ጥንተ ጠላታችን ሀገረ እንግሊዝ የአፄ ቴዎድሮስን ፀጉር ለኢትዮጵያ ልመልስ ነው አለች፡፡


እንግሊዝ ሀገር በብሔራዊ ጦር ሙዚየም የሚገኘው የአፄ ቴዎድሮስ ፀጉር እንግሊዝ ወደ ኢትዮጵያ ልትመልስ መሆኑን ቢቢሲ ዘገበ፡፡ ሀገረ እንግሊዝ ብዙ የኢትዮጵያ ቅርሶች ዘርፋ መውሠድዎ ይታወቃል።

እንግሊዞች 1960 ዓ.ም ላይ ኢትዮጵያን ለመውረር ሲመጡ እጅ ላለመስጠት ራሱን ያጠፋውን ንጉስ ቴዎድሮስ ፀጉር መውሰዳቸው ይታወቃል፡፡

እንግሊዞች በተጨማሪም የንጉሱን ልጅ ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ አፅም ጨምሮ የተለያዩ የኢትዮጵያን ቅርሶች ዘርፈዋል፡፡

እንደ ኤፒ ዘገባ በመጪው ሐሙስ ለንደን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢንባሲ በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር ቀጠሮ ተይዟል፡፡


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment