ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
በእስራኤል፣ ጀርመን፣ ብራዚል እና ላትቪያ የሚገኙት የአሜሪካ ኢምባሲዎች የሰዶማውያኑን ሰንደቅ ዓላማ ለመስቀል ፈቃድ እንዲሰጣቸው ጠይቀው ነበር። ርዕሰ ብሔር ትራምፕ ግን ከልክለዋል።
ይህ ውሳኔ ጥሩ ነው፤ ነገር ግን፡ ሴት ልጃቸውን በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ ልከው የነበሩት ርዕሰ ብሔር ዶናልድ ትራምፕ፡ በአንድ በኩል፡ ልክ እንደ ወስላታው ባራክ ሁሴን ኦባማ፡ ይህ የሰኔ ወር የግብረ-ሰዶማውያን ወር እንዲሆን ድጋፋቸውን ይሰጣሉ፥ በሌላ በኩል ደግሞ ቆንስላዎች ሰንደቅ ዓላማውን እንዳይሰቅሉ ያዛሉ፤ ይህ የሚያሳየን ፖለቲከኞች የሰይጣን ተከታዮቹንም ክርስቲያኖቹንም ማስቀየም እንደማይፈልጉ ዲፕሎማሲዊ የሆነውን መንገድ መከተላቸውን ነው።
ይህ ነገር ሰሞኑን በኢትዮጵያ ከሚካሄደው ሤራ ጋር የተያያዘ ነው። በዚህ አጋጣሚ መጠየቅ ያለብን፤ ዶ/ር አብዮት አሕመድ ስልጣን ላይ እንደወጣ የዴንማርክና ፊንላንድ ኤምባሲዎች የሰዶማውያኑን ሰንድቅ ዓላማ አዲስ አበባ ላይ እንዲሰቅሉ ማን ነው የፈቀደላቸው? ይህን ከላሊበላ ጉዳይ ጋር በማያያዝ ዶ/ር አሕመድን አፋጣችሁ ጠይቁት፤ እስካሁን ለምን በጉዳዩ ላይ ጸጥ አለ? ጸጥታውን ከቀጠለና ተገቢውን እርምጃ የማይወስድ ከሆነ ሀገራችን የመጀመሪያውን የግብረ-ሰዶማዊ-እስላማውያን መንግስት መስርታለች ማለት ነው ፥ ሃይማኖታቸው ሰይጣናዊነት፣ አማልክታቸውም 'በኣልና ሞሎክ' ናቸው ማለት ነው። አቤት ጉዳቸው!
[ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴፪፥፴፭]
“ይሁዳን ወደ ኃጢአት እንዲያገቡት፥ ይህንን ርኵሰት ያደርጉ ዘንድ፥ እኔ ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን ነገር፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለሞሎክ በእሳት ያሳልፉ ዘንድ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉትን የበኣልን የኮረብታውን መስገጃዎች ሠሩ።”
[ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፯፥፱፡፲፩]
“ትሰርቃላችሁ፥ ትገድላላችሁ፥ ታመነዝራላችሁ፥ በሐሰትም ትምላላችሁ፥ ለበኣልም ታጥናላችሁ፥ የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት ትከተላላችሁ መጣችሁም፥ ስሜም በተጠራበት በዚህ ቤት በፊቴ ቆማችሁ። ይህን አስጸያፊ የሆነ ነገርን ሁሉ አላደረግንም አላችሁ። ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት በዓይናችሁ የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን? እነሆ፥ እኔ አይቻለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።”
Blogger Comment
Facebook Comment