ሉሲፈር የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ከሰንደቃችን ወደ ቤተ ክርስቲያናችን?


ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

በሰሞነ ፋሲካ ተዘጋጅተው የነበሩትን መንፈሳዊ መርሐ ግብሮች በቀጥታ ሲያስተላልፍ የነበረው ጣቢያ "ባላገሩ" የተባለው "የባህል" ዘፈኖችንና ጭፈራዎችን በማዘጋጀት የሚታወቀው ቡድን እንደሆነ ሳይና ኮከቧም ብልጭ ድርግም ስትል እራሴን በወቅቱ የጠየቅኩት፤ "እንዴ፡ መርሐ ግብሮቹን ለማስተላለፍ ለምንድን ነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን መስኮተ ትዕይንት ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ ያቃተው?" የሚለውን ጥያቄ ነበር።

ይህን ክስተት ምናልባት ሌላ ወገን ታዝቦት ይሆናል በሚል ለአንድ ወር ያህል ጠብቂያለሁ፤ እስካሁን ያየሁትና የሰማሁት ነገር የለም፤ ሁሉም ለታዕታይ ህሊናው የላኩለትን የሉሲፈርን ኮከብ ብልጭታ ዓይቶትና ተቀብሎት ጸጥ ብሏል።

የህወሓት/ኢሕአዴግ መንግስት በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ላይ ያለችውን ስለ ዲያብሎስ የሞትና የባርነት ህግና ስርዓት የምትናገረውን ባለ አምስት ማዕዘን ኮከብ ሲያሳርፍ   ኢትዮጵያውያንን በዛር መንፈስ  አደንዝዞበታል። ይህም ማለት የኢሕአዴግ መንግስት የተመሠረተው በሰይጣናዊ የሞትና ባርነት ህግና ስርዓት ነው ማለት ነው።

ይህችን ኮከብ በእስልምናው አምልኮ መልክና ምሳሌ ውስጥ በመስጊዱ ሚናራ እንዲሁም በእስላም ሀገራት ባንዲራዎችና ገንዘቦች ላይ ከግማሽ ጨረቃዋ ራስ ላይ ሆና የምትታይ ናት። የኮከቧ መልክና ምሳሌ የእስልምናው መንግስት፤ የዘንዶው መንግስት ህግና ስርዓት አርማ ነው። ይህ መልክና ምሳሌ ነው ዛሬ ኢትዮጵያን ጨምሮ መላው ዓለምን የሚገዛው። ይህ ዲያብሎስ የሰውን ልጅ በመልኩና በምሳሌው የፈጠረበት መልክና ምሳሌ ነው።

እስኪ እራሳችንን እንጠይቅ? የሰውን ልጅ ከምድር አፈር በመልኩና በምሳሌው አስቀድሞ የፈጠረውን የእውነተኛውን አምላክ የእግዚአብሔር ህግና ሥርዓት ማለትም መልክና ምሳሌ የሚናገረውን የዳዊት ኮከብ የኢሕአዴግ መንግስት ለምን አልተጠቀመም? አሁን መልሱ ግልጽ የሆነልን መሰለኝ!

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment