ግብረሰዶማውያን ለምን ኢትዮጵያ መድፈር ጀመሩ?


ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

ሁሉንም ነገር አስቀድመው በደንብ ያቀነባበሩት ይመስላል፤ ዶ/ር አሕመድ ልክ ስልጣን ላይ ሲወጣ የዴንማርክና ፊንላንድ ኤምባሲዎች የግብረሰዶማውያንን ባንዲራ በኢትዮጵያ ምድር አውለበለቡ፤ በአጋጣሚ?አይመስለኝም!

ዶ/ር አብዮት አሕመድ ከፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር የላሊበላን ቅዱስ ምድር ሲረግጥ የዓለም አቀፍ የግብረሰዶማውያን አጋንንት ተለቀቁ፣ የቤተ ጊዮርጊስንና የአማኑኤል ዓብያተክርስቲያናትን ለመድፈር ታሪካዊ የሆነ አጋጣሚ ተፈጥሮናል ብለው አሰቡ፤ ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያን በዓለም ላይ በጣም ጽኑ የሆነ ፀረ-ግብረሰዶማዊነት አቋም እንዳላቸው ስለሚያውቁ የልብ ትርታቸውን ለመለካት "ወደ ላሊበላ እንሄዳለን!" እያሉ ተንኮለኛ በሆነ መንገድ እራሳቸውን አስተዋወቁ። በአጋጣሚ? አይመስለኝም!

የተዋኅዶ ጋዜጠኞች፡ እስኪ ባካችሁ ዶ/ር አህመድ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን አቋም እንዳለው ለማወቅ ሞክሩ፤ "ግብረሰዶማዊያን አንተን ተከትለው ለኢትዮጵያውያን ቅዱስ ወደ ሆነችው ላሊበላ ምድር ለመምጣት አቅደዋል፤ ምን ይሰማሃል?" ብላችሁ እስኪ ጠይቁት።


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment