ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ልዩ መልእክት



✍ ቆሞስ አባ ጳውሊ | ከግንባር

የሀገር መከላከያ ሰራዊት የአንድን ሀገር ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነት እና የህዝብን ደህንነት ከውጭ ወረራና ከውስጥ ስጋቶች ለመጠበቅ በህግ የሚቋቋም የታጠቀ ኃይል ነው።  ዋና ዓላማው ሉዓላዊነትን ማስከበር ሲሆን ይኸው የሀገሪቱን ድንበር ከማንኛውም የውጭ ጠላት ጥቃት መከላከል ነው። ሌላኛው ዓብይ ስራው ደግሞ ህገ-መንግስቱን መከላከል (ከአምባገነን ስርዓት) እና ሰላም ማስከበር ነው:: የሀገር መከላከያ ሰራዊት መርሆዎች ያሉት ሲሆን ከማንኛውም ፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ መሆን እንዳለበት ይታወቃል:: የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ሳይሆን ለህገ-መንግስቱ የታመነ ከሁሉም ብሄር ብሄረሰቦችም የተውጣጣ ለህዝብ ብቻ የሚቆምም ነው:: 

 ሆኖም ግን የአሁኑ የብልጽግና መከላከያ ሰራዊት ይህን አምባገነን ስርዓት ለማስቀጠል የሚጥር የወንበ*ዴዎችና  ሀገር ፍቅር የሌላቸው ስብስብ ነው::   አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጣ ጀመሮ ዳር ደንበርን ክፍት አድርጎ የውጭ ጠላት እየፈነጨበት መንደር ለመንደር ህጻናትን ሳይቀር አረጋዊያንንም ጭምር የሚጨ*ፈጭፍ  እጅግ አረመኔያዊ ኃይል ነው::  ኢትዮጵያ ወደ ከፍተኛ ቀውስ እንድትገባ ዋነኛው ተጠያቂ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እንደሆነ ሁላችንም መገንዘብ ይኖርብናል:: ህዝብ በቃን ስርዓቱን አንፈልግም ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ  ከመጨፍጨፍ ጀምሮ ህግ ለማስከበር ብሎ በትግራይና በአማራ ክልል ተሰማርቶ የሰራው ግፍ እጅግ የሚዘገንን ነው:: በአሁኑ ሰዓት በመላው የአማራ ህዝብ በየቀኑ ከሚጨፈጨፉት በዘለለ የሚ*ደፈሩ  ሴቶች ስፍር ቁጥር የላቸውም! መከላከያ ሆይ አንተ ከህዝብ መውጣትህን እንዴት እረሳህ? የህዝብ ልጅ አይደለህምን? ወደ እናትህ ፣ አባት ፣ እህትና ወንድምህ እንዴት በጭካኔ ትተኩሳለህ? የቆምክበትን ዓላማ በእውኑ ታስተውለዋለህን?  መንግስት ይሄዳል መንግስት ይመጣል አሮጌ ስርዓት ያልፋል አድስ ስርዓት ይተካልም! ሀገርን የሚጠብቅ የህዝብ ልጅ ግን ቋሚ ነው!  እርጅና እና ሞት ካልገደበው የህዝብ ልጅ ለህዝብ የሚቆም ነው::   ውድ የመከላከያ  ሰራዊት አባላት ወገኖቻችን እባካችሁን አስተውሉ! መንግስት እናንተን ከህዝብና ከታሪክ ጋር እንድትጣሉ አድርጓል::  ትላንት በሰሜን ጦርነት የከፈላችሁት መስዋ*ዕትነት ከንቱ እንደነበር ዘንግታችሁት ነውን?  ስንቶቹ ረገፉ? ስንቶቹስ አካለ ስን*ኩላን ሆነው ተስፋቸው ጨልሞ በስቃይ እየኖሩ ነው? መንግስት ዞር ብሎ አላያቸውም! እናንተም ነገ ተመሳሳይ እድል እንደሚገጥማችሁ መረዳት አለባችሁ:: ታሪክም ሲወቅሳችሁ ይኖራል:: ጥንት ኢትዮጵያን ያቆዩልን አርበኞች(የኢትዮጵያ ፋኖ አባላት)  ሀገራችንን በደምና በአጥንት መሰረት ነው:: እነርሱም ሀገርን ጠበቁ ዳር ደንበርን አስከበሩ ታሪክም ለዘላለም ሲዘክራቸው ይኖራል:: 

በመሰረቱ አሁን ያለው የአብይ አህመድ ስልጣን አስጠባቂ ኃይል (መከላከያ) ምንም ወታደራዊ ድስፕሊንም ይሁን ሰብዓዊነት የሚሰማው አይደለም:: አብዛኛዎቹ የመከላከያ ሰራዊት  የኦሮሞ ልዩ ኃይል አባላት ስለሆኑ የአማራ ጥላቻ ስላለባቸውም ጭምር ህዝብን ለማሰቃየትና ክልሉን ለማውደም የተሰማሩ ናቸው::  

እውነተኛ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የነበራችሁና አሁን ሰላም ለማስከበር በሚል በመንግስት ፕሮፖጋንዳ ተታላችሁ ህዝብን እየበደላችሁ እናንተም በከንቱ መስዋዕት እየሆናችሁ ያላችሁ ሁላችሁም አስተውሉ!   የገጠማችሁት ከህዝብ ጋር እንጅ ከተወሰኑ አማጽያን ጋር አይደለም!  ኢትዮጵያን እንዳትፈርስ ከሚከላከልና ለኅልውናው ከሚታገል እውነተኛ ህዝብ ጋር ነውና ጸባችሁ ምንም አታሸንፉም!  

ያላችሁ አማራጭ ከህዝብ ጎን ቆሞ በታሪክ ከመወቀስ መዳን ብሎም ከንቱ መስዋዕትነትን ማስቀረት ነው::  ወደዳችሁም ጠላችሁም ምንም አታሸንፉም! ህዝብን ማሸነፍ አይቻልም!  ከህዝብ ጋር እውነት አለ! ህዝብ ሁሌም አሸናፊ ነው::  አብይ አህመድ መሽቶበታል! አትድከሙ!  እደግመዋለሁ አትድከሙ በከንቱ መስዋዕት አትሁኑ! 

ውድ በመከላከያ ውስጥ ያላችሁ ወገኖቻችን ሳይመሽ ንቁ! ሀገርን በጋራ ከውድቀቷ እናንሳትና ታሪክ እንስራ! ይህ ካልሆነ ግን አገዛዙ ጋር አብራችሁ ታሪክ ትሆናላችሁ ፤ ትውልድ የማይዘነጋው መጥፎ ታሪክ!  ድል አይቀርም አንድ ሆነን ኢትዮጵያን እንታደግ! ድል አይቀርም ድል አይቀርም! ኢትዮጵያ ታሸንፋለች አምባገነን ስርዓቱና ተባባሪው ኃይል ሁሉ ይወድቃሉ!


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment