የ ISIS የሽብር አዋጅና የመንግስት ዝምታ

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ


ትዕቢተኞቹ አሕዛብ የክርስቲያን ገዳዮች እግዚአብሔር አምላክ ስለ ክርስቲያኖች የተናገረውን በጣም ኃይለኛ የሆነ ቃል ያውቁታልን?

[፩ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፫፥]

፮ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?

፲፯ ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።

አሕዛብ ዲያብሎሳዊውን የግድያ ተግባር በድፍረትና በጭካኔ መልክ ቀጥለውበታል፤ ክርስቲያኖችን በተለያየ ሰብብ አስባብ እየፈለጉና የተለያየ ስም እየለጠፉ ሕፃናትን ሳይቀር ይገድላሉ፣ ያስራሉ፣ ይሰውራሉ፣ ያጠፋሉ ፥ ግራኙ የባዕድ አገልጋይ መሪያቸውም ከገደለና ካስገደለ በኋላ ኢትዮጵያን ትቶ ወደ ባዕዳኑ ሃገር ይጓዛል ፥ ከዚያም አሕዛብ እራሳቸው ገድለው እራሳቸው ይጮሃሉ፤ ልክ ሚስቱን ገድሎ ሚስቴን ገደሉብኝ እንዳለው ወንጀለኛ ዓይነት ፥ አዎ! ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሀልና አሕዛብም በሰፊው ያማርራሉ፣ ያጉረመርማሉ፣ ክርስቲያኖችን መውቀስና ያ የኔ ነው፣ ይሄ ይገባኛል ማለት ይጀምራሉ።

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፪፥ ፩፡፭]

"አሕዛብ ለምን ያጕረመርማሉ? ወገኖችስ ለምን ከንቱን ይናገራሉ? የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ። ማሰርያቸውን እንበጥስ፥ ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል። በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል። በዚያን ጊዜ በቍጣው ይናገራቸዋል፥ በመዓቱም ያውካቸዋል።"


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment