ቤተክርስቲያናችን ከታሠሩት ጋር የታሠረች፥ ከተገረፉት ጋር የተገረፈች፥ ከተገደሉትም ጋር አብራ የሞተች ናት

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፰፥፲፰ ]

"እውነት እላችኋለሁ፥ በምድር የምታሥሩት ሁሉ በሰማይ የታሠረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል።"

በኤርትራ ክፍለ ሀገር (ሁሉንም የኢትዮጵያ ግዛቶች ክፍለ ሀገራት ነው የምላቸው) ከተመሠረተ ስድስት መቶ ሃምሳ ዓመታትን ያስቆጠረው ታላቁ የደብረ ቢዘን ገዳም ጣሊያን ኤርትራን እያስተዳደራት እያለም ቢሆን በኢትዮጵያ አስተዳደርና ንብረት ሥር ነበር (በውጫሌ ስምምነት ውስጥ ተጠቅሷል) ላለፉት አሥራ ሦስት ዓመታት በፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወኅኒ የሚንገላቱት(ውሸት ነው አልተፈቱም)የቀድሞው የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ የዘጠና ሁለት ዓመቱ አዛውንት አቡነ አንጦኒዮስ እንዲፈቱላቸውና የኢሳያስ መንግስት በቤተክርስቲያን ጉዳይ የሚያደርገውን ጣልቃ–ገብነት በመቃወም ድምጻቸውን ሲያሰሙ የነበሩት የታሪካዊው ደብረ ቢዘን ገዳም መነኮሳትየሚከተሉት ናቸው፦

፩ኛ. አባ ክብረአብ ተክሌ
፪ኛ. አባ ማርቆስ ገብረ ኪዳን
፫ኛ. አባ ገብረ ትንሣኤ ተወልደ መድሕን
፬ኛ. አባ ኪዳነ ማርያም ተከስተ
፭ኛ. አባ ገብረ ትንሣኤ ዘ-ሚካኤል

ነገሮችን ሰፋ አድርገን ከተመለከትን ይህ በዶ/ር ግራኝ አሕመድ እና በፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የተቀነባበረው ፀረ– ክርስትና ዘመቻ መሆኑን እንረዳለን።

ለአንድ የሰሜን ኢትዮጵያውያን ትውልድ መጥፋት ተጠያቂ የሆነውን ኢሳያስ አፈወርቂን ወድቆበት ከነበረው የማዕቀብና መገለል ጉድጓድ ያወጡት ዶ/ር ግራኝ አሕመድ እና ሉሲፈራውያኑ ደጋፊዎቹ ናቸው። ኢሳያስ ኦነጎችን እና ብርሃኑ ነጋዎችን እየቀለበ ሲያሳድግለት ስለነበር እንዲሁም ወጣት የተዋሕዶ ልጆች እየተሰደዱ እንዲያልቁ ትልቅ አስተዋጽዖ ስላበረከተ የ ዶ/ር ዐቢይም የሉሲፈራውያኑ ደጋፊዎችም ባለውለታቸው ነበርና ነው። አሁን ሁለቱ የተዋሕዶ ጠላቶች በተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ጥቃት በመፈጸም ላይ ይገኛሉ።

በጅጅጋ የተዋሕዶ ልጆች ላይ የተካሄደው ጭፍጨፋ እንደ ማንቂያ ደወል ሊሆነን በተገባ ነበር። ዛሬ እየታዘብን ያለነው፤ ወንጀለኞች እየነገሡ፥ እውነተኞች እየኮሰሱ፤ ዘራፊዎች እየፋፉ፥ ከልብ አገልጋዮች እየተገፉ፥ መንፈ ሳውያኑ ሊቃውንት ሜዳ ላይ እየተጣሉ የመጡበትን ዘመን ነው። እስኪ በአሁኑ ሰዓት እየተሰደደ፣ እየታሠረና እየተገደለ ያለው ማን እንደሆነ እንመልከት። ሃፍረተ–ቢሱ ገዳይ አል–ዐቢይ ገና ሃዘኗን ያልጨረሰችውን የጄነራል አሳምነውን ባለቤትና የልጆቹ እናትን ለማሠር ደፍሯል፤ ይህ እንዴት ይሆናል? በኢትዮጵያ ታሪክ ይህን መሰሉን ጽንፈኛ ተግባር የምናውቀው መንግስቱ ኃይለ ማሪያም የኃይለ ሥላሴንና ሚንስትሮቹን ቤተሰቦች አንድ ባንድ እየለቃቀመ ሲገድል በነበረበት ዘመን ብቻ ነው። ወያኔ እንኳን የ ብርሃኑ ነጋንና መሰሎቹን ቤተሰቦች ያንገላታበት ግዜ አልነበረም። ገዳይ አል–ዐቢይ እንደ ሞኞቹ ወያኔዎች በማሠር ብቻ አልተወሰነም፤ ተቃዋሚ የሚላቸውን እየመነጠረ ወዲያው ይገድላል።

ሰሞኑን ከታሠሩት ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን መካከል አንድም ጴንጤ ወይም ሙስሊም አለመኖሩ ብዙ ሊጠቁመን የሚችል ነገር አለ። አዎ! በተዋሕዶ ልጆች የግራኝ አሕመድ እና የመንግስቱ ኃይለማርያም ቀይ ሽብር ዘመን ተመልሶ መጥቷል።

ቤተክርስቲያናችን ከታሠሩት ጋር የታሠረች፥ ከተገረፉት ጋር የተገረፈች፥ ከተገደሉትም ጋር አብራ የሞተች ናት፤ ደግሞም የካህን ሐዘንና ዕንባ ከባድ ነው፥ ውዳሴ ማርያምና ዳዊት ስለሚደግም ስር ይነቅላልና ለጉዳዩ ቤተክህነትም ምዕመናንም ተገቢውን አትኩሮት እንስጠው።

እግዚአብሔር ሁሉንም ከእሥራታቸው ይፈታቸው ዘንድ ስለ ታሠሩ ሰዎች እንማልዳለን!
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment