✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ አውታር | ሰላቢ እጆች
በሰሜን አየርላንድ፣ ባለፈው ሳምንት በርካታ ምሽቶች ላይ ኃይለኛና ዘረኛ በተለይ አፍሪካውያንን የሚያሳድዱ ተቃውሞዎች ተካሂደዋል። መንስኤው አንድ ሱዳናዊ ስደተኛ በአንድ ነጭ አይርላንዳዊ ላይ የፈጠረው ጭካኔ የተሞላበት የቢላ ጥቃት ተንቀሳቃሽ ምስል ወድምጽ/ቪዲዮ መውጣቱ ነበር።
አሁን በቤልፋስት እና በአካባቢው የተፈጠረው ግጭት ለሁለተናው የጀርመን ብሔራዊ መስኮተ ትዕይንት/ቴሌቭዥን የችግር ጉዳይ እየሆነ መጥቷል። አዲስ የተመረተው ዘረኛው ቢሊየነር ኢለን ማስክ በመስኮተ ትዕይንት/ቴሌቪዥኑ ሠሪዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል። ዳራው በ መስኮተ ትዕይንቱ/ቴሌቪዥኑ አንድ መርሐ ግብር/ፕሮግራም ላይ፤ “ኢለን ማስክ እና ቀኝ አክራሪው ብሪታኒያዊ ቶሚ ሮቢንሰን ነጭ ዜጎቻቸው በተለይ በየመንገዱና በየቤታቸው አፍሪካውያንን እያደኑ እንዲጨፈጭፏቸው በኤክስ (X) ጥሪዎቻቸውን ለብዙ መቶ ሚሊየን ተከታዮቻቸው አሰራጭተው ነበር” የሚል ዘገባ በማቅረቡ ነው።
ይህ ምንም የማያጠራጥር ነው፤ እያየናቸውና እየሰማናቸው እኮ ነው። ዘረኛው ኢለን ማስክ አፍሪካውያንን/ጥቁር ሰዎችን አጥብቆ እንደሚጠላ ዓለም ያወቀው ነገር ነው። እኔ እንኳን የኢለን ማስክን ዘረኝነት የታዘብኩት ከአስር ዓመታት በፊት ዶናልድ ትራምፕ በፕሬዝደንት እጩነት ቅስቀሳዎችን ባደረጉበት ወቅት ነበር። መድረክ ላይ ዶናልድ ትራምፕ፣ ኢለን ማስክ እና ራፐሩ ካንየ ዌስት ቆመው ይታዩ ነበር። የኢለን ማስክ ለካንየ ዌስት ያሳየው ዘረኛ የሰውነት ቋንቋው ግልጥ ብሎ ታይቶኝ ነበር።
በዚህች ዓለም 'አዳሜ' ወይም 'ሰው' ያልሆኑ ሰው-መሰል ፍጥረታት በጥቁሩም፣ በነጩም፣ በቢጫውም መካከል አሉ። በኢትዮጵያም አሉ። አደገናው ኢለን ማስክ እና ካሳደጋት ከራሱ ሴት ልጅ የወለደው አባቱ የቆዳ ቀለምን ወይንም የዘረኝነትን ካርድ መዝዘው በተለይ በነጮች መካከል ሰው የሆኑትን ምስኪኖች ወደ ሲዖል ከእነርሱ ጋር ለመውሰድ ነው እየሠሩ ያሉት። አሥሬ 'ማርስ፣ ማርስ' የሚለው 'ሲዖል' መሆኑ ነው። የኢለን አባት ኤሮል እና ብሪታንያዊው ቶሚ ሮቢንሰን ሰሞኑን ወደ ሞስኮ በመጓዝ ከፑቲን ጋር ተገናኝተው ነበር። እንግዲህ የሁሉም ዓላማቸው እነርሱ 'አውሮፓዊ፣ ነጭ፣ ካውካሲያዊ' የሆኑትን ሕዝቦች አንድ አድርጎ ዓለምን ለሉሲፈር ከመስዋዕት ጋር ማቅረብ ነው። በአርሜኒያ፣ በኢትዮጵያ፣ በየመን፣ በሶርያ፣ በኢራቅ፣ በኢራን፣ በዩክሬን የሚካሄዱት ጦርነቶች የዚህ ዲያብሎሳዊ ሤራ መንገዶች ናቸው። የክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ የኤሳው እና እስማኤል ሤራ ነው ፥ እስራኤል ዘ-ስጋም ከበስተጀርባው አለችበት።
ለማንኛውም ሉሲፈራውያኑ እና አሻንጉሊቶቻቸው እንደ ዶናልድ ትራምፕ እና እንደ ኢለን ማስክ ያሉትን ቅጥረኞች በገንዘብና በሚቻለው ነገር ሁሉ ለዚህ ያበቃቸው ሲ.አይ.ኤ እና ስውር መንግስቱ በዓለም ላይ የ'ዘር' የተሰኘው ግጭትና ጦርነት ይቀሰቀስ ዘንድ በጣም ይፈልጉታል። ደግሞም ጀምረውታል። ቀደም ሲል በዩጎዝላቪያ፣ ዛሬ ደግሞ በኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ እያየነው ነው። ኢትዮጵያውያን ሆይ፤ ሰውየው የዓለማችን አደገኛና መሰሪ ፍጡር ነውና የኢለን መስክን ነገሮች ከመገልገል ተቆጠቡ፤ በኮምፒውተሮቻችንም በኩል ይጠብሱናልና እንደ ኤክስ (X) ካሉ ቦታዎች ቶሎ ውጡ!!!
Blogger Comment
Facebook Comment