እንደቁራ የጠቆሩት ምንድን ናቸው ቢለው

"ሹመት ፈላጊዎች ፣ ገንዘብ ወዳጆች ፣ በጠዋቱ ከመኳንንቱ ጋር ለማዕድ የሚቀመጡ ፣ በፍጻሜ ዘመን የሚነሡ ኃጥኣን መነኮሳት ናቸው።" አለው። 

 አመክሮ፣ ትምህርት፣ ሕይወት፣ እውነትና እውቀት ሳይኖረው መንኩሶ፣ ከዚያም ቆምሶ ቀጥሎም ጰጵሶ የምናየው ሲሞናዊ ሕይወቱ በዘመነ እንጦንስ ወመቃርስ ከ1800 ዓመታት በፊት  እንዲህ ተነግሮ በመጽሐፈ መነኮሳቱ ተጽፎ እናገኘዋለን 

አባ እንጦንስ አባ ጳውሊን ሊጠይቀው በሔደ ጊዜ አባ ጳውሊን ፦ "እስኪ ይህ ሥርዓተ ምንኩስና ከእኔ በኋላ ይቀራል ወይስ ይቀጥላል የሚለውን ከእግዚአብሔር ጠይቅልኝ?" አለው።

አባ ጳውሊም በጸሎት እግዚአብሔርን ጠየቀለት፡ 

ከጸሎቱ በኋላ የአባ ጳውሊ ገጽ በደስታ ተመላ። አባ እንጦንስም ፦ "ምን አየህ?" ብሎ ጠየቀው:: አባ ጳውሊም "ነጫጭ ርግቦች አንተ እየመራኻቸው በጠፈር ላይ ሲሔዱ አየሁ" አለው። አባ እንጦንስም ፦ "ምንድን ናቸው? ሲል ጠየቀው። "በቆብ የምትወልዳቸው ንጹሐን ጻድቃን መነኮሳት ናቸው" አለው። 

አባ እንጦንስም ፦ "እስኪ ደግመህ አመልክትልኝ" ብሎ ለመነው በድጋሚ ሲጸልይ የአባ ጳውሊ ፊቱ በሐዘን ተመላ። "ምነው?" ሲል አባ እንጦንስ አባ ጳውሊን ጠየቀው:: "በክንፋቸው ላይ ጥቁር መልክ የተቀላቀለባቸውን ርግቦች አየሁ" አለው። "እነዚህ ደግሞ ምንድን ናቸው?" ሲል አባ እንጦንስ ጠየቀ። "ጽድቅና ኃጢኣት እየቀላቀሉ የሚሠሩ መነኮስት ናቸው" አለው::

"እስኪ ለሦስተኛ ጊዜ አመልክትልኝ" አለና ለመነው:: አባ ጳውሊም ጸለየለት። በዚህ ጊዜ አባ ጳውሊ ድምፁን ከፍ አድርጐ ጮኾ አለቀሰ፡፡ አባ እንጦንስም "ምነው ምን ሆንክ?" አለው። 

"እንደ ቁራ ጠቁረው አየኋቸው" ሲል መለሰለት። "ምንድን ናቸው?" ቢለው "ሹመት ፈላጊዎች ፣ ገንዘብ ወዳጆች ፣ በጠዋቱ ከመኳንንቱ ጋር ለማዕድ የሚቀመጡ ፣ በፍጻሜ ዘመን የሚነሡ ኃጥኣን መነኮሳት ናቸው።" አለው። 

አባ እንጦንስም "ንስሐ ሳይገቡ በሞት እንዳይወስዳቸው እስኪ እግዚአብሔርን ለምንልኝ" አለው። የዚህ መልስ ግን ከአባ ጳውሊ አልመጣለትም።

አሁን እየሆነ ያለው ይኸ ነው። 

ከመክራከር መመከርና አመክሮ ተቀብሎ ሥርዓትን ማክበር።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment