ሉሲፈራውያኑ ፩ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በተለያዮ መገናኛ ዘዴያቸው ስለ ጽላተ ሙሴ ፅፈዋል!

ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

ሉሲፈራውያኑ ፩ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በተለያዮ መገናኛ ዘዴያቸው ስለ ጽላተ ሙሴ ፅፈዎል። Is the Ark of the Covenant in Ethiopia? / “ጽላተ ሙሴ በኢትዮጵያ ነውን?” በሚል ርዕስ “ ዘ ደይሊ ቢስት / የየዕለቱ አውሬ ” የተሰኘው አሜሪካዊ ተወዳጅ የዜናዎችና አስተያየቶች ኅዋ ሰሌዳ ሰፊ ዘገባ ከሦስት ቀናት በፊት አቅርቦ ነበር። ሴት ጋዜጠኛዋን፡ ትታዘብና ይታዘቡን ዘንድ፡ ሴቶች መግባት ወደ ማይፈቀዱባቸው የሀገራችን ቅዱሳት ገዳማት መላካቸው ለተንኮል ቢሆንም፤ እውነት ሲመሰክሩ ደስ ሊለን ይገባል። የአውሬውም መልዕክተኛ ያየችውን በከፊል እንደሚከተለው ዘግባለች፦
“ኢትዮጵያ በ ኅይማኖታዊ ትዕይንት የተሞላች አገር ናት፤ በላሊበላ፣ አክሱም እና ጎንደር እሁድ እሁድ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሴትና ወንድ መነኮሳት፣ ደብተራዎችና ነጋዴዎች፣ ብርቱ ሕፃናትና አረጋውያን፡ ነጭ ወይም ብርቱካንማ ቀለም ያላቸውን ልብሶቻቸውን በመልበስ በየዓብያተ ክርስቲያናቱ ተሰባስበውና የአካባቢውንም ገጽታ አሳምረውት ይታያሉ።

በመላው ዓለም ካየኋቸው ሕዝቦች ሁሉ እንደ ኢትዮጵያውያን ያለ በጥልቁ መንፈሳዊ የሆነ ሕዝብ ገጥሞኝ አያውቅም – አምልኮተ እግዚአብሔር በሁሉም የሕይወት ገጽታ ላይ ይንጸባረቃል። እናም በጉዞዬ ወቅት ግልጽ የሆነልኝ አንድ ነገር፡ ቤተክርስቲያኗ ለጽላተ ሙሴ የምትሰጠው ክብር የተወለደው ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር ዘንድ የቃል ኪዳኑ ታቦት የመጨረሻ ማረፊያ ቦታ እንድትሆን በመመረጧ ነው።” በማለት ምሥክርነትዎ ሰጥታለች።

በቅርቡ የእንግሊዙም “ ደይሊ ኤክስፕረስ ” ጽላቱን በተመለከተ ጉዳይ ተልካሻ ዜና ይዞ ቀርቦ ነበር… እንግዲህ በአሁኑ ሰዓት ሁሉም፡ በተለይ ከአውሬው የሆኑት ሁሉ ዓይኖቻቸውን በ ቅዱስ ታቦቱና በ አክሱም ጽዮን ላይ አሳርፈዋል…ከዚህ ጀርባ ብዙ ተንኮል እንዳለ አንጠራጠር።

ለማንኛውም፡ በተለይ እኛ ኢትዮጵያውያን፡ አውሬው ሳይቀር የመሰከርልንን፡ እና ቸሩ እግዚአብሔር የሰጠንን ይህን ትልቅ ጸጋ በቀላሉ ባንመለከተውና ቅድሚያ ብንሰጠው ለራሳችን በጎ ነገር ከማድረግ ተርፈን ለቀረው ዓለም ሳይቀር ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማበርከት እንችላለን።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment