✍ መስከረም ለቺሳ (ዶ/ር) | ዮቶጵያ
አንተ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት ሆይ!
ላንተ ገለልተኛ እንዲያውም ኦርቶዶክስ የሚመስሉህ ነገር ግን ጥልቅ ፀረ ተዋሕዶ ጥላቻና ዒላማ ያላቸው መናፍቃንና አሕዛብ ፖለቲከኞች የኾኑ ምሑራን፣ የስነ ጽሑፍ ሰዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የታሪክ ተመራማሪዎች፣ ደራሲዎች፣ መጣጥፍና መነባንብ አቅራቢዎች፣ ኮሜድያኖች፥ የድርጅት ሥራ አስኪያጆች፣ አንባቢዎችና ፈላስፎች፣ ኹሉን አቃፊ የሚመስሉ የሶሻል ሚድያ ዜናና ወሬ አቅራቢዎች፣ በየራድዮው የምትሰማቸው መዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጆች፥ ወዘተ... ለረዥም ጊዜ በአእምሮህ ሲስሉብህ የኖሩት አንተና መሰሎችህ ኦርቶዶክሶች እና አባቶቻችሁ ሰው ስትገድሉ እንደኖራችሁ፥ ስትረግጡና ስትበድሉ፣ ስታፍኑ እንደኖራችሁ፣ ፈላሻውንና ሙስሊሙን፣ ካቶሊኩንና ጴንጤውን ስታሳድዱ እንደኖራችሁ፣ አሁንም በደማችሁ ያ ዝንባሌ እንዳለ፣ ኹሉንም በግድ ኦርቶዶክስ ለማድረግ ስትጫኑ እንደኖራችሁ፣ ረጋጭ እና ጨቋኝ ባሕሪ እንዳላችሁ፥ ሌላው ቀርቶ፡ ለእምነታችሁ እንኳ የምትቆረቆሩት፡ በመኃይምነትና በድንቁርና ምኑንም ሳታውቁትና እግዚአብሔርን ሳትወድዱት እንደኾነ አድርገው፡ በቀልድም በቁም ነገርም ሲነግሩህና በገዛ እምነትህ ላይ እምነት እንድታጣ፥ ኃይል ያለውም እንዳይመስልህ ሲሠሩ ነው የኖሩት።
ስለዚህ፡ አሁን ያንን ለማካካስ፡ ለስላሳ፣ ቅልስልስ መኾን እንዳለብህ፥ የሌላ እምነት ተከታዮችን ለማባበልና ለማስደሰት፡ የራስህን እምነት ጠንካራ አገልጋዮችን እንድትነቅፍ፥ "አክራሪ ናቸው" ብለህ እንድትወቅስ፥ ከኹሉም በላይ ደግሞ፡ የኹሉም እምነት ተከታዮች approval ያልሰጡትን የራስህን አገልጋይ እንዳትቀበልና የእውነተኛ መምህር/አገልጋይ መለኪያው ኹሉንም እምነቶች የሚወድና የሚቀበል መኾን እንዳለበት እንድታምን፥ እውነተኛ የሃይማኖት ሰው ማለትም ለኹሉም ሃይማኖቶች ጥቅም እኩል የሚሠራ እንደኾነ እንዲመስልህ አድርገው፡ የተልመጠመጠ መሥፈርት በየአጋጣሚው አእምሮህ ውስጥ ጠቅጥቀውብሃል። ያንን ለማውጣት በጣም ከብዶሃል። አሁን "ኦርቶዶክሳውያን በእምነታቸው ተለይተው እየተገደሉ ነው" ስትባል፡ ለራስህ እምነት መቆም ተሥኖሃል። "ኃጢአት ነው" ብለው ሲነግሩህ ኖረዋላ! "ወገንተኝነት ነው" ብለው ሲያንቋሽሹብህ ኖረዋላ! "ለራስህ ሃይማኖት ማዳላት ነውር ነው" ብለውሃላ! እና በየት በኩል ሙሴ ትኾናለህ? በየት በኩል የነኢያሱና የነሶምሶን፥ የነአስቴርና የነዮዲት፥ የነዳዊትና የነሰሎሞን፥ የሐዋርያትና የሰማዕታት በረከት ይደርብህ? እነሱ'ኮ የቆሙት አንዲት ብቻ ለኾነችው የእግዚአብሔር እውነት ነው?!
አደንዛዦችህ፡ "ወገንተኝነት ተው" የሚል ስብከት የሚነግሩህ፡ ላንተ ብቻ እኮ ነው?! እነሱ አያምኑበትም። የምትጠፋበትን መንገድ ብቻ ነው የሚቆምሩልህ።
በያጋጣሚው፡ ፊት ለፊት በሽልማት በእውቅናና በምስጋና ፕሮግራም ሲያሞግሡና ሲያደንቁልህ የምታያቸው፡ ለአንተ አርአያ እንዲኾኑ የሚፈልጓቸውን መንፈሳዊ አቋም የሌላቸው መሃል ሰፋሪዎችን ነው። ለሃይማኖቱ የቆመ ሰው፡ በዚህ ዘመን "አደገኛ" እና "በኅብረተሰቡ መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚሠራ" እንደኾነ አሳምነውሃል። አንተም ተቀብለኸዋል።
ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ሆይ!
ብዙዎቻችሁ፡ በማይመስሏችሁ ሰዎች የሶሻል ሚድያ account ሥር follower እና subscriber ኾናችሁ ተኮልኩላችሁ ሳያችሁ እጅግ ይገርመኛል። Atheist, መናፍቅ፥ ፀረ-ኦርቶዶክስ የኾኑ ገጾች ላይ ምን ትሠራላችሁ? የግድ የሚያስቅ ነገር ስለጻፈ እኮ follow ማድረግ አለባችሁ ማለት አይደለም? የግድ መልኳን አሳምራ ስለመጣች እኮ እንደምታምር ለመንገር ገጿ ላይ ተሰልፋችሁ መዋል አለባችሁ ማለት አይደለም? እሷ እኮ ሥራዋን እየሠራች ነው? እሱ እኮ ከላይ የዘረዘርኩላችሁን ደካማ ሥነ ልቦና እያሠረጸባችሁ ነው? ምን ኾናችሁ ነው አፋችሁን ከፍታችሁ በየatheist እና በየመናፍቁ ገጽ ስትጃጃሉ የምትውሉት?
ለነገሩ፡ በአንድ ጥሪ 2000 ዓመት የኖረ የገና ማኅሌት ትቶ አደባባይ ያመሸ ትውልድ አይደል? ነገ ጠዋት አንዱ ተነሥቶ፡ "ባሁኑ እሑድ ቅዳሴ የለም፤ ፍኖተ ጽድቅ አዳራሽ ተገናኝተን እንዘምር" ቢሉት ተከትሎ ይኼዳል። ይኽ ሰይፍና ገጀራን የሚቋቋም ትውልድ አይደለም።
መልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ "ይኽ ትውልድ እንደጎመን የሚቀረደድ ትውልድ ነው፤ ቡዳ በልቶታል" ብለዋል።
እውነታቸውን ነው!
ማንም በቀላሉ እንደ ጓሮ ጎመኑ ይቀነጥሰዋል።
አደንዛዦችህ፡ ቀን ቢሮ ገብተው ሲያደነዝዙህ የሚውሉ፡ አስቀድመው ሌሊት ለዲያቢሎስ ሠውተው ነው። ከላይ ስታያቸው፡ አለባበሳቸው፥ አነጋገራቸው፥ አጻጻፋቸው፡ እንዲህ ያለ የመንፈስ ነገር የሚገባቸው አይመስሉም። "የምን ኢሉሚናቲ ነው? እንዲህ ያለ የተጨናነቀ ወሬ አታውራብኝ። እኔ በሰብአዊነት፥ ደግ በመኾን፥ ኹሉን እኩል በመውደድ ነው የማምነው፤ ክርስቶስ ፍቅርን አይደል ያስተማረው?" ይሉሃል። የማይጠቅሱልህ ፈላስፋና የፈረንጅ ወይም የዐረብ ባለቅኔ የለም። የእውቀት ሰው መስለውሃል። የእምነትና የገርነት ቢበዛም የሜካፕ ሰው ብቻ መስላሃለች። ግን፡ በሌሊት ለዲያቢሎስ የሚሠዉትን ሠውተው ነው የሚመጡት። አጀንዳቸውም አንተ ነህ--ኦርቶዶክሳዊው ወጣት። ትፈዝዝና ትደነግዝ ዘንድ፥ ትጃጃል ዘንድ፥ አምላክህ ሊነግርህ የሚፈልገውን እንዳትሰማ፥ ዓይንህን ሊገልጥልህ ለሚፈልገው እውነት እንዳትገልጥ፡ በፍቅርና በወሲብ፥ በፍልስፍናና በ"ሥልጡን ባሕሪ" ስም፡ ልፍስፍስነትን አስተምረው የተቀቀለ ፓስታ አድርገውሃል።
እና... ተኝተህ ተኝተህ ድንገት ትነሣና፡ እርምህን ብትቃወም፡ የምትቃወመው የራስህን ሰው ነው። ለቤተክርስቲያን ጥብቅና የቆመውን፥ ድምጹ እስኪነቃ የሚጮኸውን "ይኼ ሰውዬ አይመቸኝም! እንደዚህ ክርር ሲሉ ይደብሩኛል" እያልህ ትተቻለህ። ጅላንፎ!
እና በየትኛው ጸሎትህና እምነትህ ነው የአሩሲዋን እመቤት ዘንዶ ተዋግተህ የምታሸንፈው? በየትኛው ጾምህና ስግደትህ ነው በየወንዙና በየተራራው በአገሪቱ ሲመለክ የኖረውንና አሁን ፖለቲካ ኾኖ መጥቶ ጠምዝዞ ሊውጥህ የደረሰውን ዛር ተዋግተህ ወደ ጥልቁ የምትጥለው?
እየተነገራችሁ አሁንም ትጃጃላላችሁ። ይገርመኛል።
አርሲ ኼዶ ለመዋጋት የሚያበቃ ዝግጅት ላይኖርህ ይችላል።
እስኪ ከአንድ ዘፋኝ፥ መናፍቅ፥ ኤቴይስት የsocial media ገጽ ላይ unsubscribe አድርጎ ከመውረድ ጀምር?
እሱንም ከቻልህ አንድ ነገር ነው!
ዱሮ ከጣልያን ጋር ተዋግተው ያሸነፉት ኢትዮጵያውያን እኮ፡ ልጃቸው ዘፋኝ ስትኾንባቸው፡ ከቤት አስወጥተው ያባርሩ የነበሩ ጠንካሮች መንፈሳውያን ነበሩ?!
አንተ፡ አሩሲ ፈረቀሳ በሌሊት እየኼደች፡ የድምፅ፥ የመወደድ ሞገስ፥ የዝና፥ የገንዘብ፥ የአነሁላይ የሰውነት ቅርጽና የወጣትነት ድግሞት አስደግማ የምትመጣ አርቲስት አድናቂና አጃቢ ኾነህ ትኖርና፡ ድንገት "በአርሲ ኦርቶዶክሳውያን ተጨፈጨፉ" ሲባል ጭንቅላትህ ዜናውን መረዳት ራሱ ያቅተዋል። ስታስተውል ስላልኖርክ ኹሉ ነገር ድንገት ይኾንብሃል። "ሌላ ችግር ቢኖር ነው እንጂ ነገሩ የሃይማኖት አይደለም፤ የኛዎቹ ገገማ አክራሪዎች ናቸው እንደዚያ የሚያጮሁት" ብለህም ራስህን ታጽናናለህ።
አንተ የምትኖርበት የሽንጥና የዳሌ ዓለም እና መሬት ላይ ያለው እውነታ አንድ አይደሉም።
እስኪ፡ ሰው ለመኾን፡ ከምትችለው ጀምር።
የግድ አርሲ ኼደህ መዋጋት አይጠበቅብህም።
ሰሞኑን ቀዝቃዛ ጠበል በጠዋት ተነሥተህ ከመጠመቅ ጀምር። እሱንም ከቻልክ አንድ ነገር ነው።
Blogger Comment
Facebook Comment