የግራኝ አሕመድ አውሬ መንግስት ተቀዳሚ ፍልሚያ ከኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጋር እንደሆነ የሚጠራጠር የተዋሕዶ ልጅ ካለ በጣም አዝናለሁ።
አሁን የአሕዛብ ረመዳን አልቋል፤ ስለዚህ በመጪዎቹ ቀናትና ሳምንታት የጤና ሚንስትሯ ወይዘሮ ኮሮና በቀን አንዴ ብቅ እያለች “በወረርሽኝ ታሟል” የሚባለውን ሰው ቁጥር ከፍ፣ ከፍ በጣም ከፍ እያደረጉ ይመጣሉ። ዋናው ዓላማቸው ለዲያብሎሳዊ ተግባራቸው እንቅፋት የሆነችባቸውን ቤተ ክርስቲያንን እንደገና ማዘጋት ነው።
እንግዲህ ልብ በሉ፤ አደጉ በተባሉት አገራት አሁን የወጣ መረጃ እንደሚጠቁመን፤ “ስዎች በተቀራረቡና በተገናኙ ቁጥር በኮሮና ቫይረስ የመጠቃት ዕድላቸው በጣም ዝቅ ያለ ነው።” ስለዚህ ሰዎች በተቃራኒው አሁን በጣም መቀራረብና መገናኘት አለባቸው!
አዲስ አበባ ልደታ ማርያም (ሜክሲኮ) አካባቢ ችግር መፍጠራቸው ያለ ምክኒያት አይደለም። ላለፈው መስከረም ፬/4 ተጠርቶ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ በዋናነት ያካሄደችው ቅድስት ልደታ ማርያም ቤተክርስቲያን ብቻ ነበረች። የመንፈሳውያኑ ኢትዮጵያውያን ጠላት የሆነው የግራኝ አሕመድ መንግስት ይህን ያውቀዋል፣ ይህን ደግሞ በጣም ይፈራዋል። ስለዚህ አሁንም የእንቅስቃሴ እገዳውን በልደታ ሠፈር ጀምሯል። የሚገርም ነው፤ ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ የሚገኘው የሜክሲኮ ኤምባሲ ለግብረ-ሰዶማውያን የድጋፍ መግለጫ ማውጣቱ ነው። በአጋጣሚ?
እናታችን ቅድስት ማርያም ከሚታየው እና ከሚሰማው ክፉ ነገር ሁሉ ትጠብቀን፣ ረድኤትና በረከቱ፣ ምልጃና ፀሎቷ አይለየን። አሜን! አሜን! አሜን!
Blogger Comment
Facebook Comment