ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
የዶ/ር አብዮት አሕመድ መንግስት የኢትዮቴሊኮምን፡ “ኢትሳላት” ለተባለው ለተባበሩት ዓረብ ኤሚራቶች ( UAE ) ተቋም አሳልፎ ለመስጠት ሽርጉድ በማለት ላይ ነው። (ስማቸው ሳይቀር እንዲመሳሰል ተደርጓል፤ “ኢትዮቴሌኮም”፣ “ኢትሳላት”። እነዚህ የዲያብሎስ ልጆች የስልኩን መስመር የሚፈልጉት በስልኩ መስመር ውስጥ ጋኔን አፍላቂ የሆነ የንፋስ መስጊድ ለማስገባትና የመቶ ሚሊየን ኢትዮጵያውያንን መንፈስ ለመቆጣጠር ነው። ወዮላችሁ ለአረቦች ትሸጡና!
ስልክ የመገናኛ ዘይቤ ብቻ አይደለም። ሴረኞች የሰው ልጅን በጨረር ለመመረዝና ለመሰለል የሚጠቀሙበት መሣሪያ ጭምር ነው። ይህ የኢትዮ ቴሌኮምን የሚመለከተው ዜና በተሰማ በማግስቱ የዓረቡ ዓለም አስደንጋጭ የሆነ ጉዳይ ላይ ወድቋል፤ በዛሬው ዕለት ኦማን፣ ኢራን እና አረብ ኤሚራቶች አካባቢ በሚገኘው የባሕረ ሰላጤ ሁለት ነዳጅ የያዙ ታላላቅ መርከቦች ላይ የ ቦምብ ጥቃት ደርሶባቸው ሰምጠዋል። እርስበርስ እጅግ በጣም በሚጠላሉት በሱኒ እና ሺያ እስላም ሀገራት(ሳውዲ፣ ኤሚራቶች፣ ካታር እና ኢራን) መካከል በቅርቡ አስከፊ የሆነ ጦርነት እንደሚካሄድ እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላለሁ።
ኳታር የ2022ቱ የዓለም እገር ኳስ ዋንጫ አዘጋጅ ሆና ስትመረጥ፤ ይህ ውድድር የሚካሄድ አይመስለኝም የሚል ስሜት በወቅቱ ተሰምቶኝ ነበር፤ እስኪ እናያለን።
[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፴፬፡]
፰ የእግዚአብሔር የበቀሉ ቀን፥ ስለ ጽዮንም ክርክር የብድራት ዓመት ነው።
፱ የኤዶምያስም ፈሳሾች ዝፍት ሆነው ይለወጣሉ፥ አፈርዋም ዲን ይሆናል፥ መሬትዋም የሚቀጠል ዝፍት ትሆናለች።
፲ በሌሊትና በቀንም አትጠፋም፥ ጢስዋም ለዘላለም ይወጣል፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም ድረስ ባድማ ሆና ትኖራለች፤ ለዘላለም ዓለም ማንም አያልፍባትም።
፲፩ ጭልፊትና ጃርት ግን ይወርሱአታል፤ ጕጕትና ቍራም ይኖሩባታል፤ በላይዋም የመፍረስ ገመድና የባዶነት ቱንቢ ይዘረጋባታል።
፲፪ መሳፍንቶችዋን ወደ መንግሥት ይጠራሉ፥ ነገር ግን ማንም አይገኝባትም፤ አለቆችዋም ሁሉ ምናምኖች ይሆናሉ።
፲፫ በአዳራሾችዋም እሾህ በቅጥሮችዋም ሳማን አሜከላ ይበቅሉባታል፤ የቀበሮም ማደሪያና የሰጐን ስፍራ ትሆናለች።
፲፬ የምድረ በዳም አራዊት ከተኵሎች ጋር ይገናኛሉ፥ አጋንንትም እርስ በርሳቸው ይጠራራሉ፤ ጅንም በዚያ ትኖራለች ለእርስዋም ማረፊያ ታገኛለች።
Blogger Comment
Facebook Comment