ደስታ ተክለወልድ በአማርኛ መዝገበ ቃላት መድብላቸው ፖለቲካን እንዲህ ይተረጉሙታል፤
“ቦለቲክ (ፖለቲክ) የነገር ዘዴ፤ ውስጠ ተንኮል፤ ፈሊጥ።
በግዕዝ፤ ጉሕሉት፥ ኂጣን ሚን ይባላል። (ላዩ ዳባ፤ ውስጡ ደባ)
ድለላ፥ ሽንገላ ማለት ነው፥” ይላሉ።
ቦለቲከኛ ለሚለው ቃል የሰጡት ትርጉም ደግሞ፥ “ዘዴኛ፥ ባለፈሊጥ፥ አዋቂ፥ በነገር ተራቃቂ፥” ብለው ተርጉመውታል።
የግዕዙን ቃል፥ “ጉሕሊ” የሚለውን ከነእርባታው ስንመለከት ሊቁ ደስታ ተክለ ወልድ ፖለቲካን የሚመለከቱት፥ “ጉሕሊት”
በሚለው ቃል አኳያ መሆኑን እንረዳለን።
“ጉሕሊ፦ ክፉ አድራጊ፤ ሌባ፥ ቀጣፊ፤
ጉሕሉት፦ ማታለል፥ ልብለባ፥ ክዳት፥ ተንኰል፥ ሰይጣናዊ ባሕል።1
ጉሕሉት፦ ማታለል፥ ልብለባ፥ ክዳት፥ ተንኰል፥ ሰይጣናዊ ባሕል።1
ከዚህ ላይ የምንገነዘበው በሊቁ ደስታ ተክለወልድና በርሳቸው ትውልድ ዘመን ሊቃውንት ፖለቲካን እንደ ሰይጣናዊ ግብር አድርገው ይመለከቱት እንደነበር ነው። ይህ ደግሞ ታላቅ እውነት ሆኖ በዘመናችን ይታያል።
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶችም የምዕራባውያን የጥፋት አጀንዳ ለማስፈጸም ሌተቀን እንቅልፍ አጥተው በደጋፊና ተቀዋሚ ጎራ ለይተው እየሰሩ ነው። የፖለቲካ ድርጅቶቹ ከሚከተሉት ርዕዩተ ዓለም ጀምሮ እስከ ገንዘብ ድጋፍና መሰረት የያዙት በምዕራባውያን ድጋፍ ነው፦
“ህወሓት” በ ብሪታኒያ
“ኦነግ” በ ጀርመን
“አብን” በ አሜሪካ
“ኢዜማ” በ ስዊድን? እርዳት ነው የተመሠረቱት! የሉሲፈራውያኑ ምዕራባውያን መሣሪያዎች እና “Useful Idiots / ጠቃሚ ጅሎች” ናቸው።
“ኦነግ” በ ጀርመን
“አብን” በ አሜሪካ
“ኢዜማ” በ ስዊድን? እርዳት ነው የተመሠረቱት! የሉሲፈራውያኑ ምዕራባውያን መሣሪያዎች እና “Useful Idiots / ጠቃሚ ጅሎች” ናቸው።
Blogger Comment
Facebook Comment