በራሳቸው በካቶሊኮች ዘንድ የተጠላውና መናፍቅ የሆነው የቫቲካን ጳጳስ ፍራንሲስኮ ከቡልጋሪያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶች ጋር ለመገናኘት እሁድ ዕለት ወደ ቡልጋሪያ በመጓዝ ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች ጋር የጋራ የጸሎት አገልግሎት የማክበር ተስፋ ነበረው። ነገር ግን የቡልጋሪያ ኦርቶዶክስ አባቶች ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር ጸሎት ለማድረግ ፈቃደኞች እንዳልሆኑ ገልጠዋል።
የቡልጋሪያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት በዛሬው ዕለት በሶፊያ ከተማ ከጳጳሱ “ለሰላም ፀሎት” ማድረጊያ ሥነ ሥርዓት ጋር እንዲቀላቀሉ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርገውታል፤ በተለይ በዚህ “የሰላም ጸሎት” ላይ የሙስሊም መሪዎች መካፈላቸውን የቡልጋሪያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶችን አላስደሰታቸውም።
የቡልጋሪያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለብዙ ዘመናት በፀረ– ክርስቶሷ ኦቶማን ቱርክ እና በኮሙኒዝም ጭቆና ቀንበር ብዙ ፈተናን ያየች ቤተክርስቲያን ናት።
ከሦስት ዓመታት በፊትም ጳጳስ ፍራንሲስኮ በኦርቶዶክስ ጆርጂያ ተመሳሳይ ዕጣ ደርሶት ነበር።
የቡልጋሪያ አባቶች ውሳኔ ትክክለኛ ነው። ይህ ግራ የተጋባ ጳጳስ አንድ የዓለም ሃይማኖት (በቫቲካን መሪነት) ለመመሥረት በመጣደፍ ላይ ነው፤ ለዚህም ነው መሀመዳውያኑ በማስጠጋት ላይ ያለው፣ ለዚህም ነው በሚሊየን የሚቆጠሩ መሀመዳውያን “ስደተኞች” አውሮፓን እና አሜሪካን እንዲያጥልቀልቁ ድጋፉን የሚሰጠው። ወደ ቡልጋሪያም የሄደው ያው ቡልጋሪያ በሯን ለሙስሊም ስደተኞች እንድትከፍት ለመገፋፋት ነው።
"ለሰላም ፀሎት” በሚል ሰበብ በአገራችንም የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች በአንድ ላይ ሲሰባሰቡ እያየን ነው፤ ይህ ትልቅ ስህተት ነው፤ ከሰይጣን ጋር ሆኖ ለሰላም ፀሎት ማድረግ አይቻልም፤ ቅጥፈት ነው! እራስን ማታለል ነው!
ሰሞኑን አንዳንድ አስገራሚ ነገሮችን እያየን ነው፤ ለምሳሌ የበዓል ወቅትን ወይም ልዩ መርሃ ግብሮችን በመጠቀም እንደ እነ መጋቢ ሃዲስ እሸቱ አለማየሁ የመሳሰሉትን ታዋቂ የቤተክርስቲያን ‘አገልጋዮች‘ ከሙስሊም ኡስታዞችና ሸሆች ጋር መድረክ ላይ ወይም ስቱዲዮ ውስጥ በአንድ ላይ እንዲገናኙና በአገራችን ሁኔታ ላይ ተመሳሳይ መልዕክት እንዲያስተላልፉ እየተደረገ ነው፤ ከጀርባው ትልቅ ተንኮል አለ፤ “ሁሉም ሃይማኖቶች አንድ ናቸው፣ አንድ ነን፣ በሉሲፈር መሪነት ዓለም አቀፋዊ የሆነ አንድ ሃይማኖት መመሥረት አለብን” የሚል አጀንዳ ያለው ነው።
[፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፮፥፲፬ ]
“ ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?
Blogger Comment
Facebook Comment