ጳጳሱ ግብረ-ሰዶማውያንን በማውገዛቸው የ፯ወር እሥራት ተፈረደባቸው!

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

በደቡባዊው የፔሎፖኔስ ክልል የካላቭሪታ እና አይጊያሊያ ጳጳስ የሆኑት አምቭሮሲዮስ ለሰባት ወራት እንዲታሠሩና እና ለሦስት ዓመትም ከሥራቸው እንዲታገዱ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። ልክ በእርኩሶቹ ፓኪስታን እና ሳውዲ አረቢያ እንደሚታየው፡ በአውሮፓም "መሳደብን የሚከለክል ህግ" በሥራ ላይ እየዋለ ነው ማለት ነው…

በዓለማችን ላይ አሁን ከሚታዩት የክርስቶስ ተቃዋሚዎች አንዱ የግሪኩ ጠቅላይ ሚንስትር አሌክሲስ ሲፕራስ ነው። ኮሙኒስቱ ጠ/ሚ/ር አሌክሲስ ሲፕራስ ከ አራት ዓመት በፊት ስልጣኑን ሲረከብ ' በመጽሐፍ ቅዱስ መሃላ አልፈጽምም" ለማለት የደፈረ የመጀመሪያው ግሪካዊ መሪ ነው።


ከግሪክ እስክ አሜሪካ፡ ከቬኔዝዌላ እስከ ኢትዮጵያ ስልጣን ላይ እየወጡ ያሉት በፖለቲካው ዓለም "ወጣት" የሚባሉት ናቸው። ለበጎም ይሁን ለክፉ፡ ትኩስ የወጣት ደም ማሕበረሰብ ውስጥ የጃጀውን አሮጌ ደም ለማዘዋወር/ለማመስቃቀል አስተዋጽዖ ያበረክታል። አሁን በመላው ዓለም የምናየው ይህ ነው።

ልክ እንደ ዶ/ር አብይ አህመድ፤ ጠ/ሚ/ር አሌክሲስ ሲፕራስም በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ይዘምታሉ፤ ውድቀታቸውም ይህ ይሆናል፤ ምክኒያቱም የተላኩት ለሌላ ዓላማ ነበር፤ እምነተ–ቢስ ስለሆኑ የተላኩበትን ዓላማ እነርሱ እራሳቸው አያውቁትም እንጂ የተላኩት የክርስቶስን ልጆች ከሚተናኮሉት ሉሲፈራውያን ጋር እርስበርስ እንዲፋለሙ ነው። ከእባብ መርዝ መዳኛው እራሱ የእባቡ መርዝ ነውና፤ ጃዋር የሚባል መርዛማ እባብ ከነደፈን አላሙዲን የተባለ መርዛማ እባብ መድኃኒት ይሆናል።

[፩ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፩]

፳፮ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም።

፳፯ ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤

፳፰ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment