ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
መገናኛ ብዙኃን የአብዛኛው ህዝብ አዕምሮ ሰላቢ እጆች ለመቆጣጠር የሚጠቀሙባቸው መሣርያ ናቸው።
ያሳዝናል፤ የምዕራቡ ዓለም ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያም ሜዲያ በ666ቁጥጥር ሥር ነው። ሜዲያዎቹ እና ሠሪዎቻቸው ፀረ-ክርስቶስ፣ ፀረ-ተዋሕዶ፡ ፀረ-ኢትዮጵያ የሆነ አቋም ነው ያላቸው።
በምሥሉ የሚታየው ባለ አንድ ዓይን ምሥል ፣ በቅርቡ የተቋቋመው 'አሥራት ሚድያ' መለያ ምልክት ነው። አንድ ዓይን የሰላቢ እጆች የሰይጣን አምልኮ ነው።
ለምሳሌ የኢትዮጵያ ናቸው የሚባሉት የውስጥም ሆኑ የውጭ ራዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ኢትዮጵያዊ የሆኑትን የተዋሕዶ አጽዋማትንና በዓላትን በማስመልከት በአግባቡ ሲያስተዋውቁ አይሰሙም/አይታዩም። ልብ ብለው ጣቢያዎቹን የሚከታተሉ ወገኖች ከታዘቧቸው ክስተቶች መካከል፤ ለምሳሌ የልደት ወይም የመስቀል በዓል ሲሆን፤ ገንዘብን ከሚመለከቱ ማስታወቂያዎች ጋር የተያያዘ ካልሆነ፡ ስለ በዓላቱ ምንነት ነካ ነካ አድርገው የሚያወሱት ልክ ዕለቱ ሲደርስ ነው። የተዋሕዶ መዝሙራትንማ በጭራሽ አሰምተው አያውቁም።
Blogger Comment
Facebook Comment