናቸውና በኢትዮጵያ እየተካሄደ ላለው ግልጽ የሃገር ማጥፋት ዘመቻ አብረው ተጠያቂዎች ይሆናሉ ማለት ነው።

ላለፉ ዓመታት ለተፈፀመው የዘር እልቂት ተጠያቂዎቹ ዐቢይ አመድ፣ ለማ መገርሳ፣ ሽመልስ አብዲሳና መንጋዎቻቸው ናቸው። ከእንግዲህ ወዲህ ለሚገደል አንድ የተዋሕዶ ልጅ ተጠያቂዎቹ ከእነዚህ ወንጀለኞች ጋር የተደመራችሁና ዛሬም ድጋፍ በመስጠት ላይ ያላችሁ ወገኖች ትሆናላችሁ። "ተዋሕዶ ነን የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ነንብላችሁ ከገዳይ ዐቢይ ጎን የቆማችሁ ሁሉ ዐቢይ አመድን እስከ መስከረም ፩ ድረስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አኝካችሁ ለመትፋት ዝግጁነታችሁን በአደባባይ ካላሳያችሁ ከእነ ዐቢይ አመድ ጋር ወደ ሲዖል አብራችሁ እንደምትጠረጉ ከወዲሁ እውቁት። ዝም አንላችሁም!


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment