✍ ፋንታሁን ዋቄ | ፍኖተ ርቱዓን | ሞዐ ተዋህዶ
ከሰው ልጅ ክብር የሚበልጥ ልማት አለ ከተባለ "የሞት ዕፀ-በለስን የሕይወት መደኃኒት ነው" በማለት ተንኮል ምንም ስለ ሤራ የማያውቁትን የዋሐንን አዳምንና ሔዋንን አታልሎ ሞትን ካስታቀፍው ከሳጥናኤል እና ከብልጽግና ወንጌል መንግሥት በስተቀር ማንም ጥቅሙን አያውቅም።
የብልጽግና ወንጌል ሃይማኖታዊ መንግሥት ማኅቀፈ-ዕሳቤ (worldview) ይገርመኛል።
የዚህ ሥርዓት መሪና አጃቢዎቹም ሆኑ ወላጆቹ ሕወሃትና ኦነግ፤ አዋላጆቹ ደግሞ ዉሀብያ፣ ተረፈ ናዚዎቹ፣ ጡጦ አጥቢዎቹ ባዕዳን እንደመሩት
👉 ሞትን ሕይወት፣
👉 መፍናቀልን እደገት፣
👉 መፍረስን ከፍታ፣
👉 መለያየትን ነጻነት፣
👉 ጦርነትን ሕግ ማስከበር፣
👉 እልቂትን abnormal-normal (በአብይ አህመድ አሊ በፓርላማ የተነገር ነውር)፣
👉 የታሪክ ንቅለ ተከላን ታላቁ ትርክት፣
👉 ሲኖዶስን ወደ ጎሣ ምክር ቤት ማውርድን አካታችነት፣ ---- በሚል የሚተረጉም ከሰውልጅ ህሊና ፈልቆ ለሰው ልጆች ጥቅም የተደረገ ነው ለማለት የማያስችል ጸረ-ሰብእ ትርጓሜ በመስጠት የመከራ ሥርዓትን የሚመራ ነው።
ሰማይ የተሰቀለለትን፣ ምድር የተዘረጋለትን ክቡር አዳማዊ ፍጡር እያረዱና እያሳደዱ ---- ያለ ሁፍረት በሬሳ ላይ ቆሞ፣ ደም ውስጥ እየዋኘ፣ በሚገፉት ወገኖቻችን ዕንባ እየታጠበ ------
ስንዴ፣ ግድብ፣ ወደብ፣ #ችግኝ፣ #ኮሪደር ልማት፣ ሰፊ አስፋልት፣ ረዥም ፎቅ፣ ደማቅ መብራት፣ የፎቶ ዲፕሎማሲ ለሚጨፈጨፍ ክፍለ-ሕዝብ ምኑ ነው??
ልማት እና ሥልጣኔ ምናልባት እነርሱ "ብልጽግና" የሚሉት ነገር ሰውን የማይመለከት አድርገው ለማቅረብ እጅግ ይደክማሉ።
የእነዚህ ዘረኞች ብልጽግናቸው እነርሱ ለመረጡት እናንልዩ ጥቅም ይገባዋል ለሚሉት ይወገን ብቻና ብቻ ይመስላል። ለዚህም ብልጽግናቸው ከሚጨርሱት፣ ከሚያፈናቅሉት፣ በባርነት ለአረብ ከሚሽጡት፣ በድሮን ከሚገድሉት፣ ከእምነታቸውና ባህላቸው ከሚያፈናቅሏቸው፣ ታሪካቸውንና ውርሳቸውን ከሚደመስሱበት የሃይማኖትና ይፕቋንቋ ክፍለ-ሕዝብ ፋር ግኑኝነት የለዉም።
ይህም ይታወቅ ዘንድ 30 + 8 በመዋቅራዊ መንገድ ከበደኖ ጀምሮ በሁሉም ማዕዘን እስከ እርሲ ስለሚፈጁት፣ ስለሚያፈናቅሉት ርስት ስለሚቀሙት ሕዝብ በፓርላማቸው: በፖለቲካ ጠፍጥፈው ወደ አግልጋይነት የቀየሩት ሲኖዴስና መጅልስ አጀንዳ እንዳይሆን ይከላከላሉ።
በ39 ል8 የጥፋት ዘመናት ሁሉ ፍትህ ያገኝና የተካሠ ተጎጅ፣ የተከሰሰ ጎጅ፣ ከሥልጣኑ የተባረረ እረኝነት የነፈገ ኃላፊ የለም።
ከዙህ አንጻር የአብይ አህመድ አሊ የጓዶቹ ብልጽግና የአሰፋ ጃለታና የሸምሰዲን ማጋላሞቱስ ናዚያዊንዘር የማጥፋት ፍልስፍናን የተከተለ ነው።
ይህ መገታት ስለሚገባው ዒላማ የተደረገው ኦርዶሮክሳዊ ክርስቲያን እና በቋንቋ ዘውግ ዒላማ የተደረገው ብቻ ሳይሆን በብልጽግና ስም የጥፋት መሣሪያ የሆነው ቀሪው የዘር ፖለቲካ የአእምሮ ባሪያቸው የሆነው ወገን ነቅቶ መፍትሔ መስጠት አለበት።
Blogger Comment
Facebook Comment