ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እና ኢሉሙናቲ

ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ
የሀገረ ኢትዮጵያ 225ኛው ንጉሥ ኃይለሥላሴ በብዙ ሰዎች የኢሊሙናቲ አባል ተደርገው ይቆጠራሉ።ይህ የተሳሳተ ሃሳብ ከየኢሊሙናቶዎች(ሰላቢእጆች)ውስብስብነትና ሴራ የተነሳ ነው።ኢሊሙናቶዎች ትክክለኛው ማንነታቸው እንዳይታወቅባቸው የመረጃ ጦርነት(disinformation) በመፍጠር ማንነታቸውንና ሴራቸውን ለመደበቅና የተሳሳተ ሃሳብ በሕዝብ ላይ እንዲሰርጽ ያደርጋሉ።የዘመኑ የመረጃ መረብ(internet) በቁጥጥራቸው ስር መሆኑ ልብ ይበሉ።ቀዳማዊ ንጉሥ ሃጸይ ኃይለሥላሴ የነዚህ አካላት ሰለባ ሆነዋል።ምክንያቱም የእስራኤሉ ቅዱስ ዳዊት ስርወ መንግስት ያስቀጠሉና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የበላይ ጠባቂ(ተከላካይ እምነት) የኢሊሙናቲ ቀንደኛ ተቃዋሚ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረባቸው ንጉስ ስለነበሩ ነው። እውነቱ ለማወቅም ከፍተኛ ጥናትና ምርምር ይፈልጋል።የዘመኑ ፖለቲከኞች የስም ማጥፋትና ማጥላላት ተጨምሮበት ትውልዱ እውነትን እንዳያውቅ ተደርጓል።ብዙ መረጃዎችና ሰዎች ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የኢሊሙናቲ አባል ስለመሆናቸው የሚያቀርባቸው ምክንያቶችና ስህተታቸው እንገልጻለን።በብዛኛው ጊዜ የሚቀርበው ምክንያት ግርማዊ ቀዳማዊ ዐጼ ኃይለሥላሴ የሚያሳይዋት የእጅ ምልክት ነች።ይህንንም ባለማወቅና የሰይጣን አምላኪዎችን አካሄድ ባለመገንዘብ ትርጉሙ እንኳን ሳይረዱ(የተገለበጠ ፒራሚድ ነው ይላሉ) ከሰይጣናዊ አምልኮ ጋር ያያዙታል።ይህንንም ቀንደኛ የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ጠላት የሆኑትን ምዕራባውያን(የሰይጣን አምላኪዎች)ና አብዮቶኞች ነን የሚሉ የ አገራችን መንግስታት ንጉሠ ነገሥቱን ለማጣጣል ተጠቅመውበታል።ዳሩ ግን ግርማዊ ቀዳማዊ ዐጼ ኃይለሥላሴ የሚያሳዩት የእጅ ምልክት ትርጉሙ ስሉስ ቅዱስን(Holy Trinity)ይገልጻል። (የግርማዊ ቀዳማዊ ዐጼ ኃይለሥላሴ ድንቅ መንፈሳዊ ህይወት ክታች ያንብቡ) ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ የነጻ ግንበኞች-Freemason ማህበራት አባል እንደነበሩ የሚገልጹ መስረጃዎች አሉ።ሆኖም የነጻ ግንበኞች አባል መሆን ማለት የማህበሩ ድብቅና ሰይጣናዊ ተግባራትን መካፈል ማለት አይደለም።የፍሪማሶንሪ ማህበር አባላት በደረጃ() የተከፋፈለ ነው።ዝቅተኛው ደረጃ ላይ ያለ አባል በከፍተኛ ደረጃ ያሉ አባላት የሚፈጸሙ  ሰይጣናዊ አምልኮዎች አያውቅም።ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የማህበራቱ አባል የሆኑት የክብር አባልነትን በመቀበል ነበር።በተጨማሪም የጣልያን መንግስት በአድዋ ጦርነት በደረሰበት ሽንፈት ለመበቀል ከአመታት በኃላ ቅድስት ሃገራችን ኢትዮጵያን ቅኝ ለመግዛት በየዝያን ጊዜ የሮም ካቶሊክ 11ኛው ፖፕ ፓየስ በተባረከ የጦር ሰራዊት ስትወረርና ስትወጋ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሃገራችንን ከታሪካዊ ሽንፈት ለመታደግ ወደ ሃገረ እንግሊዝ ሄደዋል።የሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ሰላቢ እጆች ኢሊሙንናቲ ነች።በየእንግሊዝ ንጉሳዊ ቤተሰብም(የሰላቢ እጆች ኢሊሙናቲ የደም ሃረግ ናቸው) ድጋፍም ከየስድስት አመታት የሃገረ እንግሊዝ ቆይታ በኃላም ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል። በጣም የሚደንቀው ግርማዊ ቀዳማዊ ዐጼ ኃይለሥላሴ ሃገረ አሜሪካን በ 1963 የጎበኙ የመጀመርያው የአፍሪካ ንጉሥ ሲሆኑ በጉብኝታቸው ወቅት የሃገረ አሜሪካ ርዕሰ ብሔር ለነበሩት ጆን ኦፍ ኬኔዲን የኢሊሙናቲን ስዉርን ሴራ በመግለጽ እንዲቃወማቸውና እንዲያጋልጣቸው በነገሩት መሰረት ግርማዊ ቀዳማዊ ዐጼ ኃይለሥላሴ ወደ ሃገራቸው በተመለሱ በአምሳኛው(50ኛው) ቀን ርዕሰ ብሔሩ ጆን ኦፍ ኬኔዲ በአደባባይ የኢሊሙናቲን ሴራ በማጋለጡ በመኪናው ከሚስቱ ጋር ሲመለስ በሲ.አይ.ኤ (CIA)እጅ ተገድሏል።ሌላኛው የግርማዊ ቀዳማዊ ዐጼ ኃይለ ሥላሴ በጎ ነገር ደግሞ ራስተፈሪያን ፈጣርያቸውን ባለማወቅ የግርማዊ ቀዳማዊ ዐጼ ኃይለ ሥላሴን እንደ ፈጣርያቸው ማምለክ በጀመሩበት ጊዜ ኣቡነ ይስሕቅን ወደ ሃገረ ጃማይካ በመላክ ወንጌልን እንዲማሩና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ቤተ ክርስትያን በመመስረት ፈጣርያቸውን እንድያውቁና እሳቸው ፈጣሪ እንዳልሆኑ እንዲያውቁ አድርገዋል።ከዚ ጋር በተያያዘም አቡነ ይስሕቅን እውቁ የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኝ ቦብ ማርለይ እና መላው ቤተሰቡ በማጥመቅ ፈጣሪውን እንዲያውቅ አድርገዋል።ቦብ ማርለይ ከተጠመቀ በሃላ ለግማሽ ስዓት ድረስ ያለቀሰ ሲሆን ከሰባት ወር በሃላም ሂዎቱ ሊያልፍ ችሏል።(ጸሃፊው ቦብ የኢሊሙናቲ ሰለባ እንደሆነም ያምናል።) 

የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንፈሳዊ ህይወት
‹‹ግርማዊነታቸው ሃይማኖተ ጹኑ፣አርቆ አስተዋይና ታላቅ የሰላም አባት ነበሩ።የመንፈሳዊ ሕይወታቸው ጽናት ምእመናንና ምእመናት በሃይማኖታቸው እንዲጠነክሩ ከማድረጉም በላይ በእህት ኦርየንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያናት ዘንድየሃይማኖት ጋሻ፣ብቸኛ ኦርተዶክሳዊ ንጉሰ ነገስትእየተባሉ እንዲጠሩ አስችሏል።የሃገርንና የታሪክን ሃላፊነት በብቃት በመወጣት ኢትዮጵያ ለደረሰችበት ዘመናዊ ሥልጣኔ የእድገት ምዕራፍ ከፋችና መስራች ሆነዋል።ማንም እንደሚረዳው በዓይን የሚታዩ፣በእጅ የሚዳሰሱ ታላላቅ ስራዎች አከናውነዋል።ኢትዮጵያ ሃገራችን ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያናችንና ተዋህዶ እምነታችን በመላው አለም በበለጠ እውቅና እንዲያገኙና ተገቢውን የክብር ስፍራ እንዲይዙ ያልተቆጠበ ጥረት አድርገዋል።የሁሉንም ድካም በከንቱ የማያስቀር እግዚአብሔር በበጎ ሥራቸው ዋጋቸውን እንደሚከፍላቸው እናምናለን።ሁሉም ክርስትያኖች በጸሎት ያስቧቸዋል።በተለይ ቤተ ክርስትያናችን ዘወትር በጸሎት ስታስባቸው ትኖራለች።››---አባ ጳውሎስ

ግርማዊ ቀዳማዊ ዐጼ ኃይለሥላሴ እናታቸው ወ/ሮ የሺ እመቤት በተወለዱ በሁለት ዕድምያቸው፣አባታቸው ልዑል ራስ መኮንንም በተወለዱ በ፲፫ ዓመት ዕድምያቸው ሙተውባቸው ምንም እንኳን በሰው ሰው ያደጉ የሙት ልጅ ቢሆንም ከእርሳቸው በፊት እናታቸው ወ/ሮ የሺ የወለዷቸው ልጆች በተከታታይ ስለሞቱባቸው ግርማዊነትቸው የሞት ማክተምያ ናቸው።በዩሐንስ ልደት ወላጆቹም ሆኑ ብዙዎች እንደተደሰቱ ሁሉ የግርማዊነታቸው ልደት ለወላጆቻቸውና ለብዙዎች ታላቅ ደስታ ስለነበረ በተወለዱ ጊዜ ከንጉሰ ነገስት ዐጼ ምኒልክ ጀምሮ ከየመኳንንቱና ከየመሳፍንቱ እንዲሁም ከአከባቢው  ባላባቶችና ነዋሪዎች ብዙ እጅ መንሻ ቀርቦላቸዋል።

የግርማዊ ቀዳማዊ ዐጼ ኃይለ ሥላሴ ታሪከ ልደት በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል መልአካዊ አንደበት ነቢየ ልዑል ዐርከ መርዓዊ ተብሎ ከተሰየመው ከታሪክ ልደት ዩሐንስ ጋር በብዙ መልኩ ይመሳሰላል።የነቢየ ልዑል ዩሐንስ እናትና ኣባት ኤልሳቤጥና ዘካርያስ አምልኮተ እግዚአብሔር የጸኑ፣በጾምና በጸሎት፣በምጽዋትና በስግደት የተወሰኑ በጠቅላላምውም መንገዳቸውን ሁሉ በእግዚአብሔር ሕግና ትእዛዝ ያደረጉ ከኃጢአት የራቁ ጻድቃን ወይም ደጋግ ሰዎች እንደ ነበሩ ሁሉ የግርማዊ ቀዳማዊ ዐጼ ኃይለ ሥላሴ ወላጆችም ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤልና ወ/ሮ የሺ እመቤትም በሕገ እግዚአብሔር የጸኑ፣በጾምና በጸሎት፣ በምጽዋትና በስግደት ተወስነው የእግዚአብሔርን ሕግና ትእዛዝ ጠብቀው የሚኖሩ ደጋግ ክርስትያኖች ነበሩ።

የነቢየ ልዑል ዩሐንስ አባት ካህነ ኦሪት ዘካርያስ በቤተ መቅደስ በጸሎት ላይ እንዳለ ጸሎቱ ተሰምቶለት ሚስቱ ኤልሳቤጥ ዩሐንስን እንደምትወልድለት፣በተወለደዉም  ሕፃን ልደት እናትና አባቱም ሆኑ ብዙዎቹ እንደሚደሰቱ፣በእግዚአብሔርም ፊት ትልቅ ሰው እንደሚሆን ከእናቱ ማህጸን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ እንደሚሞላበት፣ብዙሔ የእሥራኤል ልጆችም ወደ ሕገ እግዚአብሔር እንደሚመልስ፣የ አባቶችን ልብ ወደ ልጆች የከሀድያንንም ህሊና ወደ ጻድቃን ህሊና አእምሮ ይመልስ ዘንድ ጉዞውን በመንፈስ ቅዱስ በኃይለ ኤልያስ እንደሚያደርግ፣ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ሕግ እንደሚሰራና ሕዝቦችንም እግዚአብሔርን ለመቀበል እንደሚያዘጋጅ ብሥራታዊው መልአከ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ታዞ በትንቢታዊ ቃል ነግሮት ነበር፣(ሉቃስ ፩ ፥፲፫-፲፰)

ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ትምህርቱ ‹‹እሱ ከነብያት ሁሉ ይበልጣል፣እነሆ እሱ መንገድህን በፊት የሚጠርግ መልእክተኛዮን እልካለሁ፣ተብሎ የተጻፈለት እሱ ነውና በእውነት እላችሃለው ከሴቶች ከተወለዱ ልጆች ከዩሐንስ መጥምቅ የሚበልጥ አልተነሳም፣ከመጥምቁ ዩሐንስ መነሳት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ መንግስተ ሰማያት ትገፋለች፣የተገፉም  ይቀማሟታል(ይቀራመቷታል)፣ኦሪትም ነብያትም ሁሉ እስከ ዩሐንስ ድረስ ተንብየዋልልና፣ልትቀበሉት ከፈቀዳችሁስ(ከወደዳችሁስ)ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ እሱ ነውና።›› (ማቴ ፲፩፥፱፡፲፬)በማለት ተናግሮታል።

ግርማዊ ቀዳማዊ ዐጼ ኃይለ ሥላሴ  ሃገራቸው ኢትዮጵያ በፋሽስት ኢጣልያ በተወረረችበት ወቅት ጄኔቫ ላይ በዓለም መንግስታት ፊት ባሰሙት ታሪካዊ ንግግር ‹‹ዛሬ በኢትዮጵያ ላይ የተጫረው ክብሪት(የነደደው እሳት)በዓለም ላይ ሳይጫር አይቀርም፣ታሪክና እግዚአብሔር ፍርዳችሁን ይጠብቁታል።›› በማለት የተናገሩት ንጉሳዊ ቃለ ትንቢት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተፈጽሟል፣ግርማዊነታቸው በሁሉም 
መስክ ለኢትዮጵያ እድገትና ልማት መንገድ ጠራጊ በመሆን ከእግዚአብሔር የተላኩ ነበሩ ለማለት ያስደፍራል።
በአጠቃላይ ቀዳማዊ ዐጼ ኃይለ ሥላሴ  ለሃገራችን ለኢትዮጵያ በተለይም ለጥንታዊቷ፣ታሪካዊቷና ለብሔራዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ሁለተኛ ካሳቴ ብርሃን ሰላማ ነበሩ ማለት ብለን ብንናገር በፍቃደ እግዚአብሔር ተመርጠውና ተቀብተው ከነገሱበት ወይም ሥዩመ እግዚአብሔር ተብለው በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዙፋን ከተቀመጡበት ጊዜ ጀምሮ በመንፈሳዊው ሆነ በሥጋዊው ያከናወኑት ተግባር ዋቢ ሁኖ ሊቀርብልን ይችላል።

ግርማዊ ቀዳማዊ ዐጼ ኃይለ ሥላሴ  በሕፃንነታቸው ወራት ይታይባቸው የነበረው ብሩህ ተስፋ በነገስታቱ፣በመሳፍንቱ፣በመኳንንቱ፣በቤተ ክርስትያን አባቶችና በዘመኑ በነበሩ ታላላቅ ሰዎች ጭምር ስለ ኢትዮጵያና ስለ ህዝቦቿ የወደፊት አለኝታነታቸው ብዙ ተልብሏል፣ብዙም ተነግሯል።

የግርማዊ ቀዳማዊ ዐጼ ኃይለሥላሴ  ዕድል በእግዚአብሔር እጅ ስለመሆኑና ስለወደፊቱ ታላቅነታቸው በአካልም በማዕርግም ያሳደጓቸው አባታቸው ንጉሰ ነገስት ዐጼ ምኒሊክ በሕጻንነታቸው ወራት እንዲህ ሲሉ ተነብየውላቸው ነበር።‹‹እንደንስር አሞራ ከፍ ያለ መንፈስ ይዘህ የምትገኝ አንተ ነህ›› የሚለውን ቃለ ትንቢት በሕፃንነታቸው ወራት በ አንድ ወቅት የተናገሪላችው ሲሆን በሌላ ወቅት ደግሞ በ ፲፫ ዓመት ዕድሜያቸው ደጃዝማች ብለው በሾሙአቸው ጊዜ መኳንንቶቻቸውን ሰብስበው እንዲህ ብለውላቸዋል።‹‹ሁላችሁም ያሳደግሃቹና የምወዳቹ አሽከሮቼ ናችሁ፣ልጄን ተፈሪን ከእግዚአብሔር ጋር አደራ ብዮአች አለሁ፣አደራም የምላችሁም ለዓይናችሁ እንዳትጠሉት ነው እንጂ ዕድሉ በፈጣሪ እጅ ነው።›› በማለት ግርማዊነታቸው ከሕፃንነታቸው ጀምሮ አምላካዊ ጸጋን የተጎናጸፉ መሆናቸውን የወደፊት ብሩህ ተስፋቸውን ተናግርዋል።ግርማዊ ቀዳማዊ ዐጼ ኃይለሥላሴ ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና ከተቀበሉበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ ከመንፈሳዊ ሕይወት ተለይተው አያውቁም።ንጉሰ ነገስት ከሆኑ በሃላም እነ አለቃ ገብረ መድህን የመሳሰሉ የ አብነት መምህራን በቤተ መንግስታቸው በማሰባሰብ ሰርክ ህብስት በመፍቀድ ወይም ልብስና ጉርስ በመስጠት የቅዱሳት መፃሕፍት ትርጓሜንና የቅኔን ትምህርት በሚገባ ተምረዋል።ግርማዊነታቸው ረቂቅ ሰውነት ከልጅነት እስከ ዕውቀት በዚህ ዓይነቱ መንፈሳዊ ሕይወት የተገነባ ስለሆነ የዕለታዊ ሥራቸው ሁሉ መጀመርያ ወደ ቤተ ክርስትያን ሔደው ጸሎት ማቅረብ ነበር፣በ አዲስ አበባና አከባቢዋ በሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ዓመታዊ በዓለ ንግሥ የሚከበረው ብዙውን ጊዜ ግርማዊነታቸው በሚገኙበት ነበር።በየወር በዓላቱም በ አዘቦቱም ቀን ወደ ቤተ ክርስትያን እየሄዱ  ማስቀደስ መጸለይ ትምህርተ ወንጌል መስማት፣ልዑላኑ፣ልዕልታቱ፣መኳንቱና መሳፍንቱ አብረው እየሔዱ እንዲያስቀድሱና እንዲጸልዩ።ትምህርተ ወንጌል እንዲሰሙ ማድረግ ወይም መንፈሳዊ ግዴታቸው እንዲወጡ ማድረግ ከንጉሠ ነገስቱ የዕለት ተግባራቸው አንዱ ነበር። 

ይህ ብቻ አይደለም በየዓመቱ በጾመ ፍልሰታ ሱባዔ ወቅት ድሬዳዋ እየወረዱ የውዳሴ ማርያምና የቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ መስማትም አስተጓጉለው አያውቁም ነበር።ለስብሰባና ለሥራ ጉብኝት ወደ ልዩ ልዩ ክፍለ ዓለማት በሚሔድበትም ጊዜ በቅድምያ ወደ ኢትዮያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ በመሔድ ቡራኬ ተቀብለውና ወደ ቤተ ክርስትያን በመድረስ የአትርሱኝ ጸሎት አጸልየው ነበር ጉዞአቸው የሚጀምሩት፣ሲመለሱም በቤተ ክርስትያን ተገኝተው የምስጋና ጸሎት ያቀርቡ ነበር።
ግርማዊ ቀዳማዊ ዐጼ ኃይለሥላሴ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ያደረጉት መንፈሳዊ አስተዋጽኦ እንዘረዝራለን።

፩.እምነትንና ታሪክን አዋሕደው የያዙት የጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ጥንታውያን የብራና መጻሕፍት ደብዛቸው እንዳይጠፋና ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ያደርጉት በነበረው ከፍተኛ ጥረት ከ አልጋ ወራሽነታቸው ዘመን ጀምሮ መጻሕፍትን ከየቦታው በማሰባሰብ በዘመናዊ ሕትመት እንዲባዙ ያደርጉ እንደ ነበር።

፪.አያሌ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስትያናት እንዳሳነጹ፣በዘመን ርዝመት ጉስቁልና የደረሰባቸውንም፣አብያተ ክርስትያናት እንዳሳነጹ።ግርማዊ ቀዳማዊ ዐጼ ኃይለ ሥላሴ  አብያተ ክርስትያናት ማሳነጽ የጀመሩት ገና ፲፰ አመታቸው መስፍነ ሐረር ከነበሩበት ጊዜ አንስቶ ነው።እግዚአብሔር ለሐገርና ለቤተ ክርስትያን አገልጉሎት የመረጣቸው ከልጅነታቸው ጀምሮ ስለሆነ ነው።
፫.የኢትዮጵያ ኦትርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ለመጀመርያ ጊዜ የራስዋ ፓትርያርክ እንዲኖራት አድርገዋል።ከዛ በፊት ግን ፓትርያርክ የሚሾምላት ከግብጽ ቤተ ክርስትያን ነበር።

፬.አክሱም ጽዮን የኢትዮጵያ ቅድስት ከተማ ናት።የኦሪትም ሆነ የክርስትና ሃይማኖት የገባው በዚች ከተማ በኩል ነው።በዚህም ምክንያት ነገስታት ሁሉ አክብረዋታል።ሕጓንና ሥርዓቷን ጠብቀውላት ኖረዋል።ሲያያዝ በመጣው ታሪክ እንደሚገኝው በቀዳማዊ ምኒሊክ ዘመን የመጣቺው ታቦተ ጽዮን በጥንቱ ዘመን በአክሱም አቅራቢያ በሚገኝ ቦታ በምኩራበ ኦሪት ነበረች።ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ ከገባ በሃላ ግን አብርሃና አጽበሃ የመጀመራይዩቱ ቤተ ክርስትያን አሳነጹ።ይህች ቤተ ክርስትያን ፲፪ የመቅደስ ክፍሎች እንደነበሯት ይነገራል።ከዚያ ወዲህ አክሱም በተደጋጋሚ ፈርሳ በተደጋጋሚ ታንጻለች።አሁን ያለው ቤተ ክርስትያን ያሰሩት ግርማዊ ቀዳማዊ ዐጼ ኃይለሥላሴ ናቸው።የመሰረቱ ድንጋይ መስከረም ፲፪ ቀን ፲፱፻፵፭ አኖሩ። መጽሓፉ እንደገለጽዉም‹‹ከወገብህ የሚወጣውን ዘርህን ከአንተ በሃላ አስነሳለሁ እርሱ ለስሜ ቤት ይሰራል።›› (--፪ኛሳሙ ፯፥፲፪፡፩፫)

ለአስረጅ ያህል ከረጅሙ በአጭሩ ይህን ጠቀስኩ እንጂ ስለ ንጉሥ ነገስቱ መንፈሳዊ ሕይወት ብዙ ነገር መጻፍ ይቻላል።ሆኖም    መንፈሳዊነትንና ህልወተ እግዚአብሔርን የሚክዱና ታሪክን በስጋዊ ፍላጎት በማሳሳት ትውልዱን በአብዮታዊነት የሚመሩት መንግስታት እውነትን አዛብተውል።

የኃላ ከሌለ የለም የፊቱ!

















Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment