"የክርስቶስ ተቃዋሚ፡ አሁን የተስፋፉትን ዘመናዊ ስልኮችን ወይም ስማርት ስልኮችን ለመጥለፍ የሚያስችለው የኤሌክትሮኒክ መሣሪያ አጠቃቀም ስልት በጣም ሰፊ ነው።"

ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ኪሪል የግና በዓልን በማስመልከት ከሩሲያ ቴሌቪዥን ጋር በተደረገ አንድ ቃለ ምልልስ ላይ የሚከተለውን ተናግረዋል፦
"የክርስቶስ ተቃዋሚ፡ አሁን የተስፋፉትን ዘመናዊ ስልኮችን ወይም ስማርት ስልኮችን ለመጥለፍ የሚያስችለው የኤሌክትሮኒክ መሣሪያ አጠቃቀም ስልት በጣም ሰፊ ነው።"
ቤተክርስቲያኗ የቴክኖሎጂ ዕድገትንአትቃወምም፥ ነገር ግን በኢንተርኔት የተገናኙ መሳሪያዎች "ለሰው ዘር ሁሉ ዓለም አቀፍ ቁጥጥር" ማድረግየሚችሉበትን ሁኔታ ፈጥረዋል።

ሰዎች በትክክል የት እንዳሉ፣ ምንእንደሚፈልጉ፣ ምን እንደሚፈሩተከታያቾቻቸው እንዲያውቁ ያስችላቸዋል።

እንዲህ ያለው የመቆጣጠሪያ መንገድ፡ፀረ-ክርስቶሱ ከአንድ ቦታ ሆኖ አስቀድሞ እንዲመለከት ይረዳዋል።

ፀረ-ክርስቶሱ የሰውን ዘር ሁሉ የሚቆጣጠር ዓለም አቀፋዊ መሪ ይሆናል። ይህም ማለት ይህን መሰ የቴክኖሎጂ መዋቅር እራሱ አደጋን ያመጣል ማለት ነው።
የአለም ፍጻሜን ቶሎ ለማድረስካልፈለግን በቀር ነገሮች በአንድ ማዕከላዊ በሆነ ቦታ ቁጥጥር ሥር መውደቅ የለባቸውም፤ ማዕከላዊ ሆኖ የሚንቀሳቀስ ነገር መጥፋት አለበት።” ብለዋል።
ፓትርያርክ ኪሪል ብልህ የሆነ እና በጣም ጠቃሚ የሆነ መልዕክት ነው ያስተላለፉልን። በተለይ ሕፃናት ከስማርት ስልኮች መራቅ ይኖርባቸዋል። አሁን እንኳን ምዕራባውያኑ ሕፃናት በስማርት ስልክ ሳቢያ ዓይኖቻቸው ክፉኛ እየተጎዱ ነው።
ከጥቂት ዓመታት በፊት እነ ቢል ጌትስ ከወስላታው ኮፊ አናን ጋር በማበር ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሕፃን አንድ ላፕቶፕ እንሰጣልን” ( One Laptop Per Child) ሲሉ፡ “ኡ! ኡ! አውሬው ሕፃናቶቻችንን ሊቆጣጠር ይሻል!” በማለት ስጋቴን ገልጬ ነበር።
ስለ ፀረ-ክርስቶሱ፡ ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስጠንቀቂያዎች ፩ኛ የዮሐንስን ጨምሮ በሌሎችምመጻሕፍት ውስጥ እናገኛለን፦
፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፪፥፲፰ እንዲህ ይላል፦
"ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን።"
"ውድ ልጆች ሆይ, ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው; የክርስቶስ ተቃዋሚ እንደሚመጣ እንደ ሰማችሁ መጠን አሁንም ብዙዎቹ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች መጥተዋል።
ኢትዮጵያ አገራችንንም በጥቂቱ ላለፉት50 ዓመታት እየመሩ ያሉት ፀረ-ክርስቶሶቹ ናቸው። ለመሆኑ ዶ/ር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት መቆጣጠሪያ ባለሥልጣንን የገነቡ ግለሰብ መሆናቸውን እናውቅ ነበርን? ታዋቂው የስዊዘርላንድ ጋዜጣNZZ ይህን በማስመልከት ከሁለት ወራት በፊት በሰፊው አትቶ ነበር።
በሌላ በኩል የ ጉግል ተቋምና የአሜሪካ ኤምባሲ፡ በልማት እና ስራ ፈጠራ ስም፡ ወንጀላዊ የኢንተርኔት ጠለፋና ፕሮፓጋንዳን የተመለከተ ሥልጠና በአሜሪካ ኢምባሲ በኩል ለኢትዮጵያውያን እንደሚሰጡ ባለፈው ኅዳር ላይ ተገልጾ ነበር።
በአገራችን ላይ እየተካሄደ ያለው ፀረ-ክርስቶሳዊ ድራማ በቅደም ተከተል ነው በደንብ የተቀነባበረው። ነገሮች ሁሉ ወዴት እያመሩ እንደሆነ እያየን ነው።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment