ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ትንቢት፡ ወደፊት የሚሆን፡
ወይም የሚከሰት ነገር አስቀድሞ መናገር ማስጠንቀቀ ነው። ትንቢት፡ በቅዱስ መጽሐፍም ሰፊ ክፍል ተሰጥቶት እናነባለን። የትንቢት
አስፈላጊነትም ሰዎችን አስቀድሞ ከጥፋት ለመታደግ፣ መንገድ ለማስተካከል የሚረዳ ነው። በሰው ልጅ ታሪክም እውነትም ሓሰትም ትንቢት
የሚናገሩና የሚገልጹ ሰዎች ታይተዋል። ሓሰተኛ ትንቢት ተናጋሪዎች ወይም ሓሰተኛ ነብያት የትንቢታቸው ምንጭ የሓሰት አባት ዲያብሎስ
ነው። እውነተኛ ትንቢት ተናጋሪዎች ወይም እውነተኛ ነብያት የትንቢታቸው ምንጭ የእውነት አባት ቅዱስ እግዚአብሔር ነው።
ወደ ወቅታዊው የሀገራችን ኢትዮጵያ
ሁኔታ ስንገባ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ በጭንቅ፣ በረብሻ፣ በረሃብ በአጠቃላይ ጥሩ ሊባል በማይችል ሁኔታ ግራ በመጋባት ስሜት ውስጥ እንዳለ
አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የተገነዘበው ይመስለኛል።
ኢትዮጵያ፡ ከውልደትዋ ከ፸፻፲፪ ዓመታት በፊት ጀምሮ መንገዳቸው በእግዚአብሔር መንገድ ያደረጉ፣ ለእግዚአብሔር ታዛዣ የሆኑ አባቶችና እናቶች የነበሩባት፡ አሁንም ያሏት ቅድስት ሀገር ነች። እነዚህ አባቶችና እናቶች ከእግዚአብሔር የሚቀበሉት መልዕክትና ትንቢት ለህዝቡ ሲያስተላሉፉ ኖሯል። ያአሁን ትውልድ ግን በፖለቲከኞች ሴራ የፍጥኝ በመታሰሩና ከእግዚአብሔር እውነት ይልቅ ለዘረኝነት፣ ለጥል፣ ለግድያ ራሱን አሳልፎ በመስጠቱ ከእግዚአብሔር ርቆ የዲያብሎስ ባርያ ሆኗል።
አሁን፡ ካለንበት ግራማጋባትና ጭንቅ ለመውጣት፡ ወደ እግዚአብሔር እውነት በመመለስ ቅዱሳን ገዳማውያን አባቶች ሰለወቅቱ በትንቢት ያስቀመጥልንን እውነት በመመርመር ከሚመጣው ጥፋት ራሳችን እናድን።
ይህ ነው ትንቢቱ፡፡ መጀመሪያ ከሰሜን የመጡ አንበጦች ኢትዮጵያን እንደተምች ይወሯታል፡፡ ወርረውም እስከ አጥንቷ ይግጧታል፡፡ መሣሪያ ከትከሻቸው የማይወርድ እረኞች በሽምብራ ዛፍ ሥር ተቀምጠው ጠማማ ፍርድን ይሰጣሉ፡፡ እህል በሸሃኔ ይሠፈራል፡፡ ቀጣና ይበዛል፡፡ ርሀብና መከራ ይናኛል፡፡ ትልቅ ሰው ይዋረዳል፤ ትንሽ ሰው ይከበራል፡፡ በመጨረሻቸው ግን እነዚያ ጉዶች እንደጢስ በንነው፣ እንደጤዛ ረግፈው ይጠፋሉ፡፡
ቀጥሎ ፊጋ ከብቶች ባዶውን በረት ይወርሳሉ፡፡ ለተወሰነ ጊዜም ባዶ ያገኙትን በረት እውነት መስሏቸው እምቡር እምቡር ይሉበታል፡፡ ዕውቀትና ጥበብ ባለፈበት መንገድ ያላለፉ የለዬላቸው ነፈዞች ናቸው፡፡ መሪያቸው ሃይማኖት የለውም፡፡ አለው ቢባልም ማስመሰያ እንጂ ከአንጀት አይደለም፡፡ ዕድሜው ከሦስት ዓመታት አያልፍም፡፡ የነሱም የመጨረሻ ዕጣ ልክ እንደአንበጣዎቹ ይሆንና ባላሰቡትና ባልጠበቁት ሁኔታ አከርካሪያቸውን ተመትተው ወደ ታሪክ ትቢያነት ይለወጣሉ፡፡ ያንን ጊዜ አንተ ወይም አንቺና እኔ ላናየው ብንችልም የማይቀር ስለመሆኑ ግን የዮዲትና የግራኝ አሕመድ ወይም የመንግሥቱና የመለስ መጻሕፍት
ምሥክሮቼ ናቸው፡፡ ይህ እውነት መሃላ የማያሻው አጠቃላይ እውነት ነው፡፡
በመጨረሻው መጨረሻ እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ከያሉበት ተጠራርተውና ኃይላቸውን አስተባብረው ኢትዮጵያን ይረከባሉ፡፡ በነሱም የኢትዮጵያ የቀድሞ ክብር ይመለሳል፡፡ ያም ጊዜ እጅግ ቀርቧል፡፡ይህን እውነት መናገር ማንንም አይጎዳም፤ ለማንምም የሥጋት መንስኤ ሊሆን አይችልም፡፡ እንዲያውም የምሥራች ነው፡፡ ለወፍ አራሾች ግን መርዶ ነው፡፡ (ባይገርምህ እናትና ልጅም ተገናኝተው ጥጃዋ ከእህትና ወንድሞቿ ጋር የእናቷን ጡት የምትጠባበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ምን ያስቅሃል፧)
እነዚህ የአሁኖቹ ከንቱዎችና ጌቶቻቸው ወያኔዎች ግን ትልቅ ጉዳት ያደርሳሉ፡፡ የነሱን የዓመታት መርዝ ለመንቀል ብዙ ትግልን ይጠይቃል፡፡ ብዙ ሕዝብ መስዋዕት ይሆናል፡፡ የደም ጎርፍ የማናመልጠው ዕዳችን ይሆናል፡፡ “ለኃጥኣን የመጣ ለፃድቃን ይተርፋል” እንዲሉ ነውና ብዙ አሣር ያገኘናል፡፡ መስዋዕቱን ለመቀነስ እንዲቻል (ትንቢትን ማስቀረት ባይቻልም) ወደ ፈጣሪ ተመልሰን በፆምና በጸሎት ብዙ መድከም ይኖርብናል፡፡ ኢትዮጵያ ቃል የተገባላት ምድር ናት፡፡ ጠላቶቿ ቀበርናት ሲሉ አፈሯን አራግፋ የምትነሣ፣ ገደልናት ሲሉ የምትድን ልዩ ሀገር እንደሆነች በተደጋጋሚ አስመስክራለች፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን ብዙ ዕልቂት ቢኖርም ከህመሟ ተፈውሳ በሚተርፏት ጥቂት ዜጎች ልዕልናዋን እንደገና ታስከብራለች፡፡ አራሙቻዎችም ተጠራርገው የጨለማው ንጉሥ ግዛት ወደሆነው ወደ መጡበት መቀመቅ ይወርዳሉ፡፡
ከገዳማዊያን አባቶች የተሠጠ ማስጠንቀቂያ - መጪው ጊዜ ከባድ ነው ትጉና ጸልዩ
በየከተሞች የሚታየው የሰይጣን አምልኮ ኢሬቻን ጨምሮ እምነትም በነፃነታችን ቶሎ አለመምጣት ላይ የበኩሉን ጽላሎት ማሳረፉ አይቀርም፡፡ ከጥግ እስከጥግ የቆሸሸውና በዘረኝነት፣ በሙስናና በድንቁርና የተበከለው ቤተ መንግሥታችን ብቻ አይደለም፡፡ ቤተ ክርስቲያንንና የእምነት ቤቶችን በጥቅሉ ሰይጣን ስለተቆጣጠራቸው እውነተኛ እረኞች የሉንም፡፡ ሰይጣን የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስያንን ጨምሮ የእስክንድርያዋንና የኢትዮጵያዋን ኦርቶዶክስ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ ተቆጣጥሯል፡፡ ልጅ እየወለደ በድብቅና አንዳንዴም ልክ እንደቫቲካኑ የ፲፭ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንድ ሊቀ ጳጳስ (ፖፕ ሮድሪጎ) በማንአለብኝነት በግልጽ የሚያሳድግ ፓትርያርክና ጳጳስ ባለባት ሀገራችን ውስጥ የእግዚአብሔር በረከትና ጥበቃ በቀላሉ ይገኛል ማለት ቀልድ ነው፡፡ በዚህ ዘመን መዳን ከባድ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ግፍና በደል እየተሠራ እያለ አንድም የሃይማኖት አባት በግልጽ ወጥቶ አይቃወምም፤ ቂጡ ላይ ቁስል ያለበት ውሻ እንደልቡ አይጮህም፤ ፈስ ያለበትም ዝላይ አይችልም፡፡ “አባቶቻችን”ም በጠባያቸው ሰይጣናዊነት የተነሣ ፀጋ እግዚአብሔር ጎድሏቸዋልና በጎቻቸውን ተኩላና ቀበሮ ሲቦተራርፍ፣ ሀገርን ማንም ወስላታና ወለፈንዴ ፖለቲከኛ ነኝ ባይ ሲጫወትባት ትንፍሽ አይሉም፡፡ ምክንያቱም በሆነ ነገር አፋቸው ተሸብቧል፡፡ ለነፍሳቸው ያደሩ እንደነ አቡነ ጴጥሮስ ያሉ አባቶች ሞታቸው ሰማዕትነት እንጂ ተራ ዓለማዊ የሥጋ ሞት እንዳልሆነ ስለሚረዱ እውነትን መስክረው በጥይት ተደብድበው ሞተዋል፡፡ አሁን ግን የምዕመናንንና የሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ማሠሪያ ገንዘብ እየዘረፉ፣ በዘረኝነት አሮንቃ እየዳከሩና በሴሰኝነት የወሲብ ንዳድ እየነፈሩ ስለነፍስና ስለሀገር ማሰብ የማይቻል በመሆኑ ቤተ ክርስቲያን በቅርጽ እንጂ በይዘት የለችም ፡ የምለው ሀሰት ቢሆን ጌታ ይፍረድብኝ (ባይባልም አንዳንዶችን ደስ እንዲላቸው ግዴለም ልበለው)፡፡ ድንጋይ ይክባሉ እንጂ አእምሮ ላይ የሚሠሩት አንዳችም ነገር የለም፤ የነሱ የራሳቸው አዕምሮም ባዶ ቀፎ ነው፡፡ አብዛኛው ካህንና ደብተራ ዐይኑ የሚጎለጎለው፣ መረዋ ድምጹ የሚጎላው፣ ቅኔውና ወረብ ሽብሸባው የሚሠምረው ገንዘብ ላይ ነው፡፡ ከሁለት ሰዓት የዐውደ ምሕረት ስብከት ውስጥ ፴ እና ፵ ደቂቃው ብቻ በተግባር ለማይተረጎም ሃይማኖታዊ ቃል የሚውል ሆኖ ሌላው ገንዘብ ስጡ ላይ ነው ፡ መስጠት ብቻውን ያጸድቅ ይመስል፡፡
Blogger Comment
Facebook Comment