እኅተ ማርያም ሆይ! የትግራይ ህዝብ የሚባል የለም !!



ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

በእኅተ ማርያም በኩል የሚተላለፉ መልዕክቶች ለመቀበልና ለመረዳት ብዙም አይከብደኝም ነበር ። ምክንያቱ ለዓመታት በኢትዮጵያ አውታር ኅዋ ሠሌዳየ ስለጥፋቸው የነበሩ ጉዳዮች ስለነበሩ ነው ። ከሌላ አካል ማረጋገጫ በማግኝቴ በጣም ደስተኛ ነበርኩኝ ። በተለያዮ ኅዋ ሠሌዳዎች በምለጥፋቸው ርዕሶችና ከተለያዮ ሰዎች ጋር በማወራቸው ነገሮች በሰዎች ዘንድ እንደ ዕብድ የምቆጠር ሰው ነበርኩኝ ። እኅተ ማርያም እነዚኽ መልዕክቶች ይፋ ስታረጋቸው ግን በእውነት ላይ እንደቅምኩኝ በይበልጥ አረጋገጥኩኝ ። እንዲሁም የስያሜየ የምጠቀምበት "ዘ-ኢትዮጵያ" የሚል ቃል በመጠቀምዋ ይበልጥ ወደድክዋት ። እኅተ ማርያም ለዘመኑ የምታስፈልግ ቆራጥ ፣ ቀጥተኛና ለእውነት የቆመች እኅት በመሆንዋ አከብራታለው ። ከቅርብ ጊዜያት ጀምሮ በምታስተላልፋቸው መልዕክቶች ግን ቆም ብየ እንዳስብና በትኩረት እውነትን እንድመረምር እያደረጉኝ ነው ።

በተለይ "ዘ ኢሐልቅ ዞቲ ቁጥር - ፫ - ኢ / (ሦስት - ኢ)" በሚል ርዕስ ትላንት የተለቀቀው የተንቀሳቃሽ ምሥል ወድምጽ መልዕክት ብዙ ጥያቄዎች እንድናነሳ ያደርገናል ።  እኅተ ማርያም በመልዕክትዋ  "ቴዎድሮስ የተባለ ንጉሥ አይመጣም" እና "የትግራይ ሕዝብ ትግራይን ለቅቆ መውጣት አለበት!" በማለት ተናግራለች ። ኢትዮጵያ አውታር ለብዙ ዓመታት ስለ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ንጉሥ ቶዎድሮስ ስትገልፅና ስታስተምር ነበር ። የዚኽ ትንቢት መነሻም የርትዕት ተዋሕዶ ጥንታዊ ቅድሳት መጻሕፍት እንጂ ሌላ አይደለም ። እኅተ ማርያም በተንቀሳቃሽ ምሥል ወድምጽ መልዕክቶችዋ የንጉሥ ቴዎድሮስ መምጣት አምነው ከሚገልፁ አባቶች መካከል ባሕታዊ አዳነ የበቁ እንደሆኑ ስትነግረንም ነበር ። ታዲያ አሁን ምን ተገኝ ? አስገራሚው ነገር "ንጉሥ ቴዎድሮስ እኔ ነኝ" የሚል እኅተ ማርያም በበላይነት በምትመራው "የመድኃኔ ዓለምና የቅድስት ድንግል ማርያም ማኅበር" ውስጥ መኖሩ ነው ። መንፈሳዊውም ስጋዊውም ውጊያ ዛሬ በመካሄድ ላይ ነው እኮ፤ አባቶቻችን፣ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ሕፃናቶቻችን ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልክ በየቀኑ እየተገደሉ፤ ዓብያተ ክርስቲያናት እየተቃጠሉ አይደለምን? ከዚህ የባሰው አስከፊው ጦርነትም መምጣቱ አይቀሬ ነው፤ በዚህ አካሄዳችን መምጣትም አለበት ፥ በአሁኑ ሰዓት ሌላ ምንም አማራጭ የለም።

እኅተ ማርያም እዚህ ላይ አልተጠነቀቀችም እላለሁ፤ "ቤተክርስቲያን የመሥሪያው ጊዜ አይደለም" ማለቷ ላይ እኔም እስማማለሁ፤ ነገር ግን አውሬው ከበስተደቡብ ኢትዮጵያን ለመቆራመት በተዘጋጀበት ወቅት ገዳዮችን ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ መውሰድና "በዐምሓራ" እና "ትግራይ" መካከል ግንቡን ማስፋት ተገቢ አይደለም፣ ሌላ በይበልጥ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ አለ፣ ወቅቱ አይደለም እላለሁ ፥ እውነቱን ለመናገር የኢትዮጵያ እንጂ"የትግራይ ሕዝብ" የተባለ ሕዝብ የለም ። አባ ዘ–ወንጌል"ዋ!" በማለት ያስጠነቀቁን ይህን ነበር።

ሕዝቡን አብረው ሲያተራምሱ ለነበሩት ለኦሮሞዎቹ ሙስሊሞች ለግራኝ ዐቢይ አሕመድና ለደመቀ መኮንን ሀሰን ሰው ያሳየውን ዓይነት ፍቅር፡ ትንሽ እንኳን፡ ለአንድ ትግሬ አሳይቶ ቢሆን ኖሮ እዚህ ውጥንቅጥ ውስጥ ባልገባን ነበር ። የሚደበቅ ነገር አይደለም፡ እግዚአብሔር እኮ ሁሉንም በግልጽ ያየዋል፤ ለዚህም ነው፤ "ማንም፤ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?" ያለን ። ዛሬ ሰው ለተዋሕዶ ትግሬ ከሚያሳየው ፍቅር ይልቅ ለኦሮሞ ሙስሊም የሚያሳየው ፍቅር ይበልጣል ። ዛሬ ሰው ለአፄ ዮሐንስ ሳይቀር ጥላቻቸውን በማሳየት ላይ ነው። ሰውን የትኛው መንፈስ እየጠለፈው ይሆን?

የኦሮሞ ሙስሊም የዕልቂት ሠራዊት የአዲስ አበባን ሕዝብና "ዐምሓራ" የተባለውን ኢትዮጵያዊ በቅድሚያ ለመጨፈጨፍ በሰፊው በመዘጋጀት ላይ ነው ። ይህንም በየቀኑ በግልጽ እየሠማን እያየው ነው ። ላለፉት ሁለት ዓመታት እዚህ እዚያ እያሉ ኢትዮጵያዊውን በመፈተን ላይ ናቸው፤ ኦሮሚያ በተባለው ሲዖል፡ ዐምሓራ በተባሉት ኢትዮጵያውያን ላይ ምንጠራ አካሄዱ ፥ ማንም ምንም እንደማያደርጋቸው አዩት፤ ቀስ ብለው ወደ ወሎ ገቡ ጨፈጨፉ ምንም አልሆኑም፣ ወደ ባሕር ዳርና አዲስ አበባ ሄደው አሉ የተባሉትን ኦሮሞ ያልሆኑ የጦር መሪዎችና ባለ ሥልጣናት ገደሏቸው ፥ ምንም አልተደረገም፤ አሁን ወደ ጎንደር ሄደው ሕፃናትና ማረድ ጀምረዋል፤ አዎ! ኦሮሞዎች ናቸው ሰሞኑን ኢትዮጵያውያን ሕፃናትን የገደሏቸው። ለጊዜው "ረጋ" ብለው "ምርጫ" የተባለውን የማጭበርበሪያ ካርድ በመጠባበቅ ላይ ናቸው፤ የኢትዮጵያዊውን ወኔ ቀስበቀስ በመፈታተን ላይ ናቸው። እኅተ ማርያም አላነሳቸውም እንጂ ኦሮሞዎቹ ትግራይን፣ አክሱምንና በአካባቢው ያሉትን ገዳማት በሚሳየሎች (ምናልባት ኑክሌርና ኬሚካል አዘል) ለመጨፈጨፍ በደንብ የተጠና ዕቅድ ነው ያላቸው። ልዩ ሠራዊቱ አሁን የደከመውን "ዐምሓራ" በቀላሉ ማጥፋት እንችላለን የሚል እምነት አላቸው፡(ተዋሕዶን እና አማርኛ ቋንቋን ማጥፋት አለባቸው "ኩሽ" የሚሉትን ሀገር ለመመስረት) የታጠቀውን "ትግሬ" ደግሞ ወደ ህዋ ተላከ ከተባለው ሳተላይት በሚያፈነጥቁት ጨረር መቀቀል(ህዋሓት የቀለቡት አዞ አብዮት አህመድ ልክ ሥልጣኑን ሲጨብጥ በተጠና መልክ" ህወሓት፣ የቀን ጅብ፣ ግብረ–ሰዶም ወዘተ" እያለ ቅስቀሳ ሲካሄድ ሰምተናል፡ አይደል?) ቀጥሎ ከፈረንሳይ የሚያገኟቸውን ሚሳኤሎችንና መርዞችን ለመጠቅለል ከሚያስቡት የወሎ ግዛት ሆነው በሰሜን ኢትዮጵያ ላይ መልቀቅ ። አዞው የቀለቡትን ሞኞች ቆራርጦ ሲበላቸው ዓለም ጸጥ ነው የሚለው ።

እኅተማርያም ወደ "ሐረር፣ አስመራና ሱዳን" እንሄዳለን ማለቷ አስገርሞኛል፤ ምክኒያቱም ጽንፈኛው ግራኝ ዐቢይ አሕመድም በእነዚህ ቦታዎች ላይ ነው እየተንቀሳቀሰ ያለው።

ይቆየን!
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment