[አሳዛኝ ሰበር ዜና] በደንቢዶሎ ታግተው ነበር የተባሉት ሴት ተማሪዎች መደፈራቸውን ወላጆቻቸው ተናገሩ

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ገና ያልተወራልትና ያልተሰማ ብዙ ጉድ እንደሚኖር አንጠራጠረ። ሰዉ በሀገሩ እንዴት ይህን ያህል ይሰቃያል? እስክ መቼ ነው ኢትዮጵያ የዲያብሎስ መፈንጫ የምትሆነው? ይሄን እርኩስ መንፈስንና መጥፎ ዕድልን ይዞ የመጣውን የወሮበሎች ስብስብ መንግስት በእሳት ሊጠርግ የሚችል አንድ ቆፍጣና አርበኛ እንኳ ይጥፋ? ቤተክሕነትስ ባለፈው ሳምትን መግለጫዋ ላይ ወጣት ሴት ምዕመናኗ እንዲህ እልም ብለው ሲጠፉ ጉዳዩን አስመልክቶ አንድም ቃል ትንፍሽ ያላሉበት ምክኒያት ምንድን ነው? የኢትዮጵያን ስም ለማጠለሸትና ኢትዮጵያውያን በጭካኔ ከዓረቦች እንደማይተናነሱ ለማሳየት ሲባል በተዘጋጀው በዚህ ዲያብሎሳዊ አጀንዳ ላይ እንዴት ሁሉም አካል ተባባሪ ሊሆን ቻለ? እንደው ይህ ለቴዲ አፍሮ ኮንሰርት የሚወጣበት ወቅት ነውን? በሀገራችን እየተካሄደ ያለው ነገር ሁሉ እጅግ በጣም አሳዛኝና ደም የሚያፈላ ነው! ይህች እግዚአብሔር የሚያውቃት፣ እኛም የምናውቃት ኢትዮጵያ አይደለችምና እርስታችን ኢትዮጵያን በፍጥነት ከአውሬው መንጋጋ አውጥተን ልናስመልሳት ግድ ነው። እግዚአብሔር ይርዳን!




Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment