ባለፈው ወር ላይ ሰዶማዊው የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ማክሮን ከ ግራኝ ዐቢይ አሕመድ ጋር ሆኖ ላሊበላን አላግባብ ረግጦ ነበር። “ላሊበላን እናድሰው” ብለው ነበር፤ ግን ጉዳዩ ተንኮል እንዳለበት የላሊበላን ድንቅ ዓብያተክርስቲያናት እንዲሠሩ አባቶችን እና መላዕክቱን ያዘዘው ኃያሉ እግዚአብሔር ያውቃል። እስኪ ይታይን፤ ወገኖቼ፤ በጣም ብርቅ የሆነውን እና በጎብኝዎች ዘንድ የመጀመሪያውን ቦታ የያዘውን ላሊበላ ንብረታችንን በእድሳት መልክ ሲተናኮሉ የራሳቸው አንደኛ ቱሪስት ሳቢ ካቴድራል ተቃጠለ። ሆኖም፡ በተለይ በእነርሱ ፋሲካ ቅዱስ ሣምንት ይህ አደጋ መከሰቱ እጅግ በጣም አሳዛኝና አጠራጣሪም ነው። የመሐመድ አርበኞች ይህን ካቴድራል እናፈርሰዋለን በማለት ደጋግመው ይዝቱ ነበር።
ያም ሆነ ይህ፡ በላሊበላ ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ያላግባብ ካባውን ለብሰው የነበሩት ፕሬዚደንት አማኑኤል ማክሮን እና ግራኝ ዐቢይ አሕመድ ለራሳቸውም ለአገሮቻቸውም መጥፎ ዕድልን ይዘው መጥተዋል።
ኖትራዳም ካቴድራል ከተገነባ 850 ዓመት ሆኖታል፣ ለፈረንሳይ ትልቁ ታሪካዊ ቦታ፣ ታሪካዊ ኩራት ነው። ትልቁ የጉብኝት ቦታም ነው። ትልቅ ቅርስ በውስጡ ይዟል። ይህ ካቴድራል 1ኛውን የዓለም ጦርነት፣ 2ኛውን የዓለም ጦርነት፣ የናዚን ወረራ .. ወዘተ. ሁሉንም ተቋቁሞ ለዚህ የበቃ ነው።እንደኛው አገር ላሊበላ በሉት - ለፈረንሳዮች። ይህን ሁሉ መከራ ያለፈው ታሪካዊ ቦታቸው፣ ዛሬ በእሳት ወድሟል። ምናልባት ቢተርፍ የተወስነው በግራና በቀኝ ያለው ግድግዳ ብቻ ነው - እሱም ሙሉ በሙሉ ከድንጋይ ስለተሰራ።
Blogger Comment
Facebook Comment