የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝንደንት ዶናልድ ትራምፕ፤ "ሃይማኖት እና ክርስትና ከአሜሪካ የጎደሉት ትልልቅ ነገሮች ናቸው "

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

አሜሪካን እንደገና እንድትጸልይ እናድርጋት!

ትራምፕ በማህበራዊ ሚዲያው 'Truth Social' በተለጠፈው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ “ከዚህች ሀገር የጎደሉት ትልልቅ ነገሮች ሃይማኖት እና ክርስትና ናቸው፣ እና እነሱን መመለስ እንዳለብን በእውነት አምናለሁ” ብለዋል። "ይህ እኛን ከገጠሙን ትልቅ ችግሮች መካከል አንዱ ነው፣ ለዛም ነው ሀገራችን ከቁጥጥር ውጪ እየሄደች ያለችው፣ በሀገራችን ሃይማኖትን አጥተናልና። ሁሉም አሜሪካውያን መጽሐፍ ቅዱስ በቤታቸው ያስፈልጋቸዋል፣ እኔም ብዙ አለኝ። የምወደው መጽሐፍ ነው። የብዙ ሰዎች ተወዳጅ መጽሐፍም ነው። መስራች አባቶቻችን አሜሪካን በይሁዲ-ክርስቲያን እሴቶች ሲገነቡ ትልቅ ነገር አድርገዋል። አሁን ያ መሠረት ምናልባት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየተጠቃ ነው። አሜሪካ እንደገና እንድትጸልይ እናድርግ "

❖ ታቦተ ጽዮን ሥራውን እየሠራ ነው!

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment