ኢትዮጵያ ላይ ያሴረ ጊዜው ይረዝም እንደሆነ እንጂ የእጁ ማግኝቱ አይቀርም።
በፈረንሳይ መንግስት እርዳታ እየታደሰ የነበረውን የላሊበላ ውቅር ቤተክርስቲያንን ለመገምገም ባለፈው መስከረም ኢትዮጵያ የመጡትና ከጠ/ሚ አብይ አህመድ ጋር ውይይት ያረጉት የፈረንሳይ የባህል ሚኒስትር ፍራንክ ራይስተር በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተነግሯል።
የፈረንሳይ የጤና ሚኒስትር ኦሊቨር ቬራን ቢ ኤፍ ኤም ቴሌቭዥን ላይ ቀርበው እንደተናገሩት ”ሬይሰተር አሁን እቤቱ አረፍ ብሏል። ደህና ነው።” በማለት ሚኒስትሩ እቤታቸው ሆነው ህክምና እያገኙ መሆናቸውን ገልፀዋል።
የ46 አመቱ ሬይስተር በቅርቡ በኮሮና ቫይረስ ከተጠቁት አምስት የፈረንሳይ የፓርላማ አባላት ከአንዱ ጋር በመገናኘታቸው ቫይረሱ ሊይዛቸው እንደቻለም ተነግሯል ራይስተር በዛሬው እለት ከፊልም ኢንደስትሪ ሰዎች ጋር እና ከአርቲስቶች ጋር በኮሮና ቫይረስ መከላከል ዙርያ ዉይይት ለማድረግ ቀጠሮ ይዘው ነበር። በፈረንሳይ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት 25 ሰዎች ሲሞቱ 1,412 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ኢትዮጵያ ወደሀገሩ አሜሪካ እንደተመለሰ የተነገረለት አንድ የአሜሪካ የባሕር ኃይል ወታደር በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተገልጧል ለጊዜው ወታደሩ ከኢትዮጵያ መቼ እንደተመለሰ የሰጠው ፍንጭ የለም የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር እንዲሁም የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን የሰጡት መረጃ የለም።
Blogger Comment
Facebook Comment