ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ዓለም ለስጋዋ በጣም ተጨንቃለች፤ ኤስያ፣ አውሮፓ እና አሜሪካ ቤተክርስቲያኖቻቸውን ዘግተዋል፣ በቫቲካን ከተማ የሮማው ካቶሊክ ጳጳስ ሰው-አልባ በሆነው አደባባይ ብቻቸውን ሲቀድሱ ነበር፣ የአሕዛቡም ጣዖት የመካው ጥቁሩ ድንጋይም ብቻውን ቀርቷል።
ወገናችን ግን እንዲህ ተሰባስቦ ለመላው ዓለም ጸሎት እንዲያደርስ እግዚአብሔር አምላኩ ፀጋውን ሰጥቶታል። ዲያብሎስ በዚህ ቅጥል ይላል፤ ገና ብዙ ይተናኮለናል፣ ሊያስፈራራን እና ሊያሸብረን ይሻል።
እግዚአብሔር ልጆች የወንድሞቻቸው ደም በፈሰሰበት ቦታ ላይ ለአምላካቸው እጆቻቸውን የሚያደርሱበትን ቤተ መቅደስ ይገነባሉ፤ የዲያብሎስ ልጆች ደግሞ ለዲያብሎስ የደም ግብር ባቀረቡበት ቦታ ላይ የአውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት ያቅዳሉ።
ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጥያራ በተከሰከሰበት በደብረዘይት ከተማና ዝቋላ ገዳማት አቅራቢያ በሚገኝ ሰፊ ቦታ ላይ በአፍሪቃ አንጋፋ የሆነ አውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት ዕቅድ መኖሩን በቅርብ ልንከታተለው ይገባናል። ከዚህ ቀደም በዋልድባ ገዳማት ዙሪያ ፋብሪካዎችን ለመገንባትና አህዛብን ወደዚያ ለማስፈር ተሞክሮ እንደነበረው እዚህም ተመሳሳይ ዲያብሎሳዊ ዕቅድ እንዳለ የተዋሕዶ ልጆች ካሁኑ መገንዘብ ይኖርባቸዋል። ዋልድባን በስኳር ፋብሪካ፣ የጣና ሐይቅ ገዳማትን በእንቦጭ፣ የዝቋላ ገዳማትን ደግሞ በአውሮፕላን። ጋኔኑ ግራኝ አህመድ “ፓርክ” በሚል ሰበብ የግቢ ገብርኤልን በኦዳ ዛፍ እንዲከበብ ካደረገ በኋላ አሁን በእንጦጦ ዓብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ላይ ዓይኑን ጥሏል...
Blogger Comment
Facebook Comment