ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጽያ
[ወደ ገላትያ ሰዎች ምዕራፍ ፭፥፩]
“በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።”
“ተራማጆች ሆነናል ሰልጥነናል ፥ ዓለም ደስ ይበልሽ፤ ከግማሽ በላይ የኢትዮጵያ ባለ ሥልጣናት ሴቶች ናቸው ፥ ሂ! ሃ!!" አሉን ሲኒኮቹና ግብዞቹ ባለጊዜዎቹ። እነዚህ አላጋጮች፣ ጨካኝ የዲያብሎስ የግብር ልጆች ለመሆኑ አባትና እናት አሏቸውን? ሴት ልጆችስ ይኖሯቸው ይሆንን? ምን ዓይነት ጉደኞች ቢሆኑ ነው?ሴቶቹም ወንዶቹም ምን ያህል ቀዝቃዛ-ደም ያላቸው አረመኔዎች እንደሆኑ እያየን ነው? እግዚአብሔር የሰጣቸውን ነፃነት በመንፈግ ህፃናትንና ሴቶችን የሚያግቱትን፣ ዘር እየቆጠሩ ከክልሌ ውጡ እያሉ ንጹሃንን የሚያፈናቅሉትንና የሚገድሉትን፣ የክርስቶስን ልጆች በባርነት ለመግዛት የሚሹትን፣ ቤተ ክርስቲያንን የሚያወድሙ ጨካኖች ናቸው።
[ኦሪት ዘኍልቍ ምዕራፍ ፲፬፥፲፯፤፲፰]
“አሁንም፥ እባክህ። እግዚአብሔር ታጋሽና ምሕረቱ የበዛ፥ አበሳንና መተላለፍን ይቅር የሚል፥ ኃጢአተኞችንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን ኃጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ በልጆች ላይ የሚያመጣ ነው ብለህ እንደ ተናገርህ፥ የጌታ ኃይል ታላቅ ይሁን።”
Blogger Comment
Facebook Comment