የሰይጣን ድርጅትዋ ኅወሓት እና ዋልማርት

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ፡ በሺዎች ለሚቆጠር ዓመታት ፡ መንፈሳዊነት መሠረት ባደረገ ኃይልዋ ፡ ለጠላቶችዋ ሳትንበረከክ ፡ ሥጋዊና መንፈሣዊ ነፃነትዋ ጠብቃ መጥታለች ። ካለፉት ፵፭ ዓመታት በኃላ ግን በምዕራባውያን ሰይጣናዊ ፍልስፍና በሰከሩ በራስዋ ልጆች መንፈሳዊም ሥጋዊም ከፍተኛ ጥፋት ደርሶባታል ። ይህንን ጥፋት ከፈፀሙት ግለሰቦችና ድርጅቶች መካከል ፡ ኀ.ወ.ሓ.ት የተባለ ከሰሜን ኢትዮጵያ መነሻው ያደረገ ሰይጣናዊ ድርጅት ነው ። ይህ ድርጅት ትውልድ በድንቅ ሀገራዊ ፍቅራቸውና መንፈሳዊ ፈርሐ እግዚአብሔር ካላቸው እንደነ አጼ ካሌብ ፣ አጼ ገ/መስቀል እና አጼ ዮሐንስ ከመሳሰሉት አባቶች ካፈራው ሰሜን ኢትዮጵያ መውጣታቸው አስገራሚ ያደርገዋል ። ይኅ ሰይጣናዊ ድርጅት ፡ ላለፉት ፵፭ ዓመታት ፡ ከምዕራባውያን ጋር በመተባበር ፡ በኢትዮጵያ ላይ ፡ ከፍተኛ ግፍና ሰቆቃ የፈፀመ የጥፋት ድርጅት ነው ።

ከሁለት ዓመት በፊት ፡ ስለ 'ሞንሳቶ' የተሰኝ በዘረ-መል ቅየራ ምኅንድስና  ማሻሻል ዘዴ (GMO) : ምግቦችን በማምረት : የሰው ልጆችን የሚመርዝ : የሀገረ አሜሪካ : ሰይጣናዊ ድርጅት :  በዓለም ዓቀፍና በቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ የሚሠራቸው የጥፋት ሥራዎች በ ኢትዮጵያ አውታር ኅዋ ሰሌዳ ረጅም ፅሑፍ አቅርቤ ነበር ። 

በዓለማችን : ከሞንሳቶ በመቀጠል ባዕድ ነገሮች በመቀላቀል በሚያመርታቸው ምግቦች : የሰው ልጆችን በመመረዝ ለዲያብሎስ ግብር የሚያቀርበው ድርጅት : በ1962 እ.አ.አ በሀገረ አሜሪካ : ሳም ዋልቶን ፡ በሚባል ግለሰብ የተመሠረተ 'ዋልሞርት' የተሰኝ ድርጅት ነው ። ይህ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የታሸጉ ምግቦች የሚሸጥባቸው መደብሮች አሉት ። በቅርቡ የተበረበሩት የሰይጣንዋ ድርጅት ኅወሓት ባለሥልጣኖች የመቀመርያ ቴክኖሎጂ መሣሪያዎቻቸው መረጃ ከሚያሣዮት መካከል የዋልማርት ድርጅት በቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ ለመክፈት የተደረገው ድርድር ነው ። ፍካሬ ኢየሱስ መጹሐፍ ስለነዚ ሰዎች እንዲህ ይላል ፦

❝ በዚያን ፡ ጊዜ ፡ ለብዙ ፡ ክብር ፡ የታጩ ፡ በማእረግ ፣ በሹመት ፡ ያደጉ ፡ በከፍተኛ ፡ ደረጃ ፡ ላይ ፡ የሚገኙ ፡ ሁሉ ፡  አደራችዉን ፡ ይዘነጋሉ ፣ ሀገራቸዉን ፡ ይክዳሉ ፣ መሃላቸዉን ፡  ያፈርሳሉ ፣ ከባለሟልነታቸዉ ፡ ይወጣሉ ፣ ከማእረግና ፡ ሹመት ፡ ጎደኞቻቸዉ ፡ ይለያሉ ። ባለስልጣኖች ፡ ከአመፀኞች ፡ ጋር ፡ ይተባበራሉ...ክፉ ፡ ስራቸዉ ፡በተገለፀባቸዉ ፡ ጊዜ ፡ ይፀፀታሉ ። ❞ 

ተከታዮ መረጃ ከጦማሪ ስዮም ተሾመ የመፅሐፈ ገፅ አድራሻ የተወሰደ ነው ። አንብቡት ፦

" አቶ ጌታቸው ረዳ ኃይለኛ ደላላ ነው። የድለላ ስራ የሚሰራው ደግሞ ዝም ብሎ ሳይሆን እንደ ሼህ መሃመድ አል-ሙዲን ላለ ባለሃብት፣ እንደ ሪክ ማቸር ባለቤት ያለ ባለስልጣን፣ እንዲሁም እንደ ዋልማርት (Walmart) ላለ ትልቅ ዓለም-አቀፍ ድርጅት ነው። ዋልማርት የኢትዮጵያን ገበያ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ፍላጎት ነበረው። አቶ ጌታቸው ረዳ ደግሞ የድለላ ስራ ለመስራት ቀብዱ ተቀብሏል። ሆኖም ግን ዋልማርት ወደ ኢትዮጵያ ገበያ እንዲገባ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅደቅ አለበት። ጌቾ ይህን ለማድረግ ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ይህን ተከትሎ ከአንድ ማንነቱ ካልታወቀ ግለሰብ ጋር (ስልኩ ግን ይታወቃል) ጋር ስለ ሁኔታው በቫይበር ያደረገው ቻት እንሆ በረከት ብለናችኋል። ከታች በምስሉ ላይ እንደተገለፀው አቶ ጌታቸው ረዳ ዋልማርት ወደ ኢትዮጵያ ገበያ እንዲገባ አምስት ከፍተኛ የኢኮኖሚ አማካሪዎች መሞት እንዳለባቸው በግልፅ ይናገራል። አሁንም ቢሆን የያዘው ይዞት እንጂ ጌቾ እነ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሓዬ እና ስዩም መስፍን ከመሰሎ ሽማግሌዎች ጋር አብሮ መቆየት አይፈልግም። እንኳን አሁን የዛሬ አምስት አመት ቢሞቱለት ደስታውን አይችለውም። "
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment