ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
"ህወሓት" በ ብሪታኒያ
" ኦነግ" በ ጀርመን
" አብን" በ አሜሪካ
" ኢዜማ" በ ስዊድን?
እርዳት ነው የተመሠረቱት!
ከሃዲ ፖለቲከኞች መካከል ብርሃኑ ነጋ (ዶ/ር)አንዱ ነው። ከሃዲ? አዎ! በብዙ ረገድ፤ ለምሳሌ ብርሃኑ ነጋ በ1997 ዓ.ም ላይ በተደረገው የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ምርጫ ቅንጅት ለአንድነት እና ዴሞክራሲ ፓርቲን ወክሎ የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆኖ መመረጥ ችሎ ነበር፤ ነገር ግን ከንቲባነቱን በቂ ሆኖ ስላላገኘው እና ወዲያው ጠቅላይ ሚንስትር መሆን ስለተመኘ ኢትዮጵያን ለቅቆ በመውጣት "አርበኞች" ግንቦት 7 የተባለ ፓርቲ መሠረተ። ይህ ሰው በእውነት ኢትዮጵያዊ ፍቅር ቢኖረው እና በወቅቱ ያገኘውን የከንቲባነት ማዕረግ ተቀብሎ ቢሆን ኖሮ በአሁኑ ሰዓት እንደምናየው አዲስ አበባ የዋቄዮ አላህ ልጆች ጢቦየ ጢቦ ጢብጢብ ጨዋታ ሜዳ አትሆንም ነበር።
ወደ "ኢዜማ" ስመለስ፤ በኢትዮጵያ ስም እንጅ፤ የዐምሓራ፣ ትግራዋይ፣ ጉራጌ ወይም ኦሮሞ ነፃ አውጭ ድርጅት በማለት ሌላ ፓርቲ አለመመስረታቸው ጥሩና የሚበረታታ ነው፤ ነገር ግን ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን በአመራርነት ቦታ ላይ ማስቀመጣቸው ስህተት ነው፤ ከዚህ በፊት ሲታይ በነበረው ቅሌታማ እና ፀረ–ኢትዮጵያ የፖለቲካ መዋቅር ያለቆሸሸ አዲስ ሰው/ ትኩስ ደም መምረጥ ነበረበትና።
ብርሃኑ፡ ከአሥሩ የ 'ሲ አይ ኤ' ቅጥረኞች መካከል አንዱ ነው፤ ስለዚህ የመጭው ምርጫ ልክ እንደ 1997ቱ ምርጫ ነው የሚሆነው። አሁን በተራው የሉሲፈራውያኑ ምዕራባውያን መሣሪያዎች እና "Useful Idiots / ጠቃሚ ጅሎች" 'ህወሓት' የመሠረቱት ኢህአዴግ በእነ ዶ/ር አብዮት ኦሮሞዎች መሪነት ስልጣኑን አልለቅም በማለት እነ ዶ/ር ብርሃኑን በድጋሚ እንደሚያዋርዳቸው ገና ካሁኑ መተንበይ ይቻላል።
በፓርቲያቸው ምስረታ ሥነ ሥርዓት ላይ የስዊድን ሶሺያል ዲሞክራቶች እንዲሳተፉ መጋበዛቸው በጣም የሚገርምና የሚያሳፍር ነው። በተለይ ሶሺያል ዲሞክራቲክ ፓርቲ በመላው አውሮፓ በጣም እየተጠላ የመጣ ፓርቲ ነው። ይህ ፓርቲ ለምሳሌ በስዊድን፣ ዴንማርክ፣ ጀርመን እና አውስትሪያ ተወዳጅነት የለውም፤ ይህ ፓርቲ ከአረንጓዴ ፓርቲ ጋር በማበር ሰዶማዊነትን የሚያስፋፋ፣ ህፃናት ደፋሪዎችንና ሙስሊም ወራሪዎችን የሚረዳ መጥፎ የሆነና ግራ የተጋባ ፓርቲ ነው።
ከአውሮፓ እና አሜሪካ ውድቀት ልምድ መውሰድ ይኖርብናል እንጅ ለውድቀታቸው ያበቋቸውን መንገዶች እንደ ጥሩ ልምድ አድርገን በመውሰድ አብረን መውደቅ የለብንም።
በነገራችን ላይ፤ የእነ 'ሲ አይ ኤ' ን እርኩስ ተግባር ያጋለጠው አውስትራሊያዊው የዊኪሊክስ መስራች ጁሊያን አሳንጅ ለንደን ውስጥ በሚገኘው የኤኳዶር ኤምባሲ ለሰባት ዓመታት ያህል የቁም እስረኛ ሆኖ የቆየበት እና ከአንድ ወር በፊት ወደ እስር ቤት የተወሰደበት ምክኒያት፤ በስዊድን ወሲባዊ ጥቃት ፈጽሟል ተብሎ በመከሰሱ ነበር።
አዎ! ለሁሉም ሤራቸው፡ አንዴ ስዊድንን፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ዴንማርክን፣ ጀርመንና ፈርንሳይን ይጠቀማሉ፤ ሁሉም አንድ ዓይነት ተልዕኮ ያላቸው የሳጥናኤል ሀገራት ናቸውና።
Blogger Comment
Facebook Comment