እንግዲህ ወገኖቼ መቼም ቢሆን ይታወቃል ከ20ኛው ክፍለዘመን ወዲህ በሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ መፅሐፍ ላይም በግልፅ እንደተቀመጠው የኃያላኑ የጨለማው ኃይላትና የሳጥናኤል ሙሉ ትኩረት ኢትዮጵያ እንደሆነች የታወቀ የአደባባይ ምስጢር ነው ለዚህ ምስክር ደግሞ እነሱ ራሳቸውና እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ። ኢትዮጵያ ዋና ትኩረታቸው ከሆነችባቸው ጥልቅ ጉዳዮች መካከል ደግሞ የራስ ደጀን የስውራን ስፍራ ሲሆን ወደ UNESCO የዓለም ቅርስነት የተመዘገበበትም ምክንያት እና በስሙ ጭምር (ዳሸን ቢራ) የተሰየመበትን ምክንያት በቅደም ተከተል ለመመልከት እሞክራለሁ ተከተሉኝ፦
የራስ ደጀን ተራራ እኛ እንደምናስበው ተራ ስፍራ ሳይሆን የቅኔው ሊቅና የቤተክርስቲያናችን አባት ቅዱስ ያሬድን ጨምሮ በርካታ ቅዱሳን አባቶችና መናንያን ተሰውረው ያሉበት ጥብቅ ስፍራ ነው፨ ለምሳሌ በቀላሉ ከዚያው ብዙም ሳይርቅ ከደጀን ተራራ በስተምዕራብ አቅጣጫ በሰሜን ጠለምት የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳምና (የተሰወረውም እዚሁ ስፍራ ነው) የፀበሉ መገኛ ቅዱስ ቦታ ነው። እንዲሁም በቅርብ ዓመታት በተደረገ ታሪክ በ1985 የቅዱስ ያሬድ የእጅ መስቀል ከዚሁ ቅዱስ ያሬድ ከተሰወረበት ገዳም ተሰርቆ ሔዶ በአሜሪካ በ15 ሚሊዮን ዶላር ሊሸጥ ሲል አንድ የታሪክ ተመራማሪ ይሄንን መስቀል ኢትዮጵያ አይቼዋለሁ ስለዚህ ለእነሱ መመለስ አለበት በሚል ተከራክሮና ጨረታውን አሸንፎ ከምርጥ ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር ከ18 ዓመታት በኋላ በ2003 ዓ.ም ወደ ገዳሙ በክብር ተመልሷል።
በተጨማሪም በዚህ የራስ ደጀን ተራራ ቅዱስ ስፍራ ላይ በግልፅ ያልታወቁና የተሰወሩ ጭምር ብዙ የመናንያን ዋሻዎች እንዳሉ ይታወቃል ይህም የሆነበት ምክንያት ብዙ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅርሶች እዚህ ስፍራ ላይ በመሸሸጋቸውና ምሥጢራቶቹም ሆኑ ቅዱሳን አባቶች በመጨረሻው የኢትዮጵያ ትንሳኤ እና ልዕልና ሰዓት ላይ የሚገለጡበትና ለዓለም ሁሉ የሚታዩበት ስፍራ በመሆኑ በጨለማው ኃይላት ይሄ ጉዳይ እንዳይወጣ የሚፈለግ በመሆኑ በጥብቅ ይመረምሩታል።
በተጨማሪም ልክ እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁሉ በዚህ ተራራ ስምም ዳሸን ቢራ ተብሎ የአልኮል መጠጥ በስሙ መሰየሙ በሁለት ምክንያቶች ሲሆን አንደኛው አንዱ ታርጌታቸው እና ስጋታቸው እሱ መሆኑን ለማመልከት ሲሆን ሌላው ደግሞ የወጣቱ ትኩረት ተራራውን እንደ ተራ ነገር ቆጥሮት እነሱ በሚሰጡት ኳስና ቁማር ላይ እንዲጠመድ በመፈለጋቸው ነው።
ወደ ዋናው ስጋታቸው ስንመጣ ደግሞ ከዚህ ታላቅ ተራራ የሚነሳ ሱናሚ ለአሜሪካ መጥፋት ዋና መንስኤ መሆኑን ጠንቅቀው ስለሚያውቁት ይሄ ደግሞ የአውሬው ሰባተኛ ራስ አንግሎ አሜሪካ(8ኛውን በውስጡ ይዟል) ለ2030 አዲስ የዓለም ስርአት(new world order) ስለሚያስቸግራቸውና እንዳይሳካ እንቅፋት ከሚሆኑባቸው ጉዳዮች መካከል በመሆኑ በጥብቅ ለማጥፋት ይፈልጉታል ዛቻም እስከ መሰንዘር ደርሰዋል።
ይህም የሆነበት ምክንያት ከምድራችን ስር ባለ የእሳት ባህር(የሳጥናኤል ጄነራል ሉሴፌል የታሰረበት የአፋር ኤርታሌ ልብ ይሏል?) አማካኝነት ምድር በእሳት ቀለበት የተከበበች ናት በዚህም የእሳት ፍሳሽ ተፅዕኖ ምክንያት ምድራችን በዓመት 20 ኪ.ሜ ወደ ምድረበዳነት ትቀየራለች። ታዲያ ይህ የእሳት ባህር ቀለበት በምድራችን ላይ ዛፎች በተተከሉ ቁጥር በዛፎቹ አማካኝነት ቅዝቃዜ ያገኛል። በዚያን ወቅት እንፋሎቱ በንፋስ አማካኝነት የምድርን ደረት ቀዶ ወደ ላይ ይተነፍሳል ይህንን ተከትሎም ንፋሱ ከፍተኛ ጥፋትን ያስከትላል የዚህ እንፋሎት(ንፋስ) መተንፈሻ ተብለው በምድራችን ላይ የሚጠቀሱ ሁለት ታላላቅ ስፍራዎች ሲገኙ አንዱ ይሄው ራሱ ራስ ደጀን ተራራ ነው ሁለተኛው የሜድትራንያን ባህር ነው።
ታዲያ ብዙ ከማይነገርለት እጅግ ምስጢራዊዉ ራስ ደጀን ተራራ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ደብል ቡሽን ጨምሮ የተለያዩ የዓለም ነገሥታት እንዲሁም ዓለም ላይ ያሉ የስውር የጽዋ ማህበራት የወንድማማቾች ማኅበር(the brothers)፣የፅዮን ፅዋ(the zions chalice) የተባሉ እጅግ ምስጢራዊ ማኅበራት ለበርካታ መቶ ዓመታት በግልፅና በስውር እየተመላለሱ ሲመረምሩት ቆይተዋል አሁንም እየመረመሩት ይገኛል።
ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ በዚህ መንግሥት አማካኝነት የተለያዩ ጉዳዮችን በተራራው አካባቢ ላይ ለመተግበር እየጣሩ ይገኛሉ። ስለዚህ እናስተውል ለማለት እወዳለሁ ሃሳባችሁን በአስተያየት መስጫ ሳጥኑ አስቀምጡልኝ ሻሎም።
Blogger Comment
Facebook Comment