ከዐቢይ አሕመድና ለማ መገርሳ ጀርባ ያለች ሀገረ ጀርመን!

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ


[ኢትዮጵያ አውታር ጥር 23 ቀን 2011 ዓ.ም.] - ሀገረ ጀርመን ፡ ከዐቢይ አሕመድና ለማ መገርሳ ሴራ ጀርባ ያለች ሀገር ናት። እንግዲህ ፡ የነ ዐቢይ የጥፊት መንገድ እንዲቀጥል እያበረታቻት ነው። ዐቢይ እና ለማ በሀገረ ጀርመን መነሻው ባደረገ "የፕሮቴስታት" ምንፍቅና የእምነት ድርጅት አባል መሆናቸው ልብ ይሏል።
የሀገረ ጀርመን ርዕሰ ብሔሩ ላሊበላን ከጎበኙ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው ወደ ሀገራቸው ለመብረር ሲሞክሩ ጥያራዎ ችግር አጋጥሟታል። ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው፤ እ.አ.አ እ.አ.አ በ 2014 ዓ.ም፤ ወስላታው ሽታይንማየር ገና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር እያሉም በአዲስ አበባ ተመሳሳይ ችግር ገጥሟቸው ነበር።

በብዙ ጀርመኖች ዘንድ የሚጠሉት ሶሻሊስቱ ርዕሰ ብሔር ፡ ፍራንክ-ቫልተር ሽታይንማየር ለተንኮል ነበር ወደ ኢትዮጵያ የተጓዙት።

ይህን ዜና ሁሉም የጀርመን ሜዲያዎች በሰፊው አቅርበውታል፤ በተለይ በኢንተርኔት ጋዜጦች ላይ የሚሰጡት በጣም ብዙ የአንባብያን አስተያየቶች ለርዕሰ ብሔሩም ሆነ ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ጥላቻና ንቀት የተሞላባቸው ነው።

ለምሳሌ፦
“ርዕሰ ብሔሩ እዚያው ይቅሩ፤ አውሮፕላናቸውም በአዲስ አበባ ይቆይ ምናልባት የኢትዮጵያ ወጣቶች ወደ አውሮፓ ከሚሰደዱ የሥራ ዕድል ይፈጥርላቸው ይሆናል።”
"ርዕሰ ብሔሩ በታክሲ እስክ ሜዲተራንያን ባሕር ድረስ ይምጡና በጀልባ እንዲሻገሩ እናደርጋቸዋለን።”
"ምናለ ሁሉም የፓርላማ አባላት አጅበውት ቢሆን እና ሁሉም እዚያ ተቀርቅረው ቢሆን?!“
"ይሄ ሰውዬ አይናፍቀንም፤ እዚያው በርበሬ የሚበቅልበት አገር ቢቀር ይሻለዋል”
"ኢትዮጵያ ቆንጆ ነች አሉ፤ ግን የፕሬዚደንቱ እዚያ መሆን፡ ለኢትዮጵያውያኖች የስደት መንስኤ ይሆናቸዋል”
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment