ሐዋርያው ማርቆስን የመሰለ መምሕር ያስገኘች ኢትዮጵያ ናት

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለም ላይ ካሰማራቸው ሐዋርያት መካከል ሐዋርያው ማርቆስ አንዱ ነው
ሐዋርያው ማርቆስን የመሰለ መምሕር ያስገኘች ኢትዮጵያ ናት
ሐዋርያው ማርቆስን በሚመለከት መሪራስ አማን በላይ “ሐዋርያው ማርቆስ ዜግነቱ ሮማያዊ ሲሆን፡ ትውልዱ ኢትዮጵያዊ ነው። በዚያን ጊዜ ግብጾች ቦታ አልነበራቸውም ሲሉ ተናግረዋል። ሐዋርያው ማርቆስ ቤተሰቦቹ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ ነዋሪነታቸው ግብጽና ኢየሩሳሌም እንደነበረ በታሪክ ተጠቅሷል።

አባ ተስፋ ሥላሴ ሞገስ፡ ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው መድኃኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የይሁዳ አንበሳ ነው ሲሉ መጽሐፍ ጽፈዋል። ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው መድኃኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የይሁዳ አንበሳ ነው የተባለው መጽሐፍ ገጽ 100 ላይ “ማርቆስ ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊ ነው” ሲሉ ጽፈዋል። እኒህ አባት ሐዋርያው ማርቆስን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሐዋርያት ኢትዮጵያዊ ደም ያላቸው መሆናቸውን በማመለከት ከፍ ተብሎ በተጠቀሰው መጽሐፍ ገጽ 42 ላይ፡ “ከኢትዮጵያውያን ዘር የሚወለደው ፊልጶስም ነው” ሲሉ ሁለቱ ሐዋርያት ከጌታችን ጋር ያደረጉትን የቃላት ልውውጥ በሚመለከት ጽፈዋል።
ከዚህ ላይ ማየት ያለብን እነዚህ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ቀድሞ ጀምረው ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉና ለክብር የማይሮጡ በመሆናቸው ማንነታቸው ሊታወቅ አልቻለም። እንኳን ቀድሞ በቅርቡ የዳ/ዊ አጤ ቴዎድሮስን ታሪክ የፃፉት አንዱ ደራሲ መጽሐፉን የዘመኑ የታሪክ ሊቃውንቶችን ጥቅስ ለመውሰድ ሲሉ “የማይታወቀው ደራሲ” እንደጻፈው እየተባለ ነው የሚጠቀሰው። የጥንት ኢትዮጵያውያን “እወቁልን” የማይሉ በመሆናቸው ብዙ የታሪክ አባቶቻችን ስምና ታሪክ ተደብቆ ቀርቷል። በዚህ ባለንበት አገር አሉ ከሚባሉት ሊቆች መካከል ለአንዱ የሊቀ–ጠበብት ማዕረግ ዩኒቨርስቲው ሲሰጣቸው አስተዳዳሪው ለተሰብሳቢው እንግዳ እንዲህ ብለው ነበር፦
ኢትዮጵያውያን ይህን ሰርተናል የማይሉ በስራቸው እንጂ ለወረቀት የማይጓጉ በመሆናቸው ይህ ዶ/ር እገሌ እንደሌሎች ዶክተሮች ማመልከቻ ይዞ ወደ ጽሕፈት ቤቱ መጥቶ አስቸግሮኝ አያውቅም። የስራውን ጥራትና ብቃት ዩኒቨርስቲው በማየቱ የሌቀ–ጠበብት ማዕረግ ሰጥቶታል” ብለዋል።
ትቤ አክሱም ገጽ 67 “ቅዱስ ማርቆስም ያባቱን ሀገር አስቀድሞም ያውቀው ስለነበረ መጥቶ እንዳስተማረ” ሲሉ ጽፈዋል። ከዚህ ላይ የኢትዮጵያውያን ከቀድሞ ጀምሮ የመጣው ታሪክ የሚያመለክተው ለክርስትና ሃይማኖት ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረጋቸውን ነው። ሐዋርያው ማርቆስን የመሰለ መምሕር ያስገኘች ኢትዮጵያ ናት። ላይ እንደተጠቀሰው ዛሬ ድረስ በህይወት ያሉ ደራሲያን ኮሎኔልነታቸውን፣ ጠበብትነታቸውን ወይም ሊቅነታቸውን ሳይጠቅሱ መጽሐፍ የጻፉ ደራሲያን ነበሩ። ምክኒያቱም ኢትዮጵያውያን አብዛኛው እወቁኝ የማይሉ ናቸው። በዚህ ምክንያት ከቀድሞ ጀምሮ ተያይዞ በመምጣቱ ሐዋርያው ማርቆስ ኢትዮጵያዊ መሆኑ ሳይታወቅ ኖሮ ነበር።
መሪራስ አማን በላይ፡ “ጉግሣ” መጽሔት ቅጽ ቁጥር መጋቢት 1993 .ገጽ 17 ላይ “የማርቆስን አክስት ማለት የበርናባስንና የአርስጦሎስን እህት ጴጥሮስን አግብቶ ነበር። እንዲሁሙ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የቤተ እስራኤል የሌዊና የይሑዳ ነገድ የሆነ ወደ ቀሬና ቀራኒዮ ወደ ቤተ መቅደስ ሊሰግድ መጥቶ ስሙም ስምዖን ይባል ነበር። በበነጋታው ከአባቱና ከናቱ ዘመድ ከስምዖን ጋር ማርቆስ የጌታችንን የክርስቶስን ግርፋትና ሕማማቱን እየተከተለ ተምልክቷል። አጎቱንም የአባቱን ዘመድ ኢትዮጵያዊ ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው የጌታን መስቀል እንዲሸከም አይሁዳ ሊያስገድዱት አይቷል ተመልክቷል” ሲሉ ጽፈዋል። ስምዖን ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥበት ምክንያት ስምዖን ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥበት ምክንያት ስምዖን ጥቁር መሆኑን በሌሎችም ታሪክ ታውቋል።
ሐዋርያው ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ስለሆነና ታሪኩን ስላወቁ ቀዳማዊ አጤ ኃይለ ሥላሴ አጽሙ አጽሙ ቬነስ ግዛት ከተማ ከሚቀር ግብጽ መግባት ይኖርበታል ብለው ከቬነስ መንግሥትና ቤተ ክርስቲያን ጋር ያደረጉት ጥረት ቀላል አይደለም። ቀደም ሲል ግብጾች ሊያስመልሱ ያልቻሉትን አጤ ኃይለ ሥላሴ በጥረታቸው የቅዱስ ሐዋርያው ማርቆስ አጽም ወደ አፍሪቃዋ ግብጽ እንዲገባ ሆነ። ይህ ታሪክ በመሆኑ ሊገለጽ የሚገባው ሲሆን፡ ጃንሆይ መሠረት ያደረጉት ዋናው ነጥብ ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ በዘሩ ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ነው።
የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩንን ዋኖቻችንን እናስብ፤ ከብቶች በሚሰማሩበት ሜዳ እንደ ወይፈን በገመድ አሥረው ለጐተቱት ለማርያም ልጅ ማርቆስ ሰላምታ ይገባል፤ በእሳት ነበልባል ሊያቃጥሉት በወደዱ ጊዜ ዝናብና ውርጭ ነዲዱን አጠፉት መብረቅም በድኑን ጋረዳት።
የድንግል ማርያም ልጅ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለው የቅዱስ ማርቆስ ጸሎቱና በረከቱ በሕዝበ ክርስቲያንና በሀገራችን በኢትዮጵያ ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፡ አሜን!
እንኳን አደረሰን!!!

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment