ቡናን የተቸው ራፐር


ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ አውታር

በዘንድሮው የዩሮቪዥን የዘፈን ውድድር ላይ ኢስቶኒያን ወክሎ የተሳተፈው ራፐር፤ “ኤስፕሬሶ ማኪያቶ” በሚለው ዘፈኑ ጣልያኖችን ስለተቻቸው መላው ጣልያን ተበሳጭታለች። ዘፋኙ ቡናን፣ ጥንባሆን እና ማፊያን በመተቸት ነው የዘፈነው።

☕ እንግዲህ ቀደም ሲል ባቀረብኩት ጽሑፍ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ፤ "ከአልኮል (ጫት) እና ከማጨስ ብቻ ሳይሆን ከቡናም ይታቀባሉ!" ኤስቶኒያዊው ራፐር ቶሚ ካሽም፤ ቡናን፣ ጥንባሆን እና ማፊያን ይተቻል። ታዲያ እነዚህ ሰዎች

📖 ድርሳነ ጽዮንን አንብበው ይሆን?

🐦 ከአሥር ዓመታት በፊት፣ እስማኤላውያኑ አውሮፓን እንዲወሩ ኤዶማዊቷ ካንዝለር አንጌላ ሜርከል በሩን በከፈተችበት ወቅት የቀረበ መረጃ፤ “የበልግ ፍልሰት፡ የዩሮ-እስያውያን ክሬን አሞራ ከኢስቶኒያ ወደ ኢትዮጵያ የሚያደረገውን ፍልሰት አጠናቀቀ። በየዓመቱ በልግ ላይ ጉዟቸው ወደ ኢትዮጵያ ነው! ይህ እኮ ድንቅ የእግዚአብሔር ሥራ ነው!

👉 ጫት፣ ቡና እና ጥንባሆ 👈

ጫት የዲያብሎስ ተክል ነው።
ቡና የዲያብሎስ መጠጥ ነው።
ትንባሆ የዲያብሎስ አረም ነው።
ጫት ወይም ቻት የኢትዮጵያ ሚስጥራዊ የጂሃድ ተክል ነው።
ቡና የኢትዮጵያ ሚስጥራዊ የጂሃድ መጠጥ ነው።
ትንባሆ (መነሻው ከቦሊቪያ ነው) ግን የኢትዮጵያ ሚስጥራዊ የጂሃድ አረም ነው።

📖 በድርሳነ ፅዮን ላይ ስለ ቡና ስለ ጫትና ስለ ጥንባሆ ምን እንደተጻፈ እናንብብ፤ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን።

፩.ተዓምር

ተአምሪሀ ለጽዮን እምነ ሰማያዊት ጸሎታ ወበረከታ የሀሉ ምስለ ሕዝበ ክርስቲያን ለአለም አለም አሜን።

ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ ልንገራችሁ ስሙ የተፃፈ መፅሐፍ ሁሉ እኛ ልንመከርበት ተፅፏል እንዳለ ጳውሎስ ሮሜ ፲፫፥፬፣ከአዳም ልጆች ወገን ሴሩህ የሚባል ሰው ነበር ለሴሩህም ስሙ ብኑ የሚባል ልጅ ተወልዶ በህፃንነቱ ሞተበት በብኑ ስም በተቀረፀው ጣኦት መመለክ ተጀምሯል በመቃብሩም ላይ ሰይጣን የሚወዳት ከሱስ የተነሳ ፆምን የምታሽር የከፋች እፅ በቀለች ይኽውም ከስንዴ መካከል እንክርዳድን የዘራ ጠላት ዲያቢሎስ ካለችበት አምጥቶ ዘራት።ማቴ ፲፫13÷፳፰

በብኑ ስም ቡን ተብላለች ቡና ማለት ነው ማክሰኞ ከተፈጠሩት ዕፅዋት መልካምና ክፉ ክፉ ፍሬ ያፈራል እንዳለ። ማቴዎስ ፯÷፲፪

እስማኤላውያን የሚያመልኳቸው የጣኦታቸው መሥዋዕት ሆነች የተንባላት አለቃ የሚሆን እስከ መሀመድም ትደርሳለች ተንባላትም ያለ እሷ ሌላ አይሰውም ተንባላት ማለት የመሐመድ ተከታዮች ናቸው ጣኦት የሚያመልኩ ባለዛሮችም ይህችኑ ይሰዋሉ የቡና ሱስ ያዘን ብለው ጾምን የሚሽሩ በበአል የሚወቅጡ ራሳችንን አመመን በማለት በውስጣቸው ላደረ ለሱስ ጋኔን ይሚገብሩ ብዙዎች ናቸው ወደ ቅዳሴም እንዳይሄዱ በጠዋት እሷን እየጠጡ ይችም ዕፅ ክፉ ሁና ሰውን ስታሳስት ትኖራለች።

በሰለሞን ምሳሌያት ትርጓሜ ፲፫፥፲ክፉውን ሰው ወንድሜ እንደዚህ ያለ ነገር ለምን ታደርጋለህ ቢሉት እንደፈለግሁ ልሁን ልሁን ለራስህ እወቅ እያለ ይነቅፋል ይላል እኛስ መንቀፍ ትተን ከቶ ብንተው ምን ይጎዳናል ትርጓሜ ወንጌልም ዮሀንስ የሚያሰክር ቡን አልጠጣም መንፈስ ቅዱስ አድሮበታልና ይላል ሉቃስ ፩÷፲፭

እኛስ በአርብ ቀን መንፈስ ቅዱስን ተቀብለን የለምን የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ አካላችን የሱስ ጋኔን ማደሪያ ለምን ይሆናል።

o የሰማያዊት የእናታችን የጽዮን ጸሎቷና በረከቷ ከኛ ጋር ይሁን ለዘለአለሙ አሜን።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment