ኢትዮጵያ በምዕራባውያን ኢምባሲዎች መርሬትዋ እየተወረረ ነው

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

ይህ ብርሃናዊ ምስል የሚያሳየን፦ ዛሬ የኦሮምያ ክልል ሴቶች "በደቡብ እና ምዕራብ ኦሮምያ የተጣለ አስቸኳይ አዋጅ ይነሳልን፣ በመንግስት ወታደሮች እየተፈፀመብን ያለው አስገድዶ መድፈር ይቁም" የሚሉ እና መሰል ጥያቄዎችን ይዘው በአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት ድምፃቸውን እያሠሙ ነው። ይህ ድርጊት ኢትዮጵያ በሌሎች ሀገራት አስተዳደር እና ተፅዕኖ ወድቃ እንደቆየች የሚያረጋግጥ ነው።

እስኪ "ዲፕሎማሲ ቅብርጥሲ" የሚለውን የአውሬ ማታለያ ትተን እራሳችንን በሐቀኝነት እንጠይቅ፤ ኤምባሲዎች፤ በተለይ የምዕራቡና ዓረቡ ዓለማት ኤምባሲዎች ሕዝባችንን ከመተናኮል ሌላ ለሀገራችን የሚያደርጉት ምን በጎ ነገር አለ? ምንም!

ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን የቆመ መሪ በለገጣፎ፣ ሱሉልታና ቃሊቲ የድኻ ኢትዮጵያውያንን ቤት ከማፈራረስ አንጋፋ የሆኑትን የአሜሪካን፣ ፈረንሳይን እና ብሪታኒያን ኤምባሲዎች ቅጽር ግቢ ቆርሶ ለኢትዮጵያውያን ሲለግሥ አይታችኋል ሰምታቹሃል የእነዚህን ኤምባሲዎች ቅጽር ግቢ ስፋት? ለኢምፔሪያሊዝማዊ ተንኮል አስበውበት፣ ወይንም ተንኮል ሊሠሩበት ካልሆነ ሌላ ምን ሊያደርጉበት ነው?
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment