ህወሓት ለምን ቃና ቴሌቪዥንን ከሰርጭት አያግድም ፧


ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ


ፖለቲከኛ አይደለሁም። ፖለቲካ የዲያብሎስ ማታለያ መሣርያ መሆኑ አሳምሬ አውቃለው። ህወሓት 1967 ዓመተ ምሕረት ጀምሮ የቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ ጠላቶች የሆኑት ምዕራባውያን (ኢሉሚናቲዓላማ አስፈጻሚ በመሆን እየሰራ ያለ የጨለማው ገዢ አገልጋይ  ድርጅት ነው። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ታጥቆ የተነሳው ድርጅቱ በ፵፫ የቆይታው ዕድሜ ትልቅ ጥፋት ፈጽሟል።

በድርጅቱ ምንም አይነት ግላዊ የሆነ ቂም ወይም ጥላቻ የለኝም። በተቃራኒም ወላጆቼ (አባትና እናቴህወሓት ደርግን ከስልጣን ለማውረድ በተነሳበት የትግል ወቅት አባል የነበሩና የራሳቸውን አስተዋጽዖ ያደረጉ ናቸው። ተወልጄ ያደኩትም ትግራይ ክፍለ ሃገር ውስጥ ነው። እንደ ህወሓት ትግራይን ክልል ብየ መጥራት አልፈልግም። ምክንያቱም ድርሳነ ድያብሎስ በሆነው ሕገ መንግሥት ብሎ የሚጠቀምበት ሰነድ ሆን ተብሎ በምዕራባውያን ሰነ ሓሳብ አመንጪነት ኢትዮጵያን ወደ ትንንሽ ክልሎች በመከፋፈል ቅዱስ የሆነውን ሰንደቅ ዓላማዋ ወደ ተለያዩ ቀለማት በማብዛት ማጥፋት ያለመ ነውና። ዐምሓራ ጠላቴ ነው ብሎ የተነሳበት ምክንያትም ውሃ የማይቋጥርና መሰረት የሌለው መነሻ ነበር። ይህ ምክንያት ይሁን እንጂ ዋናው ዓላማው ግን ቅድስት ምድር ኢትዮጵያን መከፋፈልና ማጥፋት ነበር። ይህ ዕቅድም ኤርትራን   በማስወገድ ጀምራዋለች።

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለማጥፋትም በምዕራባውያን ደጋፊነት እየሰራ ነው። ዐምሓራ ጠላቴ ነው ያለበት ምክንያትም ዐምሓራ ማለት ነጻ ህዝብ እግዚአብሔርን ብቻ የሚያመልክ ማለት ነውና እግዚአብሔርም የዚች ሃገር መሠረት ነው። ዐምሓራን ማጥፋት የኢትዮጵያ ታሪክ መሰረት የሆኑት ነገሮች ከስረመሰረት በማጥፋት ምዕራባውያን በዓይነ ቁራኛ የሚከታተልዋትን ሃገር በቀላሉ እጃቸው ውስጥ እንድትወደቅ ለማድረግ በር የሚከፍት ነው።

ይህ ድብቅ አላማ ለመፈጸም ኢትዮጵያዊው ታሪኩም እንዳያውቅ በምዕራባውያን ቆሻሻ ነገሮች ጭንቅላቱ እንዲሞላ በማድረግ ስለ ሃገሩ እንዳያውቅ እንዳይቆረቆር የተነገረው ብቻ አሜን ብሎ የሚቀበል ስሉብ ማንነት የተላበሰ ዜጋ እንዲሆን ማድረግ ነው። ይህ ለማደረግም የኛን ማንነት የማይናገሩ በተቀራኒው የውጭ ሃገራት ማንነት ተንኮል ፣ ሴራ መሰሪይነት የሚያስተምሩ የሞስኮተ ትዕይነት (ቴሌቪዥንጣብያዎች ማስፋፋት ነው።

GeoPoll Media Measurement service የተባለ በመገናኛ ቡዙሃን ላይ ጥናት የሚያደርግ ተቋም በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ላይ አደረኩት ባለው ጥናት በቴሌቪዥን ዘርፍ ቃና ቴሌቪዥን ከፍተኛ የተመልካች ቁጥር ያለው እንደሆነ ይፋ አድርጓል። 32.5 ከመቶ ነጥብ በማግኝት። ቃና ቴሌቪዝን ኢትዮጵያውን ህጻናት እየሰለበና እያደነዘዘ ያለ ትውልድ ገዳይ ጣብያ ነው። ጣብያው ከውጭ ሃገር የሚሰራጭ ሲሆን ባለቤቱም የውጭ ዜጋ ነው። የህወሓት መንግሥ ጣብያው መዝጋት አይፈልግም።ሲጀመር ትውልድን ማምከን ዋነኛው አላማው ነው። ሲቀጥል የገንዝብ ጉዳይ ነው። ጣብያው ላለመዝጋት የቀረበው ምክንያትም የማያሳምን ነው። የሚያሰራጩት አካላት መብታቸው ነው ፤ ዲሞክራሲ ነው የሚል ነው። ዕድሜ ከሰጠን ይቺ ዲያብሎስን  ለመጥቀም ዲሞክራሲ የምትል ቃል መጠቀም የት እንደሚያደርሰን እናያለን። እኛው ግን ልጆችችን ኢትዮጵያዊነትን በመስበክ ከጥፋት ልንታደጋቸው ይገባል።


ማክሰኞ ጥር 8, 2010 ዓመተ ምሕረት
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment