በኢትዮጵያ እየቀነሰ ለመጣው የብዝሃ ሕይወት የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ደኖች የመጨረሻው መጠለያ መሆናቸውን የሚያሳዩት ምስሎች የዘንድሮውን ሶኒ ዓለም አቀፍ የብርሃናዊ ምስሎች ሽልማት አገኙ። በስኮትላንዳዊው ብርሃናዊ ምስል አንሽ ኬይረን ዶድስ የተቀረጹት እነዚህ ምስሎች “ሄሮቶፒያ” በሚል ስያሜ በዚህ ከፍተኛ ደረጃ ባለው ዓለም አቀፍ የፎቶ ውድ ድር ላይ ቀርበው ነበር።
+ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት አሁን ማሕበረሰባቸውን ለማበረታት ደኖቻቸውን ለማስፋፋት እየሞከሩ ነው፤ይህም አበረታች የሆነ ተግባር ነው።
+ በኢትዮጵያ ጫካማ የሆነ ቦታ ካየን፥ መሀከል ላይ በርግጥ ቤተክርስቲያን እንዳለ የማወቅ እድል ይኖረናል።
+ ደኖቹ የመጠለያ፣ ፀሎት የማድረጊያ እና የመቃብር ቦታዎች ሆነው ያገለግላሉ።
+ አብዛኛው የሀገሪቱ ጫካ እያደገ የመጣውን የአገሪቱን የሕዝብ ቁጥር ለመመገብ ሲባል ለግብርና መስዋእትነት ወስዷል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ከ 100 ሚሊዮን በላይ ነው፣ ይህም በዓለም 12 ኛ ደረጃ ትልቁ ነው። በተለይ ከ 1974-1991 ዓ.ም በሀገሪቱ የኮሚኒዝም ሥርዓት፡ በ “መሬት ለአራሹ” ዘመን፡ የደን ጭፍጨፋው አሳዛኝ የሆነ ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር፤ በተለይም የቤተ ክርስቲያኒቱን ሰፋፊ ቦታዎች በመውረስ ደኖቻቸውን እየመነጠሩ ለእርሻ እንዲውሉ አድርገዋቸዋል። በአሁን ዘመን በአገሪቱ 5% ብቻ በደን የተሸፈነ ሲሆን፤ በሀያኛው ክፍለ ዘመን እስከ 45 በመቶ ነበር።
+ ምን ያህል ስብጥር እንደጠፋ በውል አናውቅም ፥ ነገር ግን ከጠበቅነው በላይ በጣም ጉልህ የሆነ የስብጥር መጠን መትረፉን እናውቃለን።
+ የደን ብዝሃ–ህይወት ስብጥርን መጠበቅ ለእርሻ በጣም አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም በዓብያተ ክርስቲያናቱ ጫካዎች ውስጥ የሚኖሩት ብዙዎቹ ወፎች እና ነፍሳት ሰብሎችን ለማዳቀል እና ተባይን ለመቆጣጠር ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረክታሉና ነው።
+ ከግማሽ በላይ ለሚሆኑት የኢትዮጵያ ሕዝቦች እናት የሆነችው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ደኖቿ የሰማይ መንግስትን በምድር ላይ የሚወክሉ ናቸው፤ እያንዳንዱ ፍጥረት የእግዚአብሔር ስጦታ ስለሆነ መኖሪያ ይፈልጋል።
+ የተፈጥሮ አካባቢዎች መንፈሳዊ ክልል አካል የሆኑት እነዚህ ደኖች በባህልና በሳይንሳዊ መልኩም በጣም አስፈላጊ ናቸው።
Blogger Comment
Facebook Comment