መጽሐፈ አማልክት


ስለዚህ መጽሐፍፍ ከዓመታት ነግረናቹ ነበር፤ የኛዎቹ አንዳንድ ድንዙዛን ተረት ተረት ሲሉ እነሱ ፊልም ይሰሩበታል።
መጽሐፉ በስንተኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደተፃፈ ባይታወቅም። በውስጡ ስለ አማልክት እና አፈጣጠራቸው እንዲሁም በሰማያት ስላደረጉት ውግያ እና አጠፋፋቸው የሚተነትን መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ እጅግ የተወሳሰበ እና አስፈሪ ታሪክ በውስጡ ይዙዋል። በተለይም ሰዎች የሚያሳዩትን ባህሪና ድርጊት የእያንዳንዱን አማልክት ስም እየጠቀሰ ሲያገናኝ እውነትም ሰው በነፃ ፈቃዱ ሚያደርገው ነገር እንደሌለና ሰዎች ከራሳቸው በተሰወሩ አማልክትና መናፍስት ተፅእኖ ስር እንደሚኖሩ ይናገራል። አንድ ሰው ሁለት መሆኑንና ከራሱ ጋር የሚዞር አንድ ከማይታይ ከሱ ከተሰወረ ውቃቢ ከሚባል ፍጥረት ጋር እንደሚኖር ያወራል። ከእነኝህ አማልክትና መናፍስት ጥቃት እራሳችንን እንዴት እንደምንከላከል አቅጣጫም ይጠቁማል። አማልክት አሉ የሉም የሚል ጥያቄ ይነሳል ነገር ግን አማልክት ባይኖሩ ኖሮ እግዚአብሔርም "የአማላክት አምላክ" አይባልም ነበር።

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment