ሬክስ ቴለርሰን ሲ.አይ.ኤ ኮትኩቶ ያሳደገውን ግራኝ ዐቢይ አሕመድን በመምረጥ የእስላም መንግስትን በኢትዮጵያ ለማቋቋም እንዲችል ትዕዛዝ ሰጥተውት እንደነበር አሁን እያየነው ነው

የሬክስ ቴለርሰን ምስል ውጤት

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

ዓባይን ለግብጽ ሸልሞ ይጠረግ ይሆን፧

በግራኝ ዐቢይ አሕመድ መንግስት እጅ የታገቱትን፡ ምናልባትም የተገደሉትን እህቶቻችንን እያስታወሰን፦

👉 ከሁለት ዓመታት በፊት፤ ዐብይ ጾም /ሑዳዴ ፪ሺ፲ ዓ።/ም

የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሬክስ ቴለርሰን ሲ.አይ.ኤ ኮትኩቶ ያሳደገውን ግራኝ ዐቢይ አሕመድን በመምረጥ የእስላም መንግስትን በኢትዮጵያ ለማቋቋም እንዲችል ትዕዛዝ ሰጥተውት እንደነበር አሁን እያየነው ነው። በወቅቱ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ይህን በማወቃቸው ነበር በዚሁ ዕለት ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት ማለት ነው። በሌላው ዓለም እንደሚደረገው፣ የህወሓት መንግስት ለምን ሕዝባዊ ምርጫ በጊዜው አልጠራም፧

ከዚህ የሬክስ ቴለርስን ጉብኝት ጥቂት ሳምናታት በፊት ቲለርሰን በቅድሚያ ከግብጹ ፕሬዚደንት አል–ሲሲ ጋር በካይሮ ተገናኝተው ነበር። ከዓባይ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በግራኝ ዐቢይ አሕመድ የሚመራ መፈንቅለ መንግስት በኢትዮጵያ ለማካሄድ የወሰኑበት ስብሰባ ነበር ማለት ነው። በኋላ ላይ ይህ ከሃዲ “ወላሂ፦ ግብጽን አልጎዳም፦” በሚለው መሃላው ይህን አረጋግጦልናል።

👉 እ.አ.አ ማርች ፩፫/፳፩፰ ዓ.ም

ከኢትዮጵያ በተመለሱ በሦስተኛ ቀናቸው የውጭ ጉዳይ ምኒስትር ቴለርሰን ከሥራቸው ተባረሩ፤ እንዲያውም ገና አውሮፕላን ላይ እያሉ ነበር የስንብት ዜናውን እንዲሰሙ የተደረጉት።

👉 ሰኔ ፪ሺ፲፩ / ፳፩፩ ዓ/ም የ “ብልጽግና አፍሪካ” ስልት ምስረታ

የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጆን ቦልተን “አዲሱን የአፍሪካ ስትራቴጂ” አቀረቡ። ይህንም ስልት “ብልጽግና አፍሪካ” የሚል ስያሜ ሰጥተውት ነበር።

ጆን ቦልተን አሜሪካ ለአፍሪካ አዲስ አጋርነት ስልት እንዳዘጋጀች ጠቅሰው የዚህ ስልት ከፊሉ የቻይናና ሩሲያን ተጽዕኖ በተለይ በኢትዮጵያ ላይ መቀነስ ያለመ ነው ብለው ነበር።

ይህን ስልት በሥራ ላይ ለማዋልም ጥንታዊቷን ኢትዮጵያን በቅድሚያ መቆጣጠር አለብን ብለው ስለሚያምኑ ጆን ቦልተን አብዮት አህመድ ኢሃዴግን ፐውዞ ሙሉ በሙሉ ለሉሲፈራውያኑ ታዛዥ የሆነውን የብልጽግና ፓርቲን እንዲመሠረት ትዕዛዝ ሰጡት። ይህን ባደረጉ ማግስት፤ ልክ በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት መስከረም ፩ / ፪ሺ ፲፪ ዓ.ም ከስልጣናቸው እንዲወገዱ ተደረጉ (ልክ እንደ ቴለርሰን)።

👉 ኅዳር ፪ሺ፲፪ ዓ።ም ላይ በአሜሪካ ሲ.አይ.ኤ ግፊት በከሃዲ ቅጥረኛ አባላት የተሞላው የእስላማዊው የብልጽግና ፓርቲ ተመሠረተ።

👉 ትናንትና የካቲት ፲ / ፪ሺ፲፪ ዓ/ም ላይ የቀድሞው የሲአይኤ (CIA) ዲሬክተር የአሁኑ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ አባይን ለግብጽ ለመስጠት ወደ አዲስ አበባ አመሩ።

የእርሳቸውስ ዕጣ ፈንታ ምን ይመስል ይሆን፧

በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ በጎ ያልሆነ ዕቅድ በመያዝ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የሚደፍር ባለስልጣን፡ ስልጣኑን ብዙም ይዞ አይቆይምና፤ ሬክስ ቴለርሰንና ጆን ቦልተንም የድብቁን መንግስታቸውን ተልዕኮ ፈጽመው በተመለሱ ማግስት ባለተጠበቀ መልክ ከውጭ ጉዳይ ምኒስትርነትና ከብሔራዊ ደህነነት አማካሪ ኃላፊነቶቻቸው ተወገዱ።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment